2012-10-12 14:17:48

ሲኖዶስ፦ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ


ትላትና የእምነት ዓመት መክፈቻ፣ ዝክረ 50ኛው ዓመት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መክፈቻ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ከተሳተፉትና አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የክርስትና እምነት ለማስፋፋት በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ባለው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ በታዛቢነት በመሳተፍ ላይ ከሚገኙት የሌሎች አቢያተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች ውስጥ አንዱ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ሮዋን ዊሊያምስ መሆናቸው ሲገለጥ።
ትላንትና በሮማ ሰዓት አቆታጠር ልክ ከምሽቱ 6 ሰዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተገኙበት በሲኖዶስ አዳራሽ ሊቀ ጳጳሳት ሮዋን ዊሊያምስ ንግግር ማስደመጣቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛቤላ ፒሮ አያይዘውም፣ ሊቀ ጳጳሳት ሮዋን ዊሊያምስ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን እይታ በሚል ርእስ ሥር ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አቢይ ቃል ኪዳን እርሱም ቤተ ክርስትያን ባህልዋና መዋቅርዋ በመለየት ጥያቄ በማቅረብ ገዛ እራሷ እጅግ ለተወሳበው ዓለም ለማቅረብ ለማስተዋወቅ ቃል ኪዳን የተገባበት አቢይ ጸጋ መሆኑ አብራርተው፣ ወንጌላዊ ትጉ ስሜት የተነቃቃበት ዳግም እውን የሆነበት ጉባኤ ለቤተ ክርስትያን ኅዳሴና ቤተ ክርስትያን በዓለም ታማኝነትዋ ያጠናከረ ጉባኤ ነበር እንዳሉ አስታውቀዋል።
“የክርስትያናዊ ሥነ ሰብእ ኅዳሴ ያነቃቃ ይኽ ደግሞ ወንጌል ማወጅ፦ እውነተኛ ሰው መሆን እርሱም በኢየሱስ ሰብአዊነት አርአያና አምሳያ የተፈጠረ መሆኑ ግንዛቤ ያሰጠ ነው፣ ስለዚህ የካቶሊክ እምነት በጠቅላላ የክርስትናው እምነት እውነተኛ ሰብአዊነት ነው። እግዚአብሔርንና ባለንጀራህን መመልከት ገዛ እራስ መመልከት ማለት መሆኑና ይኽ ደግሞ በቁጠባውና በሥነ ኤኮኖሚ ሂደት ግኑኝነትና ማንነትን መግለጥ ብሎ ለሚያምነውና በመደናገር ከእውነት እየራቀ ላለው ዓለም መልስ ነው” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ፍትህና ፍቅር የክርስትና ምስል መግለጫ መሆናቸው የታይዘ ማኅበርሰብ፣ የቅዱስ ኤጂዲዮ ካቶሊካዊ ማኅበር የአፍቅሮተ ዘ ቤት ማኅበር፣ ሱታፌና አርነት ማኅበር ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለታዊ ኑሮ ኃያውነቱን በመመስከር የሚሰጡት አስተዋጽኦ” ጠቅሰው፦ “አስፍሆተ ወንግል ከገዛ እራስ የሚጀምርና በመንፈስ ቅዱስ ለሚመራው ወደ ክርስቶስና በክርስቶስ ማደጉን በሳል በማድረግ ለሌሎችን ለመማረክ የውህደት ሱታፌ የሚሰጠው ደስታ ለማስተጋባት ለሚለውጥ እምነት ዳግመ ግኝት ማለት ነው” ካሉ በኋላ አክለውም፦ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ለውህደት ታልሞ የሚከናወነው የጋራው ግኑኝነት ማእከል በማድረግ፦ “በክርስትያኖች መካከል መራራቅ ሲኖር በመለያየቱ ሲጸኑ ክርስትና ያለው ሰባአዊነት ለመመስከርና ለማሳመን ገዛ እራሳቸው እንቅፋት ሆነው ሊመሰክሩት የሚገባቸው ሰብአዊነትን ያዳክማሉ፣ ስለዚህ አስፍሆተ ወንጌል በቅድሚያ ለገዛ እራስ ከሚለው ውሳኔ መጀመር አለበት” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክ ጋዜጠኛ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
“ማኅበረ ክርስትያን እምነታቸው በአንቀጸ እምነት በመታነጽና በአንቀጸ እምነት ላይ ያላቸው ግንዛቤ ከፍ እንዲል በማድረግ ቀናተኛ አማኞች በመሆን ስለ እምነታቸው ለሚቀርብላቸው ጥያቄ አለ መደናገጥና ፍርሃት በቂ መልስ ለመስጠት የሚችሉ ሆነው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው” አብራርተው፣ “በሃይማኖት ምክንያት ለሚከሰተው ስደትና መከራ ሃይማኖት የአመጽ መሣሪያ ሆኖ በሚታይበት ወቅት ሃይማኖት የሰላም እንጂ የአመጽ መሣሪያ እንዳልሆነ በመመስከር ተቃውሞ የማሰማትና የማውገዝ ብርታት ሊኖራቸው ያስፈልጋል” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አመለከቱ።







All the contents on this site are copyrighted ©.