2013-01-11 15:18:23

ብፁዕ ካዲናል ሳንድሪ፦ ማኅበረ ክርስትያን በግብጽ የሚታይና የስኬታማ ወንጌል ኅላዌ ምስክር


RealAudioMP3 የምሥራቅ አቢያተ ክርስቲያን ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርዶ ሳንድሪ በግብጽ ሐዋርያዊ ዑደት እያካሄዱ መሆናቸው ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚዘከር ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው ከትላንትና በስትያ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ተጠሪዎች ጋር ተገናኝተው ባሰሙት ንግግር፦ “ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገልና በዚህ አገልግሎት ለመጠመድ ከመጋብያን ማለትም ከእረኞች ከካህናት ከገዳማውያን ጋር ታማኝና ገንቢ ውህደትና ትብብር መሠረት ለማገልገል በግብጽ የካቶሊካውያን ማኅበረሰብ ሕይወት በተግባርና በቃል የእግዚኣብሔር አንድያ ልጁን በቅዱሳት ሚሥጢራት በሚታነጽ ሕይወት በትምህርተ ክርስቶስ በፍቅር ሥራ በተለይ ደግሞ በትብብርና ደጋፍ ሕንጸት ቀን በቀን በተጨባጭ አገልግሎት አማካኝነት ለመመስከር ቤተ ክርስቲያናዊ ኃላፊነት የተቀበላችሁ እነሆኝ በማለት ዝግጁነታችሁ የለገሳችሁ ናችሁ” እንዳሉ ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ወቅታዊው የግብጽ ጠቅላይ ሁኔታ በማሰብም፦ “እጅግ አንገብጋቢና ፈታኝ ወቅት ነው። ይህ በረሃማው ወቅት አገሪቱ ባላት ሃይማኖታዊ ባህል፣ ባጠቃላይ ለእግዚአብሔር ግልጸት ክፍት በሆነው የግብጽ ባህል ሕንጸት አማካኝነት የሚታለፍ ነው። ወቅታዊውና መጻኢው ሕይወት በዚህ ባህል የተገነባ ነው። የግብጽ ማኅበረ ክርስቲያን በዚህ አንገብጋቢው ወቅት ለሚገናኙዋቸው ሁሉ ፍርያማ ሥፍራ በመሆን በእምነት ጸንቶ ወደ ክርስቶስ ወንጌል የሚመራ መሆን ይገባዋል። የካልኩታ እናቴ ብፅዕት ተረዛና ብፁዕ ቻርለስ ደ ፉኩልት…ጠቅሰው… “ልንከተላቸው የሚገባን አብነቶች ናቸው” ብለዋል።
ብፁዕ ካዲናል ሳንድሪ ባሰሙት ንግግር የእምነት ዓመት በግብጽ ሃይማኖታዊ ባህል በስፋት በሚታይባት አገር፣ የካቶሊክ የሕንጸት ማእከሎች፣ ለተሟላ የሰብአዊ ሕንጸት የመከባበር የመቀባበል የመተባበር መሣሪያ ነው። በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እነዚህ እሴቶች እንዳሉ በመመስከር ማስፋፋት ያለው አስፈላጊነት፣ ቤተ ክርስቲያን በመካከለኛው ምስራቅ የተሰየመው የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ምዕዳን በማስደገፍ ካብራሩ በኋላ፣ የእምነት ዓመት ዓላማው ምን መሆኑ ገልጠው፣ ለሁሉም ሐዋርያዊ ግብረ ኖሎው ተጠሪዎች የእምነት አመተ ዓላማ እንዲያጎሉ በአደራ በማለት፣ ወጣት ትውልድ በግብጽ ባጠቅላላ በመካከለኛው ምስራቅ መከባበር መተባበር መቀራረብ የሚቻል መሆኑ መስካርያን ሆነው እንዲገኙ የሰላም መሣሪያ ለመሆን እንዲታነጹ አደራ ብለዋል።
ብፁዕነታቸው ትላትና ጧት የንጽሕት ድንግል ማርያም የፍራንቸስካውያን የደናግል ልኡካን ማኅበር መሥራች እናቴ ብፅዕት ማሪያ ትሮያኒ የተወለዱበት 200ኛው ዓመት ምክንያት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ፣ ገዳማውያንና ልኡካነ ወንጌል በመካከለኛው ምስራቅ የቤተ ክርስትያን ሰላም እንዲረጋገጥ የምታከናውነው ጥረት እንዲመሰክሩ አደራ ካሉ በኋላ፣ በተለይ ደግሞ በሶሪያ በኢራቅ ዓመጽና ጥላቻ በሚታይባቸው አገሮች ሁሉ ሰላም እንዲረጋገጥ ቤተ ክርስቲያን የምታቀርበው የሰላም ጥሪ መስካሪያ እንዲሆኑ በማሳሰብ፣ ቤተ ክርስቲያን በመካከለኛው ምስራቅ የተሰየመው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለመካከለኛው ምስራቅ ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን በመጥቀስ የሰብአዊ መብትና ክብር የሰዎች እኩልነት ማነቃቃት ይጠበቅብናል ማለታቸውና በዚያኑ በትላንትናው ዕለት ከስዓት በኋላ ወደ ሻርም ኤል ሸይክ በመሄድ አዲስ የተገነባው እመ ሰላም ቤተ ክርስቲያንን መባረካቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.