2012-12-28 15:26:31

ራሻ፦ የሞክሶ ሊቀ ጳጳሳት፣ ሁሉን ለሚችል አግዚአብሔር ሕይወታችን እንዲያድስ እንፍቀድለት


በሞስኮ የእመ አምላክ ካቴድራል ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፓውሎ ፐዚ በላቲን ሥርዓት በተከበረው በዓለ ልደት ምክንያት ለሞስኮ ካቶሊካውያን ማኅበረሰብ ባስተላለፉት መልእክት፣ “የሚጠራችሁ ታማኝ ስለሆነ (1ተሰ. 5፣ 23-24) በሚል የቅዱስ ጳውሎስ ሓዋርያዊ መልእክት መሪ በማድረግ “እግዚአብሔር ሁሉን ያደረጋል፣ የሚለው ቃል ብሥራተ ገብሪኤል ለተበሳሪቷ እመ አምላክ ያብራራው ቃል፣ ምንም’ኳ በእምነታችን ስንደክም መታመን ሲሳነን፣ እግዚአብሔር አለ መታመናችን ሳያግደው ነጻነታችን በማክበር ይጠባበቀናል” እንዳሉ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ “ጅምሩ የእግዚአብሔር ነው እኛን ፍለጋ ወደ እኛ ይመጣል፣ በእምነት እንመልስለትም ዘንድ ይጠራናል፣ እግዚአብሔር ወደ ዓለም በመምጣት አዲስ ሰውን ቀሰቀሰ፣ አሁንም ጥሪው ይቀጥላል፣ እግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፣ የምንነጋገርበት እግዚአብሔር የአስተሳሰባችን የአእምሮአችን ውጤት ሳይሆን፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ሰው የሆነው የሕያዋን እግዚአብሔር ነው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
“ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ለማርያም ባበሰራት ቃል አማካኝነት የእግዚአብሔር በአዲስ ጎዳና ዳግም መምጣትና ለሰው ልጅ አዲስ የሕይወት ትርጉም ለመስጠት በእርሷ ማሕጸን እድሮ ሰው ሆኖ ቅርባችን ለመሆን እንደሚመጣ ገልጦ ሲያበቃ፣ ስለዚህ ሁሉም አዲስ ጅማሬ የመጀመሪያ ቃል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አለ መሆኑ ያረጋግጥልናል፣ እግዚአብሔር ዓለምንና በዓለም የሚታየው እርሱን አለ እግዚአብሔር መኖር የሚለው ተጋርጦ እንዲቀረፍ እንፍቀድለት፣ እግዚአብሔር በትስብእቱ ወደ ሰው ልጅ ታሪክ በመግባት ሰው በመሆኑ ወደ ሰው ከሰው ልጅ በላይ ቅርብ በመሆኑ የሰው ልጅ ጉዞ አድሷል” በማለት የበዓለ ልደት ትርጉም ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፦ “እግዚአብሔር በኢየሱስ ናዝራዊ አማካኝነት የሰውን ልጅና ታሪኩንም ጭምር በመቀበል፣ አዲስ ጅማሬ አረጋገጠ” ያሉትን ቃል ጠቅሰው፣ የሚያፈቅረን ታማኝ ነው ካሉ በኋላ ብፁዕነታችው ለሁሉም መልካም የሰላም የወንድማማችነት ፍቅር የሚጎላበት በዓለ ልደት ተመኝተው መልእክቱን እንዳጠቃለሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.