Home Archivio
2012-09-28 14:07:38
ቅዱስት መንበር ለሰው ልጅ ደህንነት ጥበቃ ዋስትና ነች
በቅርቡ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አንድ በሩዋንዳ እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. ተከስቶ በነበረው በጅምላ ጭምጨፋ ማለት ተፈጽሞ በነበረው ዘረ በማጥፋት ጭፍጨፋ ተግባር እጅ አለባቸው ተብለው የተከሰሱት አንድ
የአገሩቱ የሰበካ ካህን አባ ቡቲሁንዛ በቅድስት መንበር የተጠበቁ ናቸው የሚለው የሰጡት ዜና በማስመልከት የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና በቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ሕንጻ የጉባኤ አዳራሽ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ቅድስት መንበር ተከሳሹ ካህን ለመከላከልም ሆነ እሳቸውንም በመደገፍ ያከናወነቸው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለ መኖሩ ብቻ ሳይሆን ቅድስት መንበር ከተከሳሹ ካህን ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት እንደሌላት ይፋ አድርገዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.