2013-02-20 15:39:55

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የቫቲካን ረዲዮ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ አስመርቶ የሚያቀርበው ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር መሠረት ትላንትና “እግዚአብሔር ማን ነው? በእርሱ አምናለሁ ሲባል ምን ማለት ነው?” የተሰየሙት ጥያቄዎች ማእከል በማድረግ አባ ኮዋልዝይክ ባቀረቡት 14ኛው አስተምህሮ፦ “በእግዚአብሔር አምናለሁ” ይኽ ደግሞ በአንቀጸ ተአምኖተ ሃይማኖት የሚደገም ቀዳሜ ሃሳብ ነው። ነቢይ ኢሳያስ በምዕ. 44 ቍ.6 እግዚአብሔር ‘እኔ ፊተኛ ነኝ…እኔ ኋላኛ ነኝ’ ይላል፣ እግዚአብሔር የነገሮች ሁሉ መሠረትና አናሥር ነው። የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በምዕራፍ አንድ በአንቀጽ አንድ ‘ሁሉን በሚችል ሰማይና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አምናለሁ’፦ ይክ የሐዋርያት ጸሎተ ሃይማኖት (ተአምኖተ ሃይማኖት) ቀዳሚ ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን መሠረትም ነው። መላው ጸሎተ ሃይማኖት የሚናገረው ስለ እግዚአብሔር ይሁን እንጂ ስለ ሰውና ዓለምም ከእግዚአብሔር እንጻር ያወሳል። ልክ ቀሪዎች ትእዛዛት በመጀመሪያው ላይ የተመሠረቱ ናቸው፣ ቀሪዎቹ አንቀጾች እግዚአብሔር ደረጃ በደረጃ ራሱን ለሰው መግለጡን ይበልጥ እንድንረዳ ያግዙናል። ፈላስፋው ቡበር ‘እግዚአብሔር የሚለው ቃል በሰው ልጅ ቋንቋ ብዙ በትክክልም ይሁን በማዛባት ብዙ የተባለበት ርእስ ነው’ ይላል፣ እውነትም ነው”
በእግዚአብሔር አላምንም ሲባል ምን ማለት ነው? ስለዚህ በእግዚአብሔር አላምንም የሚለው በጭንቅላቱ በአስተሳሰቡ ላለው እግዚአብሔር ነው አላምንም የሚለው። የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቅዱስ መጽሓፍ የተገለጠው የእግዚአብሔር የመለያ ስመ-ተግባር ያለውን ሁሉ ያቀርብልናል። ለምሳሌ በኦርት ዘጸአት ምዕ. 3 ቁ. 14 ያለና የሚኖር እኔ ነኝ…” ሲል ስሙን ያለና የሚኖር በማለት ለሙሴ ያስተዋውቃል። ይህ የእግዚአብሔር ስም በስነ ኅልውና እንዲሁም በፍልስፍና ረገድ ሊተነተንና ሊተረጎም ይችላል፣ ‘ያለ’ ሲል ታማኝነትን ያመለክታል፣ የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 206-207 ላይ ‘እኔ ያለሁ እሱ ነኝ-እኔ የሆንሁ ነኝ’ የሚለው የእግዚአብሔር ስም ትርጉም የአባቶቻችሁ አምላክ ነኝ-ከእናንተ ጋር እሆናለሁ በማለት ዘለዓለማዊ ታማኝነቱን ገልጧል” ሲል ያመለክታል። እንዲሁም በቁ. 212 እግዚአብሔር በሚገልጠው ስሙም አማካኝነት ‘በዘመናት ሂደት የእስራኤል እምነት በመለኮታዊ ስሙ መገለጥ ውስጥ ያለው ሙላት ሊያሳይና ጥልቅ ግንዛቤ ሊያስጨብጥ መቻሉንም’ ያመለክትልናል። ብለዋል።
በአዲስ ኪዳን ዘንድም አንደኛ የየውሐንስ መልእክት ምዕ. 4 ቁ. 8,16 ዘንድ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በማለት የእግዚአብሔር ስምና ተግባር የሆነው መለያው ፍቅር በሚል ቃል ተገልጦ እናገኛለን፣ ይኽ ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ያፈቅረናል ብቻ ሳይሆን የእርሱ መሆን ፍቅር መሆኑ የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 221 ‘እግዚአብሔር ፍቅር ነው…የእግዚአብሔር ህላዌ ራሱ ፍቅር ነው። ጊዜው ሲደርስ አንድያ ልጁንና የፍቅሩን መንፈስ በመላክ እግዚአብሔር ጥልቅ ምሥጢሩን ገልጦአል። እግዚአብሔር ራሱ ዘላለማዊ የሆነ የፍቅር የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ልውውጥ ነው፣ ሁላችንም የዚሁ ፍቅር ልውውጦች ተካፋዮች እንድንሆን ጠርቶና’ በማለት ይተነትነዋል” ካሉ በኋላ አባ ኮዋልዝይ አያይዘውም ቁ. 230 “ራሱን በሚገልጥበት ጊዜ እንኳን ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ ምሥጢር እንደሆነ ነው። ‘ልታውቁት ከቻላችሁ እርሱ እግዚአብሔር አይደለም (ቅዱስ አጎስጢኖስ)” ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ካወቅነው እግዚአብሔር ሊሆን እይችልም፣ የነገሮችን እውነተኛውን ምሥጢር የመሆን ጥልቅ ምሥጢር ተመክሮ ሲኖረን እግዚአብሔር ብለን ስለ ምንጠራው አካል ወይንም ኅላዌ ተመክሮ ይኖረናል” በማለት ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.