2012-12-10 15:16:07

ኮንጎ፦ በሰሜናዊ ኪቩ ሰላም እንዲረጋገጥ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ አቀረቡ


RealAudioMP3 የደሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ አገራዊ አንድነትና እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 1960 ዓ.ም. ከቅኝ ግዛት ነጻ መውጣት በኋላ ተያይዞ የተረጋገጠው ድንበራዊ ክልል ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እውቅና የሰጠው ሉኣላዊነት መከላከልና ማክበር ለአገሪቱ ሰላም ወሳኝ መሆኑ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት የሰላም ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ብፁዓን ጳጳሳት በአገሪቱ ሰሜናዊ ኪቪ ክልል ያለው ሁኔታ ላይ በማተኮር ኤም 23 በመባል ከሚጠራው ታጣቂ ሃይሎች ጋር መንግሥት የጀመረው የሰላም ድርድር የአገሪቱ ሉአላዊነት የማይነካ መሆን እንዳለበት በማሳሰብ በተለይ ደግሞ በኡጋንዳ ርእሰ ከተማ የተጀመረው የሰላም ድርድር አጥጋቢ ውጤት እንዲኖረው የአገርና የሕዝብ ጥቅም የሚያስቀድም መሆን እንደሚገባው ማሳሰባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኮንጎ ያለው ተልእኮ ዳግም በመመልከት የሰላም አስከባሪው ኃይል የኮንጎ ሰላማዊ ሕዝብ ደህንነት ዋስትና ለማሰጠት ያለው ብቃት ከፍ እንዲያደርግ በማለት ጥሪ በማቅረብ ለጎማ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ተዮፊለ ካቦይ ትብብርና ደጋፍም እንዳስተጋቡ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.