2012-12-03 15:14:06

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “መጠባበቅና ተስፋ ማድረግ”


RealAudioMP3 ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ “መጠባበቅና ተስፋ ማኖር” በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፦ በላቲን ሥርዓት የተገባው ወደ በዓለ ልደት ዘእግዚእነ የሚያሸጋግረው የምጽአት ወቅት ላይ በማትኮር የምጽአቱ ዘመን የመጠባበቅና በተስፋ መመልከት የሚል መሆኑ ገልጠው፣ የአማኞች ማኅበረሰብና የኅብረተሰብ አባላት እንደመሆናችን መጠን፣ በዚህ ዓለም የተለያዩ ችግሮች ተካፋዮች፣ በሚታየው ችግር ውጥረት ሁሉ ውጭ ሆኖ አይመለከተኝም የሚል ማንም ሰው የለም። ዓለም አቀፍ የኤክኖሚ ቀውስ፣ ሥራ አጥነት የመሳሰሉት የብዙ ሰዎችን በተለይ ደግሞ የወጣቱ ትውልድ መጻኢ ጨለምተኛ አስመስሎት እንደሚገኝ ገልጠው፣ ማኅበራዊና የጤና ጥበቃ ጉዳይ የሚመለከቱ ችግሮች በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አመጽ፣ ሕዝቦችን ለሞት አደጋ የሚያጋልጡ በሽታዎች ግጭቶች በጠቅላላ ተስፋን የሚያጨልም ተጋርጦ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች ይታያል። በሶሪያ በማሊ በናይጀሪያ በዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ በሶማሊያ፣ በአፍጋኒስታንና በኢራቅ በግብጽ ያለው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ውጥረት የመሳሰሉትን እንደ አብነት ጠቅሰው፣ አንገብጋቢ ጥያቄዎች በጭንቀትና በሃሳብ መዋጥ የመሳሰሉ ችግሮች የከበበን ይመስላል። ይህ የምጽአት ዘመን ለምናቀርባቸው መሠረታውያን ጥያቄዎች ምላሽ የምናገኝበት ኮሳሳ ተስፋ በማግለል እውነተኛ የሆነው ተስፋችን የምንለይበት ወቅት ነው። ሁሉም በተቀበለው በተለያየ ኃላፊነትና በሚኖረው ጥሪ አማካኝነት ወደ እውነተኛው ተስፋ እንዲያመራ መተባበርና መደጋገፍ እንዲረጋገጥ ሁሉም የሰላም መሣሪያ እንዲሆን ማነቃቃት ይጠበቅበታል ካሉ በኋላ፣ ይህ የመጽአት ዘመን የጸሎትና የተቀበልነው ኃላፊነትና ጥሪ በሙላት ለመኖር እንድንችል ቁርጥ ፈቃድ በማኖር የምናገለግልበት ወቅት ነው በማለት ያቀረቡትን የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.