2012-10-28 18:55:02

አዲሱ ስብከተ ወንጌል የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ልጅ ነው፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ጥዋት በቅ.ጴጥሮስ ባዚሊካ ስለ አዲሱ ስብከተ ወንጌል ለመወያየት ከሶስት ሳምንታት በፊት የጀመረው 13ኛ መደበኛ አጠቃላይ የጳጳሳት ሲኖዶስ መደምደምያ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል፣ ከቅዱስነታቸው ጋር ሁላቸው የሲኖዶስ አባቶች አብረው በኁባሬ ቀድሰዋል፣ ቅዱስነታቸው በስብከታቸው የእምነት ብርሃን ለሰው ልጅ ሕይወት ክቡር ሃብት ነው ሲሉ በማሳሰብ ይህንን ክቡር ሃብት የሆነው የእምነት ብርሃን ለሁሉም እንዲዳተስ ቤተ ክርስትያን ስብከተ ወንጌል የማካሄድ ግዳጅ እንዳላትና የሰው ልጆች ሁላቸው ይህንን ብርሃን የማወቅ መብት እንዳላቸው አሳስበዋል እንዲሁም በእኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት አስተምህሮም በካሪብያን የአመሪካ ክፍል በሱናሚ እየተቸገሩ ያሉትንና በደቡብ ጣልያን አገር በመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቀሉት በጸሎት ቅርበታቸውን ገልጠዋል፣
በሲኖዶስ መዝጊያው ቅዳሴ በተደረገው የም እመናን ጸሎት ስለ መካከለኛው ምስራቅ በተለይም በሲርያ ሰላም እንዲነግሥ በአረበኛ ቋንቋ ስለ ሰላም ጸሎት ቀርበዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ዛሬ 30ኛው መደበኛ እሁድ ሆኖ ለዕለቱ የሚነበበው ወንጌል ከማርቆስ ወንጌል ሆኖ ስለ ዕውሩ ባርቲሞስ ወይም የቲሞስ ልጅ ነው፣ ባርቲሞስ ጌታ በመንገድ ሲያልፍ በሰማ ግዜ “የዳዊት ልጅ ማረኝ ብርሃን ስጠኝ” እያለ ሲጮህና ሌሎች ዝም ሊያሰኙት ቢሞክሩም ጌታ ሰምቶት ጥሩት በማለት አስጠርቶት ምን ላድርግልህ ትፈልጋለህ ብሎ ሲጠይቀው “ራቡኑ መምህር ሆይ እንደገና ለማየት እፈልጋለሁ” ሲል በጠየቀው ጊዜ ኢየሱስም “ሂድ! እምነትህ አዳነችህ ብሎ ያሰናብተዋል፣
ቅዱስነታቸውም ይህንን ሁኔታ ከዛሬው ትውልድ ጋር በማያያዝ “ተስፋቢስና የሕይወት ትርጉም ላጠፋው ለዛሬው ትውልድ ከባርቲሞስ ምሳሌ ሌላ ምሳሌ ሊሰጥ አይቻልም ምክንያቱም ዕውሩ ባርቲሞስ የማየት ብርሃን ብቻ አይደለም ጠፍቶት የነበረ የእምነት ብርሃንም ጭምር ጠፍቶት ነበርና ለዚህም በጌታ ኢየሱስ በመተማመን ይጮሃል ብርሃንም ያገኛል” ሲሉ አሳስበዋል፣
“ባርቲሞስ እውነትን ጥርት ባለ መንገድ ለማወቅና በሕይወት እንዲጓዝ የእግዚአብሔር ብርሃን የሆነውን የእምነት ብርሃን የሚፈልግ ሰውን ያመለክታል፣ እኛም ከሁሉ አስቀድመን ዕውሮች መሆናችንን ለማወቅ ይህ ብርሃን ያስፈልገናል አለበለዚያ ለዘለዓለም ዕውሮች ሆነን እንቀራለን” ባቲሞስ ግን ዕውር ብቻ አልነበረም ታላቅ ሃብት ያጠፋ ለማኝም ነበር፣ የባርቲሞስ ሁኔት ለእኛ የሚያስተምረን ነገር ያለ እንደሆነ እኛም የገንዘብና የንብረት ብቻ ያልሆኑ ለሕወታችን አስፈላጊ የሆኑ ክቡር ሃብቶች እንዳሉን መለስ ብለን ልናሰላስል ይጠራናል፣ የባርቲሞስ ሁኔታ በጥንታዊ ስብከተ ወንጌል ያሉ ወገኖችን ሊያስታውሰን ይችላል፣ በእነዚህ ሰዎች የእምነት ብርሃን በመድከሙ ከእግዚአብሔር ርቀው ይገኛሉ፣ ይህ ብርሃን ለሕይወታቸው እምብዛም የሚያስፈልግ ሆኖ አይታያቸውም፣ እነኚህ ሰዎች ግን ክቡር ሃብት አጥፈተዋል፣ ይህ ሃብት የገንዘብና የዚህ ዓለም ክብር ሳይሆን ያ ክርስትያናዊ ሃብት ነው፣ እነኚህ ሰዎች ሳይረዳቸው እርግጠኛና ጽኑ የሆነውን የሕይወት አቅጣጫን አጥፍተው የሕይወት ትርጉም ድሆች በመሆን እንደ ባርቲሞስ እመንገድ ላይ ተቀምጠው የዚሁ ከእጆቻቸው ያጠፉት ክቡር ሃብት ለማኞች ሆነዋል፣ እነኚህ ሰዎች ዛሬ የአዲስ ስብከተ ወንጌል አስፈላጊነት ያላቸው ናቸው፣ አዲሱ ስብከተ ወንጌል የመላዋ ቤተ ክርስትያን ሁኔታ ይመለከታል፣ በዛሬው ዕለት በዚሁ መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚደመደመው ሲኖዶስ ሶስት መሠረታውያን ነገሮች እንደሚያስፈልጉ ገልጠዋል፣ አንደኛው የምሥጢራት አስፈላጊነትና ለቅድስና ጥሪ ማቅረብ ማለትም አዲሱ ስብከተ ወንጌልን የሚያካሄዱ ዋና አካላት ቅዱሳን እንደሆኑና እነርሱ በሚሰጡት የሕይወት ምሳሌና በሚያደርጉት የፍቅር ምግባረ ሠናይ ሁሉም ሊረዳው በሚችለው ቋንቋ ለሁላችን ይናገራሉ፣ ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ አዲሱ ስብከተ ወንጌል የአሕዛብ ስብከተ ወንጌል ከሚለው የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነድ ጋር መተሳሰር እንዳለበት ነው፤ ይህም በታደሰ የስብከተ ወንጌል ተል እኮ መሆን እንዳለበትና እተግባር ላይ የሚያውሉት ደግሞ የሐዋርያዊ ግብረ ተል እኮ ሰዎችና ዓለማውያን ምእመናን መሆናቸውን ይጠቅሳል፣ “ሁላቸው ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስንና ወንጌሉን የማወቅ መብት አላቸው፣ ይህም ሁላቸው ክርስትያን ካህናት ገዳማውያንና ም እመናን የምሥራች ዜና የሆነውን ወንጌልን የመስበክ ግዳጅ እንዳላቸው ያሳስባል፣
በመጨረሻም ሲኖዶሱ የሚያቀርብልን ሶስተኛ ነጥብ ደግሞ ቤተ ክርስትያን ልዩ ትኵረት መስጠት ያለባት ተጠምቀው ስለሃይማኖት ደንታ የሌላቸው ሰዎችን እንደገና የእምነት ደስታን እስኪያገኙ ድረስ አበርትታ መስራት እንዳለባት ነው፣
“ቤተ ክርስትያን በተለያዩ የዓለም ባህሎች በማትኰር ከእነዚህ ጋር የሚጓዙና የሚግባቡ አዳዲስ መላዎችና ቋንቋዎች በመጠቀም ፍቅር በሆነ እግዚአብሔር ላይ የተመሰረቱትን የክርስቶስ እውነተኛ ትምህርቶችን በውይይትና በጓደኝነት መንፈስ ለሁሉም ማቅረብ አለባት፣
ቅዱስነታቸው በስብከታቸው መደምደምያ ላይ የሰጡት ማሳሰቢያ የአዲሱ ስብከተ ወንጌል ተል እኮ የሚፈጽሙ ለስብከት ከመነሣት በፊት ጌታ ኢየሱስን በማግኘት ልባቸው በደስታ የተሞላ መሆን አለበት ብለዋል፣ ቅዱስ ቀለሜንጦስ ዘአለክሳንድርያን በመጥቀስ ደግሞ እውነተኛውን አምላክ ለማሰላሰል የእውነት ጠላት የሆነውን ድንቁርናን መደምሰስ ያስፈልጋል” ብለዋል፣
በመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮም የሲኖዶሱ አጋጣሚ ታላቅ የቤተ ክርስትያን ኅበረት ግዜ መሆኑንና በዚህም ባለነው ዘመን ከድካሞቻችንና ከተስፋዎቻችን ጋር የዚች ቤተ ክርስትያን አባላት መሆን ምንና ያህል ደስ እንደሚያሰኛ አጣጥመናል፣ ለዚህች ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ መታደስም በዓለማውነት መንፈስ ለተወረረው ኅብረተሰባችንም ወንጌልን በታደውሰ መንፈስ የመስበክ ኃላፊነት እንዳላት በማመልከት ቅዱስነታቸውም በበኩላቸው የሲኖዶስ አባቶች ያቀርብዋቸውን ማሳሰቢያዎች አጥንተው ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ም ዕዳናቸውን እንደሚሰጡ ገልጠዋል፣
በመጨርሻም የዛሬ 50 ዓመት የተደረገውን ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በማስታወስ ያኔ የተሰጡን መምርያዎች እንደገና በመመልከት በዚሁ የእምነት ዓመት ሁላችን እንድታደስና እንደ ባርቲሞስ የእምነት ብርሃንችንን እንደገና እንድናገኝ እንዲሆን ያላቸውን መልካም ምኞት በመግለጥ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.