2013-01-28 13:42:31

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ለውህደት መጸለይ


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የዜናን ማኅተም ክፍል ተጠሪና የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ ከትላትና በስትያ የተጠናቀቀው የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት የጸሎት ሳምንት መርሃ ግብር መሠረት በማድረግ፦ “ጌታ ከእኛ የሚጠይቀው” (ምክያስ ነቢይ) ውህደት ነው ማለትም ፍትህ ምህረትን ማፍቀር በትህትና ከእግዚአብሔር ጋር መጓዝ ነው” የሚለውን በቅድሚያ በርእሰ አንቀጹ በማስፈር ቀጥለውም፣ “የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት የጸሎት ሳምንት ለውህደት ለሚደረገው ጥረት መሠረት መሆኑና ቲዮሎጎያዊና ባህላዊ ውይይት ፍቅር ያስከተለ ማኅበራዊ ጥረትም ነው” ብለዋል።
“እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ታህሳስ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. በታይዘ ማኅበርሰብ በተዘጋጀው የመላ ኤውሮጳ ወጣቶች 35ኛው የግኑኝነት ቀን ምክንያት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ወጣቶች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዙሪያ በመሰባሰብ፣ ቃለ እግዚአብሔር በማዳመጥ በአስተንትኖና መዝሙር እንዲም በጽሞና ጸሎት በመመራት ያሳዩት የተለያዩ ሃይማኖት ምእመናን ወጣቶች መንፍሳዊነት የተስተነተነ ክዋኔ ላይ ያተኮረ የውህደት መንፈሳዊነት የኖረ መሆኑ” ቅዱስ አባታችን የሰጡት ቃል አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማስታወስ፦ “ያ ግኑኝነት ልዩነት የተሞላው እንደሚሆንና በእውነት መደናገር ይታይበታል ላሉ ሁሉ እነዚያ ከተላያዩ አቢያተ ክርስቲያን የተወጣጡ ወጣቶች በክርስቶስ በተሰጠው መንፈስ በመመራት ወደ ክርስቶስ በጋራ ለመጓዝ ስመ ጥር ወንድም ሮዠር እንዳሉት፣ የታማኝ መንፈሳዊ ነጋዲ በምድር ነውና ሁሉም ለውህደት እንዲጸልይና ውህደት ተስፋው ያደርግ ዘንድ” ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ትጠራናለች በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.