2012-09-21 13:37:52

ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ፦ አቶሚክ የጦር መሣሪያ ጨርሶ በማስወገድ የአቶም ሃይል ለህዝባዊ አገልግሎት ጉዳይ ማዋል።


የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ባለፉት ቀናት በቪየና ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጠሪ ድርጅት ባካሄደው 56ኛው ጠቅላይ ጉባኤ RealAudioMP3 ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፦ “የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ትጥቅ በማራገፍ የአቶም ኃይል ምንጭ ለህዝባዊ አገልግሎት ማዋል ለሰላማዊ ዓላማ እንዲሁም ለሰብአዊ እድገት ማስፈጸሚያ ማዋል በአማራጭ የሚታይ ዓላማ ሳይሆን ብቸኛ ዓላማ መሆን ይገባዋል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“የኑክሊያር ዕደ ጥበባዊ ሂደት፣ ለሕይወት ወይም ለሞት ባህል አገልግሎት ማዋል የተሰኙት አማራጮች እንዳሉትም” ብፁዕነታቸው ጠቅሰው፣ አስፈላጊው የመጀመሪያው እርሱም ለሕይወት ባህል ማስተግበሪያ የሚለው ዓላማ ከመከተሉ ይልቅ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ለሞት ባህል ማስፈጸሚያ ትግባሬው አመዝኖ እንደሚገኝ ነው ማለታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ባንድ በኩል የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ቅነሳ ሲፈጸም በሌላው ረገድ የኑክሊየር ጦር መሣሪያ እጅግ የማራቀቅ መርሃ ግብር በተዋከበ ሁኔታ ሲፈጸመ ይታያል እንዳሉም፣ የኑክልየር ጦር መሣሪያ ቅነሳ በግብረ ገብ አንጻር ሲታይ ለብቻው በቂ አይደለም ስለዚህ በሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃና ለሰብአዊ ሕይወት ክብር መሠረት የሆነው የሰላም ባህል መገንባት በተሰኘው ዓላማ መሟላት አለበት” እንዳሉ ያመለክታል።
የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ ከኑክሊየር ኃይል ምንጭ ጋር በተያያዥነት የሚዘረዘሩት ርእሰ ሕልውና ለመከላከል ከጸረ አሸባሪያ የኑክሊየር ጥቃት ዛቻ ለመከላከል ብሎም የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ጥቁር ገበያ” የተሰኙትን ጉዳዮች ጠቅሰው፣ ስለዚህ ለጸጥታና ደህንነት ጥበቃ መሣሪያ ማዋል ለሚለው እቅድ ማስፈጸሚያ የሚገፋፉ ጉዳዮች ተብለው ቢገለጡም “የዓለም አቀፍ ሰላም ጸጥታና ደህንነት በኑክሊየር ጦር መሣሪያ የሚረጋግጥ አይደለም። እንዳውም ሰላም የሚያናጋ ነው። ስለዚህ ለኑክሊየር ጦር መሣርይ ቅነሳና ብሎም በማጥፋት ይህ የኃይል ምንጭ ለህዝባዊና ለሰብአዊ ልማት ማስፈጸሚያ እንዲውል የሚያዝ፣ የዓለም አቀፍ ስምምነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው። በዚሁ ዘርፍ የስምምነቱ ውል ተረጋግጦ በተናጥል በሁሉም አገሮች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካኝነት በማጽደቅ ለተሟላ ገቢራዊነት ያላሰለሰ ጥረት እንደምታደርግ ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ለውድመት ለስጋት ለመቅሰፍት መገልገያ የሚውል የአውዳሚነት ብቃት ያለው ነው፣ ለሰው ልጅ ሕልውና አደጋም ነው። ስለዚህ ለዓለም አቀፍ ጸጥታና ደህንነት ለመዋስ ብቻ ሳይሆን፣ የኑክሊየር ኃይል ምንጭ ማእከሎች አደጋ እንዳያስከትሉ ተብሎ በነዚህ ማእከሎች የርእሰ ደህንነት ዋስትና ጥበቃ የአደጋ መከላከያ ደንብ ለገዛ እራሱ ዋስትና አያሰጥም። እርግጥ የኑክሊየር ኃይል ምንጭ ማእከሎ ተገቢ የዋስትና ጥበቃ ከአድጋጋ የመከላከያ ደንብ ሊኖራቸው ተገቢ ነው። ይኽም የኑክሊየር ማአክሎች ያለባቸው ኃላፊነት ምንኛ አቢያ መሆኑ የሚያመለከት መሆኑ ነው የሚገልጠው። የኑክሊየር ኃይል ምንጭ ድኽነትና በሽታ ለማስወገድ እቅድም ማዋል አስፈላጊ ነው”። እንዳሉ የጠቆመው የቅድስት መንበር መግለጫ በማያያዝ፣ የኑክሊየር ኃይል ምንጭ በሥነ ሕይወት ዕደ ጥበብ በኑክሊየር ዕደ ጥበብ በሥነ ሕክምና ዕደ ጥበብ ያለው አስተዋጽኦ ማንም የሚዘንጋው አይደለም፣ ሆኖም ይኽ ገጹ በኤኮኖሚ ጥቅም አንጻር ሥር አስቀምጦ የትርፍ ማካበቻ መሣሪያ አድርጎ ድኻው የዓለም ሕዝብ የዚህ ዕደ ጥበብ ተገልጋይነት መብት መጣስ፣ ቅድስት መንበር በጥብቅ በማውገዝ፣ የኑክሊየር ኃይል ምንጭ ለህዝባዊና ለሰብአዊ ልማት መዋል አለበት እንደምትል ነው” እንዳሉ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.