2013-01-21 15:17:37

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ ጸረ የጦር መሣሪያ


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ ጸረ የጦር መሣሪያ በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ እ.ኤ.አ የ2013 ዓ.ም. የሰላም መልእክት፦ “በዓለም ለወታደራዊ ጉዳይ የሚፈሰው ውጪ ማደግና እንዲሁም የጦር መሣሪያ ንግድ ቀውስ የማያውቀው እንዳውም እጅግ ከፍ እያለ መሆኑና ይኽ ደግሞ ሁሉም በቸልተኝነት የሚያየው መሰናክል ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። ስለዚህ ሁሉም ይኸንን ድርጊት በቸልተኝነት እንዳያየው” የሚል አደራ የተኖርበት መሆኑ አባ ሎምባርዲ መሠረት በማድረግ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በአመሪካ 300 ሚሊዮን ተናንሽ የጦር መሣሪያ ባለ ንብረት መሆኑና የጦር መሣሪያ ንግድና አጠቃቀሙንም ጭምር ለመቆጣጠር የደነገገው ሕግ በርግጥ ቅን እርምጃ ነው። በኒውታውን የተከሰተው ዘግናኙ የግድያ ተግባር ተመሳሳይ አደጋ ለማገድ ይህ የጸደቀው ሕግ በቂ ሳይሆን መልካም እርምጃ ነው። ስለዚህ የዚህ ዓይነት አእምሮ በሳተ ሰውም ይሁን በጥላቻ መንፈስ ተነቃቅቶ በሚፈጸመው የግድያ ተግባር ምክንያት በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት 47 የተለያዩ የኃይማኖት መሪዎች በአገሪቱ የጦር መሣሪያ ንግድ እንዲገታ የሚያግዝ ሕግ እንዲወጠን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለሕግ መወሰኛው የባላይ ምክር ቤት ጥሪ ማቅረባቸው አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ አስታውሰው፣ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች አነስተኛ የጦር መሣሪያ ንግድ ለራስ ደህንነት በሚል ዓላማ በስፋት የሚዘዋወርና ለንግድ የሚቀርብ ቢሆንም ቅሉ ለሞት አደጋ በማጋልጡ ጉዳይ ቀዳሚ ሥፍራ የያዘ ነው። ጸረ ሰብአዊ ፈንጆች ከዓለም ጨርሶ ለማስወገድ የተደረሰው የስምምነት ውሳኔ የተከተለ አደገኛ የጦር መሣሪያ መፍታት ውሳኔ ወሳኝ ነው። ይኽ ደግሞ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ንግድ ለማገድና የተለያዩ የወንጀል ቡድኖች የገቢ ምንጫቸውን ለማክሸፍ የሚያግዝ መሆኑ አስታውሰው፣ ሁሉም በሶሪያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው ቢልም ቅሉ አሁንም ወደ አገሪቱ የጦር መሣሪያ ሲገባ ይታያል። ሰላም ከልብ የሚመነጭ ነው። ሆኖም የጦር መሣሪያ ቅነሳ ለሰላም መንገድ የሚያግዝ ነው በማለት ያቀረቡትን ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.