2012-12-12 13:56:48

የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የቫቲካን ረዲዮ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ አቢያተ ክርስትያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ የተመራ የሚያቀርበው ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላትና፦ በክርስትና ታሪክ ጅማሬ አስፍሆተ ወንጌል በጽሑፍ ሳይሆን በቃል መተላለፉ የተንገረው የድህነት ታሪክ ቆይቶ በጽሑፍ ጭምር የሚተላለፍ ሆኖ፣ የሁለት ሺሕ ዓመታት ዕድሜ ያለው ታሪክ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት-ባህል ብላ በመግለጥ በዚህ ርእስ ሥር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ሰፊ ትንተና እንደሰጠበት ገልጠው፣ ክርስትያን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክና ስብእና ላይ የሚኖሩት ተአምኖተ ሃይማኖት “የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን እንዲያውቁ ነው። (1ጢሞ. 2,4)” የሚል ቃል የሚተገብር መሆኑ አባ ኮዋልዝይክ አስረድተው፣ ሰለዚህ ‘የኢየሱስ ታሪክ ለሁሉም ዘመን ሰው መተላለፍ መቅረብ መሰበክ አለበት” ብለዋል።
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ወንጌል የተስተጋባው በሁለት መልኩ መሆኑ ሲገልጥ፦ “በቅድሚያ በቃል ቀጥሎ በጽሑፍ”፣ ይኽም “በስብከተ ሐዋርያት” ቀጥሎም “በአስተንፎ መንፈስ ቅዱስ ቅዋሜው የተረጋገጠው ቅዱስ መጽሐፍ አማካኝነት” መሆኑ እንረዳለን፣ “መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም የላቀ የበላይነት ያለው የእምነት መግለጫ ነው” ብለዋል።
የሐዋርያት ስብከተ በዘመናት ውስጥ በብፁዓን ጳጳሳት በተባባሪዎቻቸው አማካኝነት ቀጣይነቱ መረጋገጡ አባ ኮዋልዝይክ ሲያረዱ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁጥር 78፦ “ምንም’ኳ የቅርብ ትስስር ቢኖረውም ከምጽሐፍ ቅዱስ ለየት ያለው ይህ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚሆነው ሕያው ውርስ ትውፊት ተብሎ ይጠራል፣ በትውፊት አማካይነት ‘ቤተ ክርስቲያን በአስተምህሮዋ በሕይወቷና በአምልኮዋ ምንነቷንና እምነቷን ሁሉ ጠብቃ ለእያንዳንዱ ትውልድ ታስተላልፋለች’።” የሚለውን ጠቅሰው ካስረዱ በኋላ፦ “እያንዳዱ ንኡስ እያንዳንዱ የእያንዳንዱ ዘመን ባህል (ትውፊት) የዚያ አቢይ ትውፊት ክፍል ነው።” የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቍ. 83፦ “ሐዋርያዊ ትውፊትና ቤተ ክርስቲያናዊ ሥርዓቶች’ በሚል ርእስ ሥር፣ ‘ትውፊት(ቶች) በቤተ ክርስትያን ሥልጣን አማካኝነት ሊሻሻል ወይም ሊቀየር የሚቻል ነው” የሚለውን ጠቅሰው የተለያዩ ባህሎች (ትውፊቶች)፣ ሥርዓተ አምልኮዎች ለእምነታችን ድጋፍ እንጂ ያንን ቅዱስ ሐዋርያዊ ትዊፍት የሚያፍን የሚያደበዝዝ አይደለም ስለዚህ አቢይ ጥንቃቄ የሚያሻው ትምህርት ነው በማለት የሰጡት አስተምህሮ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.