2012-12-17 15:02:37

ኡጋንዳ፣ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ ከግሉ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጋር ተገናኙ


RealAudioMP3 የአሕዛብ ስብከተ ወንጌል ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ ዝክረ 100ኛው ዓመት አስፍሆተ ወንጌል በኡጋንዳ ምክንያት በዚያች አገር ሐዋርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸው ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚዘከር ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው በጉሉ ሰበካ ከዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጋር በመገናኘት ለተማሪዎቹ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ “ምን ዓይነት ካህን ለመሆን እሻለሁ? ክርስቶስን የሚመሰክር ታማኝ ጽኑ እምነት ያለው የሚያፈቅር ይኸንን በቃልና በሕይወት የሚኖር ካህን ለመሆን እሻለሁ ወይ? በተሰኙት ጥያቄዎች ላይ በማተኮር፣ በዚህ ዝክረ 50 ዓመት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እየተረጋገጠባት ባለቸው ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ውስጥ ምን ዓይነት ካህናት መሆን ይጠበቅብናል፣ የብዙ የእምነት ሠማዕታት ደም የፈሰሰበተ እምነት አቅቦ በመኖር ለመመስከር ዝግጁ ነኝ? ቤተ ክርስትያን በእኔ ትተማመንም ዘንድ ብቃቱ አለኝ ታማኝስ ነኝ ወይ? በዚህ 20ኛው ክፍለ ዘመን ክርስቶስን በተአዛዞ በንጽሕና በድኽነት ለመኖር ዝግጁ ነኝ፣ ቤተ ክርስትያን የሚያጸናው የሚገነባው የክርስቶስ ልብ አለኝ ወይ? የርእሱ መንገድ ለመከተል ዝግጁ ነኝ? መልሱ በግል ከእያንዳንዱ የዘርአ ክህነት ተማሪ የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው። ስለዚህ ክርስቶስን ለማወቅ እና እርሱን ለማበሰረ ከእርሱ ጋር መሆንን መማር ያስፈልጋል፣ ለሙሉ ሕይወቴ ካህን ብየ መልስ ለምሰጠትና ቤተ ክርስትያን ውሳኔውን ትቀበለውም ዘንድ ይኸንን ጥሪ የምመረምርበት ጊዜ ወሳኝና እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ስለዚህ የማዘጋጃ ዓመታት በቀልድ እንዳይታለፍ አደራ” እንዳሉ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት፣ አለ ጸላይ ሕይወትና ከክርስቶስ ጋር ካለ መገናኘት የሚኖር የዘርአ ክህነትና የክህነት ሕይወት የለም በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የአፍሪካ ቃለ መሓላ የተሰየመው በአፍሪካ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በለገሱት የድህረ ሲኖድስ ሓዋርያዊ ምዕዳን የዘረዘሩትን ለክህነት ሕይወት አስፈላጊው መንገድ ጠቅሰው ያሰሙት ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.