2013-01-31 18:04:14

የር.ሊ.ጳ. ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ባለፈው ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ አስተንትኖ “በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ” የሚሉትን የጸሎተ ሃይማኖት መክፈቻ ቃላት ተመልክተናል፣ ሆንም ግን የሚቀጥለው የጸሎተ ሃይማኖት ክፍል እግዚአብሔር አብ ማን መሆኑን በመግለጥ ይቀጥላል፣ እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል ሰማይና ምድርን የፈጠረ አባት ነው ይላል፣ በዛሬው ዕለት አባት በሚለው ቃል ለማትኰር እወዳለሁ፣ ጸሎተ ሃይማኖት የሚያቀርብልን የእግዚአብሔር መሰረታዊ መግለጫ እርሱ አባት መሆኑን ነው፣ ዛሬ ስለ አባት መናገር እንደ ወትሮው ቀላል አይደለም፣ በተለይ ደግሞ ቤተ ሰብ ተበታትኖ የሥራ ሁኔታ ሁሉን አፍኖ ይዞ ባለውና ብዙ አባቶችና እናቶች የቤተሰባቸው ፍጆታንና ገቢያቸውን ለማመዛዘን በሚቸገሩበትና የወደፊት ሁኔታ በሚያስጨንቃቸው ዘመን እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን በሁሉም በሚያካሄዱት ዘመቻና ሌሎች ችግሮች በልጆችና አባቶች መካከል ሊደረግ የሚገባውን ገንቢ ግኑኝነት በማውደም ይገኛሉ፣ አንዳንዴ እርስ መገናኘትም በብዙ ችግር ነው የሚከናወነው፣ አባታዊ መተማመንና ግኑኝነት እያስቸገረ ይገኛል፣ በዚህም እግዚአብሔር እንደ አባት ማቅረብ ከበድ ይላል፣ ባጭሩ ምሳሌና አብነት ሊሆኑ የሚችሉ አባቶች ማግኘት አስቸጋሪ ነው፣ ፈላጭ ቆራጭና የማታጠፍ አባት ወይንም ምንም የአባትነት ፍቅር የማያሳይ አባት የባሰውኑ ደግሞ ከነጭራሹ የጠፋ አባት ተመኵሮ ባለው ትውልድ እግዚአብሔር እንደ አባት እንዲመለከትና በመተማመን ሁሉም በእጁ እንዲተው ለማስተማር ማሰብ ቀላል አይደለም፣
ሆኖም ግን የቅዱስ መጽሐፍ ግልጸት ከእነዚህ ችግሮች ባሻገር እንድንሄድ ይረዳናል፣ ስለ እግዚአብሔር ሲነግረን ደግሞ እውነተኛ የአባት ትርጉምን ይገልጥልና፣ ከሁሉም ይህንን የእግዚአብሔር ገጽታ የሚገልጥልን ቅዱስ ወንጌል ነው፣ ለሰው ልጅ ደኅንነት ሲል እግዚአብሔር ዓለምን አንድያ ልጁን እስከመስጠት ያፈቀረ አባት መሆኑን ይገልጥልናል፣ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር ፍቅር ከዚህ ዓለም አባት ፍቅር እጅግ የላቀና የታመነና መጨረሻ የሌለው ቢሆንም ቅሉ በወንጌል የምናገኘው የአባት አሳቢነት መግለጫ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ትንሽም ቢሆን ልንረዳ ያስችለናል፣ “ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው?” (ማቴ 7፤9-11፣ ሉቃ 11፤11-13)፣ እግዚአብሔር አባታችን ነው ምክንያቱም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ስለባረከንና ስለመረጠን (ኤፈ 1፤3)፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ አደረገን (1ዮሐ 3፤1)፣ እንደ አባትም ቃሉ ትምህርቱ ጸጋውና መንፈሱን እየሰጠን እግዚአብሔር በኑሮአችን በፍቅሩ ይሸኘናል፣
ኢየሱስ እንደገለጠው እርሱ የሰማይ ወፈችን ምንም ሳይዘሩና ሳያጭዱ የሚመግብና የበረሃ አትክልቶችን ከሰለሙን የክብር ልብስ በበለጠ ውበጥ በሚያሸብርቁ አበቦች የሚሸልም አባት ነው (ማቴ 6፡26፤ ሉቃ 12፤24-28) አያይዞም ኢየሱስ እኛስ ከበረሃ አበቦችና ከሰማይ ወፎች አንበልጥምን ይላል፣ እግዚአብሔር “በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን የሚያወጣና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን የሚያዘንብ” (ማቴ 5፤45) ይህንን ያህል በጎ ከሆነ እኛም መንገድ የተሳሳትን እንደሆነ ሁሌ አለፍራቻና በሙሉ መተማመን በአባታዊ ምሕረቱ መተማመን እንችላለን፣ እግዚአብሔር የጠፋና የተጸጸተ ልጁን የሚቀበልና የሚያቅፍ መልካም አባት ነው (ሉቃ 15፤11) ለሚለምኑትም በነጻ የሚሰጥ አባት ነው (ማቴ 18፤19 ማር 11፤24 ዮሐ 16፤23) ለዘለዓለም የሚያኖር የሰማይ ኅብስትና የሕይወት ውኃ የሚሰጥ አባትም ነው (ዮሐ 6፤32.51.58)፣
ስለዚህም ነው ዘማሪው በመዝሙር 27 ላይ በጠላቶች በክፉ ሰዎችና በአቀናጣሪዎች ተከቦ ሳለ ከእግዚአብሔር እርዳታ ሲለምናና በእርሱም ሲማጠን ሙሉ እምነት እንዳለው “አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ” (ቍ 10) በማለት ምስክርነቱን ይሰጣል፣ እግዚአብሔር ልጆቹን የማይተው አባት ነው፣ አፍቃሪ አባት ሆኖ ከሰው ልጆች መተማመን እጅግ በላቀ መተማመን ዘለዓለማዊን ደኅነት እንዲከፍትልን የሚደግፍ የሚረዳ የሚቀበል የሚምርና የሚያድን አባት ነው፣ ምክንያቱም ዘማሪው በመዝሙር 136 ላይ የደህንነት ታሪክን እየተረከ በእያንዳንዱ ኁልቍ መጨረሻ ላይ እንደሊጣንያ በመደጋገም “ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና”፣ የእግዚአብሔር አባት ፍቅር አይጎድለም አይደክምም ልጁን መሥዋዕት በመስጠት እስከ መጨረሻ የሚያፈቅር ወደር የሌለው ፍቅር ነውና፣ እምነት ይህንን እርግጠኝነት ይሰጠናል፣ ይህም ሕይወታችን ለመገንባት የማነቃነቅ የመሠረት አለት ይሆንልናል፣ የጨለማው ተመክሮ የብርቱ ሥቃይ ጊዜ ተመኩሮ ብቻችን በማይተወንና ሊያድነና ለዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲያደርሰን ሁሌ አጠገባችን ባለው እግዜብሔር መተማመን ተድግፈን አስቸጋሪ ግዝያትና የአደጋ ግዝያትን ለመቋወም እንችላለን፣ (ትርጉሙ ይቀጥላል)








All the contents on this site are copyrighted ©.