2012-12-26 16:19:29

የቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ዝክረ በዓል


ዛሬ በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ የቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ዝክረ በዓል በመሆኑ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ሁሌ በታላላቅ በዓላት እንደሚያደርጉት እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ነጋድያንና ከሮም ከተማ የተሰበሰቡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ይህንን አስተምህሮ አቅርበዋል፣
ውድ ወንዶሞችና እኅቶች፤ በየዓመቱ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ክብረ በዓል ነጋታው የዲያቆኑና የመጀመርያ ሰማዕት የሆነው የቅዱስ እስጢፋኖስ ክብረ በዓል ይዘከራል፣ የሐዋርያት ሥራ በ6ኛ 7ኛ ም ዕራፎቹ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋና መንፈስ ቅዱስ የሞላው ሰው እንደነብረ ይግልጥልናል፣ በዕለቱ በሚነበበው የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተከታዮቹ ስለሚያጋጥም ስደት “ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና” እንደነገረው ሁሉ አደገኛ ስደትና አስቸጋሪ ሁኔታዎች የማይቀር ነው ነገር ግን በዚሁ ጊዜ ጌታ ብቻቸው እንዳይተዋቸውና እንደሚከላከልላቸው “አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።” በማለት ይገልጠዋል፣ እንዲህ በመሆኑ ደግሞ ዲያቆኦን እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ሰርተዋል ተናግረዋል እስከ ወደር የሌለው መሥዋዕትነት በመክፈልም የክርስቶስ ፍቅር እየመሰከረ ሰማዕት ሆነዋል፣ ቀዳሜ ሰማዕቱ በዚሁ መሥዋዕትነት ያጋጠመው ሥቃይ ሙሉ በሙሉ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት ጋር ይጋጠማል፣ ሕማማቱም ልክ እንደሚደገም ዓይነት ሰፋ ባለ ትንተና አቅርቦታል፣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሕይወት በመላዋ በእግዚአብሔር እየተመራች የኖረችና የጌታ ሕማማት በእርሷ የተደገመ ከክርስቶስ ጋርም የተጋጠመች ነበረች፣ ሊሞት በተቃረበበት የመጨረሻ ደቂቃዎች ተንበርክኮ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሳለ የደገመኡን ጸሎት ይደግማል “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።” እንዲህ ሲሆን ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ ገዳዮቹን ይቅር እንዳለው ቅዱስ እስጢፋኖስም “ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ።” (የሐ ሥ 7፤59-60)
በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ዓይኖቹ በሞት ሊከደኑ እየታገሉ ወደ ሰማይ ትክ ብሎ ይመለከታል ስማዩ ተከፍቶ ኢየሱስንም የሁሉ ጌታ የሆነውና ሁልንም ወደ እርሱ በሚስብ በእግዚአብሔር አብ ቀን እጅ ተቀምጦ ያያል፣
በቅዱስ እስጢፋኖስ ክብረ በዓል ቀን እኛም ፊታችን ወደ ሰማይ ማቅናትና ዓይኖቻችንን ደግሞ በዚሁ ደስ የሚያሰኝ ዘመነ ልደት ምሥጢረ ሥጋዌው በምናሰላስለው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ እንድናተኵር እንጠራለን፣ በምሥጢረ ጥምቀትና ሜሮን እንዲሁም በቤተ ክርስትያን ምሥጢሮች የሚመገበው ክቡር እምነት፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢረ ጥቀ ቅዱስ ቍርባን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገዛ ራሱ ጋር አቈራኘን፣ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ደግሞ ሁሉንም የሚፈውስና ከፍ በማድረግ ዋጋ የሚሰጥና ወደ ፍጻሜ የሚያደርሰውን የድኅነት ተግባሩን ሊቀጥል ይፍልጋል፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ እንዳደረገው ክርስቶስ ወደ ገዛ ራሱ እንዲስብህ ራስክን ነጻ መተው ለሚጠራህ ብርሃን ሕይወትህን መተው ማለት ነው በዚህም ብርሃኑ ሕይወትህን አቅጣጫ አስይዞ መልካሙን ነገር ለመከተልና በእግዚአብሔር የፍቅር ዕቅድ የተሰጠውን የሰው ልጅ መንገድ መከተል ትችላለህ፣
ቅዱስ እስጢፋኖስ በአዲሱ ስብከተ ወንጌል ለማገልግል ቈርጠው ለተነሱ ሁሉ ምሳሌ ነው፣ እርሱ የሚያሳየው ስብከተ ወንጌል ምንም እንኳ ጠቃሚ ቢሆንም አዲስ ዘዴና ተክኒክ አንግቦ ወንጌል ለመስበክ መዘጋጀት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መምላታን በእርሱ እንድትመራ መፍቀድ ነው፣ የስብከተ ወንጌል ሕዳሴው በክርስቶስ ምሥጢር ምን ያህል እንደሰጠሙ ቃሉን ምን ያህል እንደቀሰሙት እንዲሁም በምሥጢረ ቍርባን ከሚገኘው ክርስቶስ ምን ያህል እንደተመገቡት ጠለቅ ባለ መንገድ አይቶ የሕያው ኢየሱስ እንደራሴ ሆኖ መናገርና መሥራትን ያመለክታል፣ አጠር ባለ አነጋገር ሰባኤ ወንጌሉ ክርስቶስን ወደ ሌሎች የሚያደርሰው ምን ያህል ከክርስቶስና ከወንጌሉ ጋር እንደኖረ በሕይወቱ በሚመስክረው ነው፣ በዚሁ የእምነት ዓመት ቤተ ክርስትያናችን እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ያሉ እምነትና ብርታት በሞላው መንገድ ለጌታ ኢየሱስ ሊመሰክሩ የሚችሉ ወንዶችና ሴቶች እንዲበዙባት እመቤታችን ድንግል ማርያምን እንለምን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.