2012-11-19 14:46:59

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለአዲሱ የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ መልእክት አስተላለፉ
“አቢያተ ክርስትያን አንድ እንዲሆኑ”


እ.ኤ.አ. ባለፈው መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ ሸኑዳ ሦስተኛን እንዲተኩ በግብጽ የበሀሪያ ረዳት ጳጳስ ባለ ስልሳ ዓመት ዕድሜ ብፁዕ አቡነ ታዋድሮስ መመረጣቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ብፁዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ 118ኛው የግብጽ RealAudioMP3 ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ከድኅረ ሙባራክ ቀዳሜ ፓትሪያርክ እ.ኤ.አ. ህዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም. የተቀበሉት ሐዋርያዊ ኃላፊነት በይፋ ተልእኮው ለመጀመር በካይሮ ቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መረከባቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተካሄደው የሥሜተ ፓትሪያርክ በዓል ኩላዊት ቤተ ክርስትያንን ወክለው በተሳተፉት የአቢያተ ክርስትያን አድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ በኩል ለአዲስ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ተዋድሮስ ሁለተኛ ባስተላለፉት የደስታ መገልጫ መልእክት፦ ቅዱስ አባታችን “አዲሱ ፓትሪያርክ በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸውና ሁሉም አቢያተ ክርስትያን አንድ እንዲሆኑ ለሚደረገው ጥረት በጋራ ለመተባበር ያላቸው ፍላጎት በማደስ፣ ለአድነትና ለውህደት የሚደረገው ጥረት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነትም እንዲጎላ እንደሚጸልዩ በማረጋገጥ። ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር በተትረፈረፈ ጸጋ እንዲባርካቸውና በዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎትም እንዲሸኛቸው ለቤተ ክርስትያናቸው ለሁሉም የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስታያን ምእመናንና ውሉደ ክህነት በሚሰጡት ሐዋርያዊ አገልግሎት እግዚአብሔር እንዲመራቸው ተማጽነው ረዥም እድሜ ለአዲሱ ፓትሪያርክና ለግብጽ ሰላምና ብልጽግናን እመኛለሁኝ” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“ሁሉም የክርስቶስ ተከታዮች ያ በክርስቶስ ቀድሞ የተፈለገውና ጽሎት የተደረገበት አንድነት በፍቅርና በእርቅ አማካኝነት በኵላዊት ቤተ ክርስትያንና በኦርቶዶካዊት ቤተ ክርስትያን መካከል እንዲረጋገጥ ተመኝተው በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጸሎት ሃሳብ እንዲሆን አደራ” ካሉ በኋላ “የጋራው ውይይት በሥነ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ በቲዮሎጊያ ጭምር የሚከናወን እንዲሆንና፣ ወንጌላዊው ድህነት እውነተኛው መልእክት በዓለም ፊት በጋራና በውህደት እንዲመሰከር” አሳስበው፣ ለአዲስ ፓትሪያርክ “ወንድማዊ ቅርበትና ወዳጅነት በመግለጥ እግዚአብሔር በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው እንዲባርካቸው የእግዚአብሔር ቡራኬ እማጠናለሁኝ” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.