2012-12-07 14:30:23

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 አዲስ የመገናኛ ብዙኃን ሥልት ተጠቃሚ
አዳዲስ የዕደ ጥበብ መሣሪያዎች ለአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. እፊታችን ታህሳስ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንፃ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የማኅበራዊ የመገናኛ ድረ ገጾች ውስጥ በሆነው አንዱ እርሱም Twitter-ትዊተር በመባል የሚታወቀው ድረ ገጽ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በይፋ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ይኸው የቅዱስ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በትዊተር የማኅበራዊ የመገናኛ ድረ ገጽ የግላል እጦማር አድራሻቸው በይፋ በተከፈተበት ዕለት 700 ሺሕ ተከታዮች መመዝገባቸውም ለማወቅ ተችለዋል።
የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ስለ ጉዳዩ ከቫቲካን ጋዜጠኛ ፊሊፓ ሂትቸን ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አንዳመለከቱት፣ በትዊተር የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሦስት ቀናት ውስጥ 700 ሺሕ ተከታዮች ካስመዘገበ በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በዓለ ልደት ዘእግዚእነ ለማክበር በቀረው የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከታዮቹ ብዛት ወደ አንድ ሚሊዮን ከፍ እንደሚል ይገመታል ካሉ በኋላ በርግጥ ቅዱስ አባታችን የኵላዊት ቤተ ክርስትያን እረኛ ናቸው ስለዚህ እውቅና ለማግኘት ሳይሆን ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ጥሪ መሠረት ከሁሉም ጋር አለ ምንም ገደብ ለመገናኘት የሚያስችላቸው እንጂ እንደ ማንኛው ኮከብ ታዋቂ ዜጋ የሚሳተፉበት አይደለም። በትዊተር ተከታዮች ካሉዋቸው ከያንያን ጋር የሚነጻጸር አይደለም። ስለዚህ በዚህ በምንኖርበት ዓለምና ለእያንዳንዱ ዜጋ ቅርብ ለመሆን ካላቸው ፍላጎት አንጻር የተደረሰ ውሳኔ ነው። በቅርቡ ቅዱስ አባታችን የመንፈሳዊነት ምድረ በዳ መስፋፋት አሳሳቢ መሆኑ ገልጠዋል እንደነበር የሚታወስ ነው። ከዚህ አኳያ ቅዱስነታቸው በትዊተር በኩል ከሁሉም ጋር ለመገናኘትና በእምነት ለማጽናት ያላቸው ፍላጎት የሚያረጋግጥ ውሳኔ ነው ብለዋል።
በትዊተር አድራሻቸው በኩል ለሚቀርብባቸው ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡበት ነው። ሆኖም መዘንጋት የሌለበት ነገር ቢኖር አወንታዊ አሉታዊና ዘላፊ ትዊት መኖሩ ነው። ስለዚህ የተለያዩ መልእክቶች ሊገኝበት ይችላል፣ የሚያስፈራም አይደለም፣ እስካሁን ድረስ ስለ መከራ ስቃይ ችግር ላይ ያተኮረ መልእክት እየደረሰ ነው። በርግጥ በትዊተር በኩል የቤተ ክርስትያን ችግር ይፈታል ማለት ሳይሆን፣ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተጠቃሚው ለመደገፍ ከቤተ ክርስትያን ርቆ ለሚገኘው ቅርብ በመሆን ለማወያየትና ለመደገፍ የሚያግዝ አገልግሎት መሆኑ አብራርተዋል።
ሰብአዊ ፍጡር እግዚአብሔር የናፈቀው ፍጡር ነው። የሕይወት የመኖር ትርጉም ለመለየት ተስኖት በሰመመን እይኖረ ነው። ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃሉ ሸክማችሁ የከበደባችሁ እናንተ ደካሞች ሁሉ ወደ እኔ ኑ! እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ” (ማቴ. 11,25) ሲል የተናገረው እውነት የሚያንጸባርቅ ውሳኔ ነው። የዘመኑ ሰው መኖር ደክሞት የኅልውና ጥያቄ አስበርግጎት ከገዛ እራሱ ተገሎ ለመኖር ወይንም ከዚህ ጥልቅ ጥያቄ የሚያስተጓጉለው ልምዶችን በመከተል ሲዋትት ይታያል። እንዲህ በመሆኑም ለዚህ ሕዝብ በሚገኝበት ሥፍራ ሁሉ ቀርቦ ማነጽ የቅድስት ቤተ ክርስትያን ኃላፊነት ነው። ስለዚህ በዚህ የሕይወት ጎዳና ሕዝቦች የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አጽናኝና ደጋፊ እንዲሁም የሚያንጽ ቃል እንዲያገኝ ማድረግ ጥበብ መሆኑ አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.