2012-11-26 14:18:42

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. 24/11/2012)
የእግዚአብሔር የፍቅር መንግሥት ግንባታ የማይቋረጥ ነውና በታሪክ ክስተቶች አትደናገጡ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት ዓመታዊ የክርስቶስ ንጉሥ በዓል ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በብዙ ሹሕ የሚገመቱት ምእመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁ፣ እንደተለመደው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከውጭና ከውስጥ የተወጣጡ በብዙ ሺ የሚገመቱ ምእመናንና መንፈሳዊ ነጋድያን በተገኙበት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ የክርስቶስ መንግሥት እንዲስፋፋና ብሎም በሁሉም ሥፍራ ጅማሬው ይረጋገጥም ዘንድ ለቤተ ክርስትያን የተሰጠ ሐዋርያዊ ኃላፊነት ነው በሚለው ሃሳብ ላይ ያተኮረ አስተምህሮ በማቅረብ፣ “ለወንጌላዊነት በመለወጥ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ እንዲስፋፋ ሊገለገል ሳይሆን ለማገልገልና እውነትን ለመመስከር የመጣው ክርስቶስ ንጉሥ የሁሉም አማኞች ልብ የሚነካ ነው” ካሉ በኋላ፦ “ሁሉም ባለፈው ቅዳሜ የካርዲናልነት ማእርግ ለተሰጣቸው 6 አዲስ ብፁዓን ካርዲናላት መንፈስ ቅዱስ በእምነትና በፍቅር የጸኑ እንዲሆኑ ጸጋውን እንዲያበዛላቸውና በዚህ መሠረትም የተሰጣቸው አዲሱ ኃላፊነት ለክርስቶስና ለመንግሥቱ መስፋፋት ዳግም በጽናት ለዚህ ጥሪ ለመኖር እንዲችሉ ስለ እነርሱ እንዲጸለይ አደራ እላለሁኝ” ብለዋል።
ቅድስት ድንግል ማርያም ለመላ ቤተ ክርስትያንና ለመላ ምእመናን ከለላ ትሆንም ዘንድ ሲጸልዩ፦ “የአሁኑ ጊዜ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ተስፋ ላይ በጸና መንፈስ ለመኖር እንዲቻል፣ በዚህ እጅግ አስቸጋሪ በሆነው ታሪክ የሚኖር ቢሆንም ቅሉ እግዚአብሔር የፍቅር መንግሥቱ ከመገንባት ወደ ኋላ እንደማይል ቅድስት ድንግል ማርያም ‘መንግሥትህ ትምጣ’ በማለት ወደ ሰማያዊ ቤት የሚያቀርብ ቃልና ተግባር ለመፈጸም እንድንተጋ ትደግፈን” ብለዋል።
በመጨረሻም ቅዱስነታቸው፣ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የተፈጸሙት ዓበይት ክንዋኔዎች የሆኑትን በተለይ ደግሞ በኤኳዶር ቅዱስት ቤተ ክስትያን ብፅዕና ላወጀችላቸው እናቴ ማሪያ ትሮንካቲን “መላ ሕይወታቸውን ለወንጌልና ለሰውብአዊ ሕንጸት አገልግሎት ያዋሉ’ በማለት አስታውሰው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ከመናብርተ ጥበብ ተማሪዎች ጋር የእምነት ዓመት ምክንያት በማድረግ አንደኛ ጸሎተ ሠርክ እንደሚመሩ ከወዲሁ ካስታወሱ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው፦ “ክርስቶስ ልባችንን ይለውጥ ዘንድ እንፍቀድለት፣ የሰው ልጅ ታላቅነት ተቀባይና ቸር ከሆነው ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ከመሆን የሚገኝ ነውና። ከእርሱ ጋር እንሁን። ጌታችን መላውን የሰውን ዘር ወደ ሰላሙ ይምራ” በማለት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ለሁሉም መልካም የክርስቶስ ንጉስ በዓል ተመኝተው ወደ መጡበት ሸኝተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.