2012-09-26 13:16:49

ዓውደ ጥናት “Il Cortile dei Gentili-የአህዛብ ቅጥር ግቢ”
“የማይታወቅ እግዚአብሔር” (ግብረ ሓዋ. 17፣23)


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን RealAudioMP3 የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ ያነቃቃው መርሃ ግብር በመቀጠል እ.ኤ.አ. መስከረም 13 እና 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በዚያች ሉተራናዊ ባህልና በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሃይማኖትና ግብረ ገብ የሚያገል ቅጥ አልቦ ዓለማዊነት ባህል እጅግ በተስፋፋባት ስለ እግዚአብሔርም ሆኖ ባጠቃላይ ሃይማኖታዊ ርእሰ ጉዳዮች በማይነሳባት አገረ ስዊድን “ዓለም ከ-ወይም አለ-እግዚኣብሔር” በሚል ርእስ ሥር ካካሄደው ዓወደ ጥናት በመቀጠል እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 እስከ ጥምቅ 6 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ “የማይታወቅ እግዚአብሔር” (ግብረ ሓዋ. 17፣23)” በሚል ርእስ ዙሪያ እምነት እና አልቦ እምነትን የሚያወያይ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚና የቅዱስ ገዳም ዘአሲዚ የዜናና ማኅትመት ጉዳይ ዋና አስተዳዳሪ አባ ኤንዞ ፎርቱናቶ እንዲሁም ደራሲ ቪቸንዞ ቸራሚ በጋራ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ይህ የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ እና ሌሎች የኢጣሊያ አበይት የፖለቲካ አካላት ከውስጥና ከውጭ አገር መጥ አማንያንና ኢአማንያን ምሁራን እንደሚሳተፉም ለማወቅ ተችለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ የሚጀመረው ያወጁት የእምነት ዓመት ላይ በማነጣጠር የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንዲካሄድ የወጠነው የአሲዚው ዓወደ ጥናት በርግጥ በዚያ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ለውይይትና ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አብነት በሆነቸው ከተማ “አንድ የማይታወቅ፣ እግዚአብሔር” በሚል ርእስ ሥር 40 ሊቃውንት አስተምህሮ የሚሰጡበት ዓወደ ጥናት መሆኑ ብፁዕነታቸው ገልጠው ከዚሁ ጋር በማያያዝም የታዳጊ ወጣት ቅጥር ግቢ እንዲሁም የትረካ ቅጥር ግቢ ወጣት ታዳጊዎችን የሚያሳትፍ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
ብፁዕነታቸው እንዳመለከቱትም፦ እስከ አሁን ድረስ የተካሄዱት የአህዛብ ቅጥር ግቢ ዓውደ ጥናቶች ካስገኙት ውጤት አንጻር ሲታይ አወንታዊ መሆኑና አብያተ ክርስትያን ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ከኢአማንያን ጋር ለመወያየት በሮቻቸውን እንዲከፍቱ ያደረገ ነው። በሌላው ረገድ ስለዚሁ ዓውደ ጥናት በማስደገፍ በመገናኛ ብዙኃን ብዙ የማይባል በመሆኑ ይህ የመገናኛ ብዙኃን ግድ የለሽነት ተጋርጦውን ለመቀረፍ የሚያነቃቃ መርሃ ግብር ነው” ብለዋል።
የቅዱስ ገዳም ዘአሲዚ የዜናና ኅትመት ጉዳይ ዋና አስተዳዳሪ አባ ኤንዞ ፎርቱናቶ በበኵላቸውም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት፦ “የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጥቅምት አራት ቀን የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ ዓመታዊ ክብረ በዓል የምታከብርበት ዕለት መሆኑ ዘክረው፣ ይህ በአሲዚ የሚካሄደው የአሕዛብ ቅጥር ቅቢ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ቅጥር ግቢ በማለት ሰይመው፣ የአሲዚው ቅዱስ አምነት የሚጎላበትና የዚህ ቅዱስ ማንነት የሚስተነተንበት መርሃ ግብር ነው” ብለዋል።
በመጨረሻም ደራሲ ቪንቸንዞ ቸራሚ “ይህ ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት በማዘጋጀትና በማነቃቃት የሚያካሂደው ባህላዊ ዓወደ ጥናት በጥልቀቱና ካለው መልእክት አንጻር ሲታይ በኢጣሊያ ብቸኛ አቢይ የባህል መድረክ ነው ለማለት እደፍራለሁኝ” ካሉ በኋላ፣ በኢጣሊያ የራዲዮና የተሌቪዥን ጣቢያ ክፍል በሆነው በራይ አንድ እንዲሁም በቫቲካን የቴሊቭዥን ጣቢያ ቴለ ፓቸው አማካኝነት በቀጥታ እንደሚሰራጭ አስታውሰዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.