2012-12-05 14:20:01

የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የካቶሊክ ትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህረተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የቫቲካን ረዲዮ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ ቤተ ክርስትያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ ተመርቶ የሚቀረበው ተከታታይ ሥርጭት በመቀጠል ትላትና የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ሥር፦ “የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግልጸትና የግል ግልጸቶች” በሚል ሃሳብ ላይ በማተኮር ባቀረቡት ተከታታይ አስተምህሮ እንዳመለከቱት፦ አዲስ የእግዚአብሔር ግልጸት አይኖርም የለም፣ ይኽ ደግሞ የእግዚአብሔር መገለጥ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት እንዲሁም የመጨረሻው ደቀ መዛሙርት ከዚህ ዓልም በሞት መለየት በኋላ መጠቃለሉ” ገልጠው“የክርስትና የእምነት እውነት ነው። የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በዚህ ማእከላዊ የክርስትና እምነት እውነት ሥር ሰፊና ጥልቅ አስተምህሮ ያቀርባል” ብለዋል።
የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ክፍል አንድ ሥር ምዕራፍ ሁለት አንቀጽ አንድ “የእግዚአብሔር መገለጥ” በሚል ርእስ ሥር “ኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂና የመገለጥ ሁሉ ምልአት፣ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በቃሉ ተናግረዋል፣ ሌላ ምንም ተጨማሪ መገለጥ እንደማይኖር በማረጋገጥም፣ ቍ. 66 ‘ስለዚህ ክርስትያናዊ መርሕ አዲሱና እርግጠኛው ቃል ኪዳን በመሆኑ ምንጊዜም አያልፍን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ክብር እንደገና ከሚገለጥበት ዘመን በፊት ምንም አይነት አዲስ ይፋዊ መገለጥ ይኖራል ተብሎ አይገመትም’ የሚለውን ቅዉም ሃሳብ የቅዱስ ዮሐንስ ዘመስቀል፦ ‘እግዚአብሔርን የሚጠራጠር ወይንም አንድ ዓይነት ራእይ ወይም መገለጽ እንዲሆንለት የሚሻ ማንኛውም ሰው ዓይኖቹን በሙሉ በክርስቶስ ላይ ባለማድረጉና አዲስ ለሆነ ነገር በምኞት ኑሮ በመዋተቱ ብቻ ሳይሆን እርሱን በማስቀየሙ ጥፋተኛ ነው’” በማለት በሰጠው አስተምህሮ መሠረት በማብራራት አረጋግጦልናል ብለዋል።
ቤተ ክርስትያን ግልጸት በመጨረሻው ደቀ መዝሙር ከዚህ ዓለም በሞት መለየት በኋላ ተደምድመዋል በማለት እንደምታስተምር አባ ክዋልዝይክ ባቀረቡት አስተምህሮ አስታውሰው፣ ሆኖም ግን የተደነገጉ የማይለወጡና በጥያቄ ውስጥ የማይገቡ የእምነት ዶግማዎች እንዳሉ ገልጠው፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቍ. 66፦ “መገለጡ የተፈጸመ ቢሆንም ገና ሙሉ በሙሉ ግልጽ አልሆነም’ በማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስብእና ግልጸት በሙላት ተጠናቀዋል፣ ሆኖም ቤተ ክርስትያን በመንፈስ ቅዱስ ተመርታ ምሉእ እውነት ለማወቅ እንዲቻል ትመራለች (ዮሐ. ምዕ. 16 ቍ. 13 ተመልከት) የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ 66 ‘የክርስትና እምነት በመጪዎቹ ምዕተ ዓመታት ደረጃ በደረጃ ራሱን በምልአት እውን ያደርጋል’ በማለት በሰጠው አስተምህሮ አረጋግጦታል” ብለዋል።
ይኽንን መሠረት በማድረግ “ግላዊ ግልጸቶች” ተብለው የሚገለጡት በቤተ ክርስትያን እውቅና ያገኙት ለምሳሌ “የሉርድና የፋጢማ ግልጸተ ማርያም” ጠቅሰው ካስረዱ በኋላ፣ የዚህ የግልጽ ትርጉምና ሚና በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቍ. 67 ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ‘ግላዊ’ በመባል የሚታወቁ እንዳንዶቹም በቤተ ክርስትያን ሥልጣን (በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ) እውቅና ያገኙ ራዕዮች ነበሩ፣…እነዚህ ራዕዮች ወይንም መገለጦች ‘በክርስቶስ ሁነኛ ምሉእ መገለጥ፣ የማሻሻልም ሆነ የፈጻሚነት ሚና የላቸውም…ስለዚህ የክርስቶስ ወሳኝና ሁነተኛው ምሉእ ግልጸት በሙላት ለመኖርና በተወሰነ የታሪክ ዘመን የሚከሰቱ ናቸው” በማለት እንደሚገልጠውም አብራርተው፣ “ግላዊ ግልጸት ለምእመናን እምነት ትእዛዛዊና ግዴታዊ መቀብል የሚል አይደለም፣ እምነት የግል ግልጸት በግድ ወይንም በትእዛዝ በቀበልን አይጠይቅም” ብለዋል።
“ምእመናን የተለያዩ የግል ግልጸቶችን በመቀበል በሞቆ ስሜት ሲከተሉትና ሲያስተጋቡት ይታያል፣ እግዚአብሔር በቅዱስ መጽሐፍ በትውፊት በቤተ ክርስትያን ሥልጣን አምካኝነት ገዛ እራሱን ያስተዋውቃል፣ ይገልጣል” ካሉ በኋላ “በዚህ የእምነት ዓመት ሌላ አዲስ ግልጸት የማንጠብቅ መሆናችን ታምነን የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ እንድናነብ” በማሳሰብ ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.