2012-10-03 14:18:03

ብፁዕ አቡነ ቶማሲ፦ የዓይነ ሥውራን መብትና ክብር ጥበቃ ዋስትና የሚያሰጥ አዲስ ደንብ አስፈላጊነቱ


ጀነቭ በሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብትና ክብር የሚከታተለው ድርጅት ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ ዓለም አቀፍ የምሁራን የጥናት ምርምር ግኝቶች ይዞታዎችና የምሁራን ግኝት የመብትና ጥበቃ ሕጋዊ ሁኔታ የሚከታተለው ድርጅት እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. RealAudioMP3 እያካሄደው ባለው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ “የዓይነ ሥውራን መብትና ክብር ጥበቃ ዋስትና የሚያሰጥ አዲስ ደንብ አስፈላጊነቱ” ላይ ያነጣጠረ ንግግር ማሰማታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ እንዳመለከተው፣ በተለያዩ አገሮች ህዳሴና የፈጠራ ክህሎት ለማበረታታትና እ.ኤ.አ. ሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. በፐኪንግ የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ የፈረመበት የስምምነት ሰነድ ያለው አስተዋጽኦ እርሱም የድምጸ-ዕይታ ከያንያንና የሥነ ጥበብ ባለ ሙያዎች ያላቸውን ክህሎት ለጥቅም ማዋል የሚቻልበት መንገድ የሚያነቃቃ መሆኑ አብራርተው፣ “የፐኪንግ የስምምነቱ ውል የዓይነ ሥውራን ክህሎት በመንከባከብ ለማበረታታት ያላቸውን ክህሎት ይዞታና የሚያስገኘው ውጤት የመብት ጥበቃ በሕግና በደንብ መዋስ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታተሙት መጻሕፍቶች ውስጥ 5 መቶኛው ብቻ የዓይነ ሥውራ መብትና ክብር የሚጠብቁ መሆኑ ጠቅሰው፣ በድኾች አገሮች 1% ብቻ እንደሆነም አመልክተው፣ ዓለማችን በተለያየ የዕደ ጥበብ ግኝትና ምርምር እጅግ በበለጸገበት በአሁኑ ወቅት የዓይነ ሥውራን የማንበብና የመጻፍ እንዲሁም የመመራመርና ያላቸው ክህሎት ገቢራዊነት ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት ጎታታ በመሆኑ በጣም የሚያሳዝን ነው ብለዋል።
ብፁዕነታቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትና ክብር ሰነድ አንቀጽ 27 እንደሚያመለክተውም “የእያንዳንዱ ዜጋና ማኅበረሰብአዊ ባህል ተሳታፊነት መብትና ክብር” መጠበቅ የሚለውን ጠቅሰው፣ የደራሲ መብት ጥበቃ ማለት ሌላው ለማወቅ ያለው ወይንም በባህል የመሳተፍ መብቱ የሚያገል ማለት እንዳልሆነ አብራርተው፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮነ አስራ ሦስተኛ Rerum Novarum-አዳዲስ ነገሮች” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዝክረ 90 ዓመት ምክንያት Laborem Exercens-የሰው ልጅ ሥራ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት የአካል መሰናክል ላላጋጠማቸው ብቻ የሚያስብ ምርጫና ሂደት አድልዎና ኢሰብአዊ ተግባር ነው” በማለት ያሰፈረው ሓሳብ ብፁዕ አቡነ ቶማሲ ጠቅሰው፣ ቅድስት መንበር የደራሲ መብት ጥበቃና እንዲሁም የምሁራንና ሊቃውንት የምርምር ውጤት ግኝት መብት ጥበቃ ትደግፋለች፣ ሆኖም ግን እወቅትና ምርምር እንዲሁም ግኝት ለማህበራዊ ጥቅም የሚል እምነት እንዳላት አብራርተው፣ ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት የእውቀት ውጤት ለጥቂቱ እርባና ያቀና መሆን የለበትም ካሉ በኋላ በመጨረሻ የሥነ ምርምር ግኝትና የዕደ ጥበብ ግኝቶች ተፈጥሮና የሰው ልጅ ሰብአዊነትን የሚያከብር መሆን ይገባዋል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.