2012-11-02 14:27:08

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የእግዚአብሔር ብርኃን ጨለማንና መደናገርን ያሸንፋል


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 31 ቀን 1512 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ጁሊዮ ዳግማዊ በላቲን ሥርዓት መሠረት የሁሉም ቅዱሳን ክብረ በዓል ዋዜማ በመሩት ጸሎተ ዘ ሰርክ ተመርቆ የተከፈተው በአገረ ቫቲካን የሚገኘው በሥነ ቅብ፣ ንድፍ ቅርጻ ቅርጽና የሥነ ሐወልት ሊቅ ሚከላንጀሎ በሚያስደንቀው ሙያዊ ጥበብ አማካኝነት ያስዋበው ቤተ ጸሎት RealAudioMP3 ሲስቲና ዝክረ 500ኛው ዓመት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ በዓለም ልዩ ውብ እጅግ ተደናቂ በሆነው ቤተ ጸሎት ተገኝተው ጸሎተ ዘ ሰርክ መርተው፦ “የእግዚአብሔር ብርሃን ጨለማንና መዛባትን የሚያሸንፍ ነው” በማለት በዚያ የዛሬ 500 ዓመት በፊት ሚከላንጀሎ እ.ኤ.አ. በ 1508 ጀምሮ 1512 ዓ.ም. ሥራውን በማጠናቀቅ ለቅድስት ቤተ ክርስትያን ያስረከበው እጹብ ድንቅ ቤተ መዘክር ካፐላ ሲስቲና-ቤተ ጸሎት ሲስቲና 5 ዘመን ቢያስቆጥርም ግርማውና ውበቱ ታቅቦ ላለንበት ዘመን የተላለፈው መሆኑ ጸሎተ ዘ ሰክር መርተው ባሰሙት ሥልጣናዊ መልእክት የገለጡት ቅዱስ አባታችን አክለውም፦ “የዚህ በሥነ ጥበብ እጹብ ድንቅ የጥበብ ሥራ የተዋበው ቤተ ጸሎት ብርሃን በዘፍጥረትና በድኅነት አማካኝነት ሕይወት ለመስጠት ድቅድቅ ጨለማን ና ትርምስ ላይ ድል የሚነሳው የእግዚኣብሔር ብርሃን የሚያበስር ነው። ቤተ ጸሎት ሲስቲና የዚያ ብርሃን ታሪክ እርሱም የድህነት እግዚአብሔር ከሰው ዘር ጋር ያለው ግኑኝነት የሚተርክ ቅዱስ ሥፍራ ነው” እንዳሉ በጸሎቱ ሥነ ሥርዓት የተሳተፉት የምረቃ በዓሉን የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
ታላቁ የሥነ ቅብ ሥነ ቅርጻ ቅርጽና ሐወልት ሥነ ንድፍ ሊቅ ሚከላንጀሎ የካፐላ ሲስቲን ማአክላዊ ገጹ የእዚአብሔር ፈጣሪነት ታሪክ የእርሱ ያንን ጨለማን መደናገር መዛበትና ትርምስ ላይ ድል የሚነሣው ተግባርና ኃይል ነጻ ፍቅር ከመሆኑ የሚመነጨው ፍጹምነት የሚተርክ ታሪክ በቅብና በንድፍ ሲስቀምጥ፦ “በእግዚአብሔር ጣትና በሰው ልጅ ጣት መካከል ያለው ግኑኝነት (መነካካት) በምድርና በሰማይ መካከል የጸናው ግኑኝነት እግዚአብሔር በአዳም አማክኝነት ከፍጥረቱ ጋር በአዲስ ግኑኝነት በማቅረብ በቀጥታ ከእርሱ ጋር እንዲገናኝ በማድረግ በእርሱ አርአያና አምሳያ የተፈጠረ በመሆኑ ለዚህ ክብር በእርሱ (በእግዚአብሔር) መጠራቱ ያብራራል”። ካሉ በኋላ፣ ካፐላ (ቤተ ጸሎት) ሲስቲና በባህርዩ ቤተ ሊጡርጊያ መሆኑና በውስጡ የተኖሩት ቅቦችና ንድፎች ይኸንን ሊጡርጊያዊ ባህርይ የሚያንጸባርቅ የሊጡርጊያ ምህዳር መሆኑ ሲያመልክቱ፦ “በዚህ ውብ ቅዱስ ሥፍራ ተገኝቶ የሊጡርጊያ ሥርዓት መፈጸም በሥነ ውበት ሥነ ፍጥረት መካከል ያለውን እንዲሁም በሥነ ጥበብ ሊቅ ዘንድ ያለው ሥነ ጥበባዊ ማስተዋል አማካኝነት የሚገለጠው የግብረአዊ ውሁድ ጥዑም ቅኝት ስሜትንና መንፈስን የሚያጣምር ሥራ በሚያጎላው ሥፍራ የሊጡርጊያ ሥርዓት ሲፈጸም የሚኖር ስሜትና መንፈስ ነው” ብለዋል።
በካፐላ ሲስቲና ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ጎን በመሆን የሚጓዝ የሚሸኝ መሆኑ ያለው እርግጠኝነት ይኖራል፦ “ከእግዚአብሔር ፈጣሪ ቃል ጋር የሚጸናው ግኑኝነት የሚጎላበት ውብ ሥፍራ ነው” በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ መልእክት እንዳጠቃለሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.