2012-12-14 13:50:52

ቻይና
ብፁዕ አቡነ ሳቪዮ ሆን፦ በቅድስት መንበር እውቅና የሌለው የቻይና ብፁዓን ጳጳሳት ማኅበር ሢሜተ ጵጵስና ውድቅ የማድረግ ሥልጣን የለውም


RealAudioMP3 በቻይና የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ማኅበር ተብሎ የሚታወቀውና እንዲሁም የቻይና አገር ወዳድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስታይን ማኅበር በቅድስት መንበር ውሳኔ መሠረት ለብፁዕ አቡን ታደዎ ማ ዳቂን የተሰጠው ሢመተ ጵጵስና ውድቅ እንዲሆንና ብፁዕ አቡነ ታደዎ ማ ዳቂን ሢሜተ ጵጵስናውን እንዳይቀበሉ የማዘዝ ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው ነው። የቅድስት መንበር ውሳኔ በማንም ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እምቢ የሚባል የሚሻር አይደለም። በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሢሜተ ጵጵስና የመሻሩም ሆነ የማንሣቱ የመሰየሙም ኃላፊነት በአዲት አገር የምትገኘው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሥልጣን አይደለም፣ ይባስም በቅድስት መንበር እውቅና የሌለው የቻይና ካቶሊካውያን ብፁዓን ጳጳሳት ማኅበር ሥልጣን እንዳልሆነ የአህዛብ ስብከተ ወንጌል ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሳቪዮ ሆን ታይ ፋኢ በማብራራት ስለዚህ ብፁዕ አቡነ ዳቂን ሻንጋይ በሚገኘው ከረዳት ጳጳስ ሐዋርያዊ መንበራቸን አይነሱም እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ብፁዕ አቡነ ዳቂን ለቅድስት መንበር ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና ለቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታማኝ መሆናቸውና አገራቸውንም እንደሚያፈቅሩ በመግለጥ ለቅድስት መንበር ትእዛዝ ተገዥ መሆናቸው ካለ ምንም ማመነታት በተግባር አረጋግጠዋል። ስለዚህ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ማኅበር ውሳኔ፣ ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን፣ ውሳኔውም የቅድስት መንበር ውሳኔ የሚከተል ባለ መሆኑም በተለያዩ አገሮች የሚገኙት ካቶሊካውትያን ምእመናን ቅድስት መንበርን በመደገፍ ድምጻቸውን እያሰሙ ናቸው። በዚህ የእምነት ዓመት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አንድነት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥር የሚገለጥ በመሆኑ፣ ሁሉም ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስትያን ይኽ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተኣዝዞ እንዲኖሩ ሁሉም ይኸንን ሃሳብ ማእከል በማድረግ እንዲጸልይ አደራ ማለታቸውንም ፊደስ የዜና አገልግሎ ተስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.