2012-11-12 14:37:50

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ አንድ አባትና አንዲት እናት


ሁሌ በሳምት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “አንድ አባትና አንዲት እናት” በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፣ በአለማችን አንድ አባትና አንዲት አናት አለኝ ለማለት የማይደፍር የሚወለዱ RealAudioMP3 የሕፃናት ብዛት ቁጥር ከፍ እያለ እንደሚሄድ ገልጠው፣ እነዚህ ሕፃናት በደረሰው የኅብረተሰብ ክፍል ውሳኔና የአኗኗር ሥልት መሠረት አንድ አባትና አንዲት እናት የሚለው የቤተሰብ ባህርያዊ መልኩ ለመኖር የተሳናቸው ሆነው ለማደግ እየተገደዱ ናቸው ብለዋል።
አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በቅርቡ የስፐይን የሕግ መንግሥት አስከባሪው የበላይ ፍርድ ቤት አንዳዊ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል ጋብቻ የሚፈቅደው ሕግ እንዲሰረዝ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ጠቀስ የቀረበው ክስ መሠረት የሌለው ነው በማለት በበኩሉም የእገሪቱ ሕገ መንግሥት የሴትና የወንድ ልዩነት የለም የሚለው ፆታዊ እኩልነት የሚለውን አንቀጽ በመጥቀስ፣ በአንዳዊ ፆታ መካከል ጋብቻ የተፈቀደና ሕገ መንግሥት አይጻረርም በማለት የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ጭምር የተለያዩ ግዛቶች በአንዳዊ ፆታ የጋብቻ ሕጋዊነት የሚስማሙበት መሆናቸው እየሰጡት ያለው አስተያየት፣ የፈረንሳይ መንግሥት ያለው ተመሳሳይ ንድፈ ሕግ አስታውሰው፣ በምዕራቡ ዓለም ባህርያዊ የቤተሰብ መሠረትና ቤተሰባዊ ባህል ራእይ የሚጻረር በጠቅላላ ባህርዩን የሚቀይር አመለካከት በመዛመት ላይ መሆኑም አባ ሎምባርዲ አብራርተው፣ በእውነቱ ይኽ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚለው ጋብቻና በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል በሚጸናው ጥላ ሥር የሚወለደው ቤተሰብአዊ ሕይወት የሚያገል ብቻ ሳይሆን፣ ይኽ አይነት ራእይ የውሁዳን ለማድረግ የሚቃጣው ያለው ጥልቅና ልዑል ሕጋዊነት ተቀባይነቱ ለማዳከም ያቀና አደናጋሪ አዲስ ጎጂ ባህል ነው ብለዋል።
ይኽ አይይነቱ አዲስ አመለካከት የሕዝብ ፍላጎት ነው ወይ? አገር እንዲመራ የሚመረጠው የፖለቲካ አካል የገዛ እራስ ውሳኔ የሁሉም ውሳኔ እንደሆነ አድርጎ በተመርጫለሁ ሽፋን የሚያጸድቀው ሕግ የአገርና የመላ ሕዝብ ጥቅም መሠረት ያደረገ ነው ወይ? የተሰኙትን ጥያቄዎች በርእሰ ዓነቀጹ በማቅረብ፣ የፍረንሳይ መንግሥት ያቀረበው ንድፈ ሕግ በፈረንሳይ ያለችው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብቻ የምትቃወመው ሳይሆን በፈረንሳይ የአይሁድ ሃይማኖት አቢይ መምህር ጭምር የተቃወሙት ቅድመ ሕገ ንድፍ ነው። በእውነቱ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚጸናው ውህደት ከዚህ ውህደት የሚወለደው ሕፃን ያጠቃለለው ቤተሰብ እየተዳከመ እርሱም አንዳዊ ፆታ መሠረት የሚፈጠረው ጋብቻ ምክንያት ሕፃናት አንድ አባትና አንዲት እናት እንዲኖራቸው የሚለው መሆናዊ መብት የሚጥስ ነው። በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚጸናው ጋብቻ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን የተጨበጠ ወይንም የተደረሰ ባህላዊ ሥልጣኔ ነው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.