2013-01-28 13:49:32

በቅድስት መሬት የሰላም ቀን፣ ብፁዕ አቡነ ትዋል፦ መንፈሳዊ ትብብር ወስኝ ነው ነው


RealAudioMP3 በቅድስት መሬት ሰላም እንዲሰፍ ሁሉ ይኸንን የጸሎት ሃሳብ በማድረግ አምስተኛው ዓለም አቀፍ ስለ ቅድስት መሬት የሰላም ቀን ትላንትና በተለያዩ 3 ሺሕ ከተሞች ተክብሮ መዋሉ ሲገለስጥ፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋል ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኤማኑኤውላ አፈጂ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “በዓለም አቀፍ ደረጃ በቅድስት መሬት ሰላም እንዲረጋገጥ የሚደረገው መንፈሳዊ ትብብርና ጸሎት ብርታት ነው። ሁሉም የቅድስት መሬት ክፍልና ዜጋ መሆኑ ሲመሰክር ማየቱ ስለ ቅድስት መሬት ሰላም የሚደረገው ጥረት ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊነትም ጭምር የሚያጠቃልል ነው። ስለዚህ የቅድስት መሬት ነዋሪና ዜጋ ሁሉ ይኽ ለሚቀርብለት ትብብርና ደጋፍ የተገባ እንዲሆን በሰላም ጥረት ቀዳሚ ሚና መጫወት ይኖርበታል። ይህ የጸሎት ቀን ለክርስቲያኖች አድነት ታልሞ ከሚደረገው የሳምንት ጸሎት መዝጊያ ጋር የሚገናኝ በመሆኑም ያለው ክብር ምንኛ የላቀ መሆኑ እንገነዘባለን። በጸሎት በማበር ስለ ውህደትና ስለ ቅድስት መሬት ሰላም ለመጸለይ የታየው ህብረት በአቢያተ ክርስቲያን ተጨባጭ ውህደት ያረጋግጥ ዘንድ የውህደት ጸጋ እንግዚአብሔርን እንለምነው” በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.