2013-01-14 15:36:46

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 13/01/2013)
ወቅታዊው ኅብረተሰብ እግዚአብሔርን እንደ ገደብ እንጂ እንደ ፍቅር አይመለከተውም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ሲስቲና ጸሎት ቤት በላቲን ሥርዓት ለተከበረው በዓለ ጥምቀት ዘእግዚእነ ምክንያት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለ 20 ሕፃናት ምሥጢረ ጥምቀት ሰጥተው ባሰሙት ስብከት፣ የወቅቱ ኅብረተሰብ በኢየሱስ ማመን ጊዜው ያለፈበት እንደሆነ አድርጎ የሚመለከተው ተግባር መሆኑ ገልጠው፣ ሆኖም እምነት ለእግዚአብሔር እቅፍ ክፍት እንደሚያደርግ ማብራራታቸው ሲገልጥ፣ እኩለ ቀን ቅዱስነታቸው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት ስብከት ቀኑ ዓለም አቀፍ የስደተኞችና ተፈናቃዮች ዕለት የሚታሰብበት መሆኑ ዘክረው ስደተኛውና ተፈናቃዩ የእምነትና የተስፋ ነጋዲ በማለት ገልጠው፣ በዚህ ርእስ ሥር ቀኑን ምክንያት በማድረግ መልእክት ማስተላለፋቸውም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ባጠናቀሩት ዘገባ ማስታወሳቸው ለማወቅ ተችለዋል።
ቅዱስነታቸው ባሰሙት የጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ስብከት፦ “የወቅቱ ኅብረተሰብ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ነጻነት የሚገታ አድርጎ የሚያይና እንዲህ በመሆኑም ሰው ሙሉ በሙሉ ገዛ እራሱ እንዲሆን የሚገታ ተመስሎ የሚታየው እግዚአብሔር መወገድ አለበት የሚልና በዚህ እግዚአብሔር ማግለል በሚል ሁኔታ በመመራት የሚኖር ነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ በሚኖር ኅብረተሰብ ዘንድ እምነትን በግልጽና ካለ አስመሳይነትን ካለ ላድር ባይነት መንፈስ መኖር እጅግ ከባድ ነው” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሲስቲና ጸሎት ቤት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦“የወቅቱ ኅብረተሰብ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነታቸውን የሚያኖሩትን ማኅበርሰብ ከጊዜ ውጭ የሆኑ ከጊዜ ጋር የማይሄዱ ጊዜ ያለፈባቸው እድርጎ ያያቸዋል። ይኽ ዓይነቱ አስተሳሰብና አመለካከት ከእግዚአብሔር ጋር የሚጸናው ግኑኝነት ምን መሆኑ ፈጽሞ ካለ መገንዘብ የሚመነጭ መሆኑና በእምነት ጉዞ እጃችንን በመያዝ ቀድሞ የሚመራን መሆኑና በእምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እውነተኛው ምሉእ ሕይወት እርሱም ውህደት ከእግዚአብሔርና ለሌሎች ክፍት የሚያደርገን ነጻ የሚያወጣው የእግዚአብሔር ፍቅር ተግባር በእኛ ላይ ይፈጽማል” ብለዋል።
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት የሚያወሱ ወንጌላውያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ፈቃድና እቅድ በነጻነት በሙላት ለመኖር ገዛ እራሱን ለመላ ሰው ልጅ ሁሉም በሁሉም በመስቀል እስከ መሠዋት ድረስ ለአብ የሰው ልጅ የማፍቀር ፈቃድ ታዛዥ ለመሆን ምንኛ ዝቅ እንዳደረገ ያመለክታሉ፣ ጌታችን ሲጠመቅ፣ ሕያውና የሚሠራው መንፈስ ቅዱስ ይገለጣል፣ ምንም ኃጢአት ሳይኖርበት ከኃጢአተኞች አንዱ በመሆን እኛ ይኸንን የንስኃ ተግባር ምሥጢረ ጥምቀት በመቀበል በእኛ ላይ ይፈጸም ዘንድ እንዳደረገም ቅዱስነታችው ሲያስረዱ፦ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቅርበት ለመመስከር ከሁሉም ኃጢአተኞች ጎን እንድንሆንና ለእነርሱ ቅርብ እንድንሆን ይሻል። ይኽንን ደግሞ ለመለወጥ በምናደርገው ጉዞ ድካም ለእኛ ኣሳቢ በመሆን እራስ ወዳድነት እርግፍ እደርገን ለመተው ከኃጢአታችን ተለይተን ለመኖር የምንሻ ከሆን እርሱን በሕይወታችን ለመቀበል ፈቃደኞች ከሆን ከወደቅንበት ለማንሳትና ወደ እግዚአብሔር አብ መልኮት ይመራናል” ካሉ በኋላ አክለውም፦ የሕይወት ምንጭ በሆነው ሞቱ በመሳተፍ፣ በትንሣዌው ለመሳተፍ ዳግም ለአዲስ ሕይወት ለመወለድ በሞቱ ምሥጢር እንሰምጣለን። ምሥጢረ ጥምቀት የሚቀበሉት ሁሉ ዳግም የእግዚአብሔር አብ ልጆች በመሆን ዳግም በመወለድ በኢየሱስ የአብ ልጅ ግኑኝነት ተሳታፊዎች በመሆን በሙሉ ተስፋና እምነት እግዚአብሔርን አባባ ብለን የመጥራት ብቃትና የውሉድ መብት ተካፋዮች ያደርገናል” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
“ምሥጢረ ጥምቀት፦ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ማወቅ ያለው ደስታ፣ ለእርሱ እጆች በእምነት የተሰጠን መሆናችንና በፍቅር እቅፍ ውስጥ መኖራችን በጥልቀት የምናጣጥምበትና በተመሳሳይ መልኩም ልክ አንዲት እናት ልጅዋ ስትደግፍና ስታቅፍ ያለው የደስታ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ጸጋ ነው” እንዳሉ የገለጡት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አክለውም ቅዱስነታቸው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት አስተምህሮ፦ “ለሃያ ሕፃናት ጸጋ ምሥጢረ ጥምቀት መመሥራቴ ደስተኛ ነኝ። ለሁሉን ለተወለዱትና ለሚወለዱት ሕፃናት ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት በተለይ ደግሞ ሁሉም የተቀበለውን ምሥጢረ ጥምቀት በማስታወስ፣ ያ ምሥጢር ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ክፍት እንድንሆን ያደረገን መሆኑ እንድናስተወል አደራ እላለሁ” ማለታቸውንም አስታውቀዋል።
“በዚህ የእምነት ዓመት ከላይ ሰማይ እርሱም ከእግዚአብሔር ፍቅር የሆነውን እንደ ልጁ ለመኖር ዳግም ለመወለድ ያበቃንን የተቀብለውን ምሥጢረ ጥምቀት ያለው ክብር እንዳይዘነጋ አደራ” በማለት ከዚህ ጋር በማያያዝም እለቱ ዓለም አቀፍ የስደተኞችና የተፈናቃዮች ቀን የሚዘከርበት መሆኑ ገልጠው፦ “የበለጠና የተሻሻለ መጻኢ ተመኝቶ አገሩና ቤቱን ጥሎ የሚሰደደው ልክ እንደ አብርሃም ለመንገድ ብርሃን በመሆን በሚመራው እግዚአብሔር ታምኖ የሚፈጽመው ጉዞ ነው። በዚህ መልኩ ስደተኞች በዓለም የእምነትና የተስፋ አብሳሪዎች ናቸው” በማለት፣ ለሁሉም ስደተኞች በጸሎታውቸው እንደሚያስቡዋቸው በማረጋገጥ ሐዋርያዊ ቡራኬ ማስተላለፋቸው ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.