2012-09-26 13:20:42

ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት፦ የጤናማ መልካም ኑሮ ሳምንት


የጋራ ንብረት ወይንም ሃብት ላይ ያተኮረ “የጤናማ መልካም ኑሮ ሳምንት” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው መርሃ ግብር በኢጣሊያ በፎርሊ ቸሰና ከተማ ከትላትና በስትያ መከፈቱ ሲገለጥ፣ ይህ ባህል ጸረ ኤኮኖሚ ወይንም ባህል የኤኮኖሚ እድገት ያስገኛልን? የሚል ጥያቄ RealAudioMP3 በማስተጋባት ባህል የጋራ ሃብት እርሱም ለማኅበራዊ ጥቅም ያቀና መሆኑ በማጉላት፣ ለጤናማው ኑሮ መሠረት መሆኑ የሚስተነተንበት ሳምንት እንደሚሆንም የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ባለ ሥልጣን ብፁዕ አቡነ ፍራንኮ ፐራዞሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የሚካሄደው የጤናማ መልካም ኑሮ ሳምንት የሚያቀርበው ጥያቄ፣ ባህል ሲባል ብዙውን ጊዜ የኤኮኖሚ ሃብት የሚሟጥጥ እንደሆነ ተደርጎ እንደሚገለጥ የሚያሳውቅ ከመሆኑም ባሻገር፣ ባህል የማምረት አቅም የሌለው ነው ተብሎ ሲገለጥ እንሰማለን፣ ከዚህ አንጻር ሰው በኤኮኖሚ ራእይ ብቻ በማንበብና በመግለጥ ለባህል ክብር እውቅና የማይሰጥ ሁኔታ መስፋፋቱ ነው የሚያስረዳን፣ የጋራ ሃብት ወይንም ማኅበራዊ ጥቅም ለሕዝቦች ጥምረት ለሕዝባዊ ጣምራ መለኪያ ነው። ስለዚህ የጋራው ሃብት ተጠቃሚው ሕዝብ መሆን አለበት፣ የጋራ ሃብት ለጋራ ጥቅም ማዋል በሕዝቦች መካከል ጥምረትን ያጎናጽፋል፣ የጋራው ሃብት ተጠቃሚው ውሱን የኅበረተሰብ ክፍል ሲሆን በሕዝቦች መካከል መከፋፈልን የበላይነትና የበታችነት ደረጃ እንዲከሰትም ያደርጋል፣ ጤናማ ኑሮ ሲባል የተስተካከለ ሁሉም የጋራ ሃብት ተጠቃሚ ሲሆንና ብቻ ነው ብለዋል።
ይህ ሳምንት በርግጥ የተለያዩ ሃይማኖትች መካከል ግኑኝነት የሚያነቃቃ የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ወሳኝ መሆኑ፣ የተለያዩ ባህሎችን በማገናኘት ሰብአዊ ግኑኝነቶች እንዲበረታታ የሚያነቃቃ ነው። በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ በስፍት በሚታይበት ወቅት “ሰው ውሱን ቢሆንም ቅሉ መጻኢን ይዞ ይጓዛል” በሚል ርእስ የጤናማ ኑሮ ሳምንት ማካሄድ ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለመቀረፍ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ በማቅረብ ሂደት አቢይ አስተአዋጽኦ ይኖረዋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.