2012-11-07 14:17:17

የቅዱስ አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለትክክለኛው ሊጡርጊያ አከባበር ደጋፊ ሕጋዊና ሥርዓተ አምልኮአዊ ደንቦች አመልካች ውሳኔ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ሓምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተገቢ ሓዋርያዊ ሥልጣን አነሳሽነት ለተገባ ወይንም ለትክክለኛ ሊጡርጊያዊ አከባበር ሕጋዊና ሥርዓተ አምልኮአዊ ደንቦችን የሚያመለክት ቅድመ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የነበረ የሊጡርጊያ ሥርዓት በተመለከተ፣ ከዚህ የአምልኮ ሥርዓት ጋር ትሥሥር ላላቸው ዓለማውያን ምእመናን መልስ ለመስጠት አቅደው በይፋ ለሁሉም RealAudioMP3 ያስተላለፉት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ገቢራዊ የሆነው የውሳኔ ሐዋርያዊ መልእክት ዝክረ አምስተኛው ዓመት ምክንያት ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላንትናው ኅትመቱ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ ያንን በቤተ ክርስትያን ጸላይ ሕይወትና እምነት ውስጥ የተወለደው እጅግ ሃብታም የሆነውን ሮማዊው የቅድሴ ሥርዓተ አምልኮ (መጽሓፈ ቅዳሴ) ያለው ክብርና ቅድስናውን በሙላት አቅቦ ተገቢ ቦታ እንዲሰጠው የሚያሳስብ መሆኑ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ የታወጀውና የተጀመረው የእምነት አመትና ቅድስት ቤተ ክርስትያን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት እያከበረችበት ባለበችበት በአሁኑ ወቅት፦ “አለማውያን ምእመናን አለ ምንም መከፋፈል አንድነታቸውን አቅበው እምነታቸውን በመግለጥ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዋና ተወናያን እንዲሆኑ አደራ እላለሁኝ” በማለት እ.ኤ.አ. ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም. Una cum Papa nostro- ውሁደ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር” በሚል ዓለማ መሠረት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔዎችን እንዲከበር ወይንም እንዲጠበቅ በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የሚያገለግሉትን የሚያቅፈው Coetus internationalis Summorum Pontificum የተሰየመው ዓለም አቀፍ ማኅበር ባዘጋጀው መርሃ ግብር መሠረት ለመንፈሳዊ ንግደት ሮማ ተገኝተው ለነበሩት ምእመናን ያስተላለፉት መልእክት፣ ለነጋድያኑ የቅዱሳት ምሥጢራትና ሥርዓተ አምልኮ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ካኛዛረስ ዮቨራ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ መነበቡ የገለጠው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አክሎ መሥዋዕተ ቅዳሴው እ.ኤ.አ. በ 1962 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ያጸደቁት በሮማ የቅዳሴ መጽሐፍ መሠረት መፈጸሙም ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.