2012-12-10 15:09:06

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “እግዚአብሔር በጽሞና ይናገራል ሰውን ከኀጢአት ነጻ ያወጣል”


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. ታሕሳስ 8 ቀን በተከበረው በዓለ ጽንሰታ ለማርያም ምክንያት እንደተለመደው የጽንሰታ ለማርያም ሐወልት ወደ ሚገኝበት ሮማ አደባባይ ስፓኛ በመሄድ ሥርዓተ አምልኮ ፈጽመው እዛው ለተገኘው በብዙ ሺሕ ለሚገመተው ከውስጥና ከውጭ ለመጣው ምእመናን ሰላምታን በማቅረብ፣ “እግዚአብሔር በጽሞና ይናገራል፣ በጸጋውም ሰውን ከኀጢአትና ከራስ ወዳድነት ነጻ በማውጣት እውነተኛውን ደስታ ለመኖር እንዲችል ይደግፋል” በሚል ሐሳብ ላይ በማተኮር ባሰሙት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፣ ለበዓለ ጽንሰታ ለማያም የተነበበው ወንጌል ዋቢ በማድረግ፣ “የእግዚአብሔር መለኮታዊ ልኡክና በማርያም መካከል በተደረገው ግኑኝነት አማካኝነት እግዚአብሔር ሰው ሆነ። በመለኮታዊ ልኡክና በማርያም መካከል ስለ ተካሄደው ግኑኝነት ወይንም ውይይት ብዙ አይባልም፣ ብዙውን ጊዜ በቸልታም የሚታለፍ ሁነት ነው። ይኽ ሁነት በዚህ ባለንበት ዘመን ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ብዙ ባልተናገረበት ነበር፣ በጽሞና የሚከሰት ምሥጢር በመሆኑም የመገናኛ ብዙኃን ምንም ባልተናገሩበት” ካሉ በኋላ የእግዚአብሔር ድምጽ ጋጋታ ቅስቀሳ ወይንም ቀንደኛ ተወናያንነት የሚል ሳይሆን፦ “የእግዚአብሔር ንቁነት ቆም እንድንል እንድንረጋጋ በጽሞና የሚያሰማው ድምጹን ለማዳማጥ እንዲቻልም የሚያነቃቃ ነው” ያሉት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አያይዘውም ማርያም እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ገዛ እራስዋ ክፍት ያደረገች መሆንዋ ሲያስረዱ፦ “የማርያም ልብ በትልቁ የእግዚአብሔር ልብ ላይ ያተኮረ፣ የራስ ወዳድነት አዝማሚያ የሌለው ፍጹም መግባባት የሠፈነበት ነው።” በማለት እግዚአብሔር ገዛ እራሱን “በትሁትነት መንፈስ የኤኮኖሚ የፖለቲካ ኃይሎች የሚያንጸባርቅ ሳይሆን ግብረ ገባዊና መንፈሳዊ ኃይሎች በጥልቀት ወደ ሚጎላበት ሥፍራ ዝቅ በማድረግ በዚህ መንፈስም ማርያምን በእግዚአብሔር ገዛ እራስ ዝቅ በማድረግ መንፈስን ተግባር እንድትተባበርና ከእግዚአብሔር ተግባር ጋር ተወሃዳለች” እንዳሉ ያመለከተው የቅድስት መንበር መግለጫ አያይዞ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም የሚያሳስበን ሰውን የማዳን እቅድ የሰው ልጅ ተግባር ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሚመጣ እንደሆነ የሚያስገነዝበን የሚያረጋግጥልን፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ከክፋት መንፈስ በላይ እጅግ ብርቱ ራስ ወዳድነት በተለያዩ ጸረ ሰብአዊ ምርጫዎች የሚፈጥረው የሰውን ልጅ ወደ ከፋ መቅ የሚያስገባው ባዶነት በሞምላት፦ ማርያም የምታስተምረን፣ ሰው ምንም’ኳ በከፋ መቅ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ቅሉ ለእግዚአብሔር ሩቅ እንዳልሆነና እግዚአብሔር ገዛ እራሱን የሰው ልጅ ወደ ገባበት ጥልቅ መቅ ወርዶ ከእግዚአብሔር ውጭ ካዘገመው ከሰው ልብ ጋር በመገናኘት ሕይወት ውብ መልካም ጥልቅ ትርጉም ያለው በኢሰብአዊነት አዘቅት ላይ የሚገኝ ቢሆንም፣ ያለው ትርጉምና ውበቱ አቢይ መሆኑ ነው” በማለት፣ “የክርስትና የኃሴት ብሥራት እርሱም ጸጋ በኀጢአት ላይ፣ ሕይወት በሞት ላይ ድል መንሣቱ የሚያረጋግጥ ነው። ጽንሰታ ለማርያም የሚያረጋግጥልን እውነትም ነው። ስለዚህ ለራስ ወዳድነት እምቢ ለእውነተኛው ፍቅር እሺ እንድንል የሚያነቃቃን፣ ጸጋ የተሞላሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ይኽ በጸጋ መሞላት የማርያም ደስታ በእርሷ ዘንድ የኀጢአት ምልክት አለ መኖሩ ያረጋግጥልና። ስለዚህ እራስንና ሌሎችን ከሚጎዳው ከራስ ወዳድነት ከኀጢአት የተለየን እንድንሆን የሚያነቃቃ ዓቢይ በዓል ነው” በማለት ጽንሰታ ለማርያም ትርጉሙን ገልጠው ያሰሙትን አስተምህሮ እንዳጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.