2012-09-19 18:49:59

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፧
ዛሬ በሓሳቤና በልቤ ባለፉት ቀናት በሊባኖስ ያካሄድኩትን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደገና ለማሰላሰል እወዳለሁ፣ ምንም እንኳ ሁኔታው እጅግ ከባድ ቢሆንም ልጆቹ ከባድ ችግር ሲያጋጥማቸው አባታቸው አጠገባቸው መሆን አለበት በሚል እምነት ጉዞውን ለማድረግ ታላቅ ፍላጎት ነበረኝ፣ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ጌታ ለሐዋርያቱ የተወላቸውን ሰላም ለመላው መሃከላኛው ምሥራቅ ለማብሰር በጌታ ቃላት አጠር ባለ መንገድ “ሰላምየን እሰጣችዋለሁ” (ዮሐ 1427)፣ የዚህ ጉዞዬ የመጀመርያ ዓላማ ቤተ ከርስትያን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚለው ድኅረ ሲኖዶሳዊ ምዕዳን ለመፈረምና በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ማኅበረ ክርስትያን ተወካዮችና ለሌሎች አብያተ ክርስትያንና ማኅበረ ክርስትያን ተውካዮች እንዲሁም ለሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች ለማስረከብ ነው፣ RealAudioMP3
እጅግ ደስ የሚል የቤተ ክርስትያን ፍጻሜ ነበር፣ እንዲሁም በዚሁ እጅግ የተወዛገበ ሆኖም ግን ለዞኑ መክፈቻ የሚታይበት አገር በመሆኑ ጉብኝቱ በተለያዩ ባህርያት ካላቸው ግለሰቦችና ማኅበሮች የውይይት አጋጣሚ ነበር፣ ይህም የሆነበት ምክንያት ዞኑ የተለያዩ ባህሎችና ሃይማኖቶች ተቻችሎ የመኖርና ገንጊ የሆነ መተባበር ስላለው ነው፣ በዛኛው የመካከለኛ ምሥራቅ ዞን ብዙ ሥቃይና ችግር ቢታይበትም ቅሉ ለተወዳጁ የመካከለኛ ምሥራቅ ነዋሪ የመበረታታትና የሰላም መልእክቴን በማበርከት ቅርበቴን ገለጥሁ፣ ለየት ባለ መንገድ ሲርያን በሚያሰቃየው ዘግናኝ ግጭቶች ሳስብ ይህ ግጭት ያስከተለው በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞትና ቤት ንብረታቸው ትተው የሚሰደዱ ሕጻናት እናቶችና አዛውንቶች እጅግ ያሳስበኛል፣ በኢራቅ ያለው አስቸጋሪ ሁኔታም አልረሳሁትም፣ ጉብኝቱ ባካሄድኩበት ወቅት የሊባኖስና የመላው መካከለኛ ምሥራቅ ካቶሊካውያን የሌሎች አብያተ ክርስትያን ተወቃዮች እንዲሁም ማኅበረ ክርስትያኑና ማኅበረ ሙስሊሙ ከፍ ባለ ስሜትና በተረጋጋ መንፈስ የእርስ በእርስ መከባበርና መረዳዳት ግዜ እንዲሁም ለመላው የሰው ልጅ ብርቱ የተስፋ ምልክት የሆነ የመረዳዳትና የወንድማማችነት መንፈስ ታይቶበታል፣ ከሁሉ በላይ ግን በብዙ ሺዎች እዛ ከተገኙ የሊባኖስና የመካከለኛ ምሥራቅ ካቶሊኮች ያደርገሁት ግኑኝነት ምእመናኑ ያሳዩት የጋለ እምነት ስሜትና ምስክርነት በልቤ ውስጥ ጥልቅ የምስጋና ስሜት አነሳሳልኝ፣
በበይሩት ከተደረግልኝ ልዩ የሆነ የክብር አቀባበል በኋላ የምፈጽመው ጉዳይ እጅግ ታላቅ የሆነ ሥነ ሥርዓት የሚጠይቅ ነበር፣ ይህም በሐሪሳ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ግሪክ መልካውያን ባሲሊካ ቤተ ክርስትያን በመካከለኛ ምሥራቅ የሚለው ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ላይ ፊማዬ ያኖርኩበት ኣጋጣሚ ነበር፣
በዚህ አጋጣሚ የመካከለኛው ምስራቅ ካቶሊካውያንን ዓይናቸው በመስቀል ለተሰቀለው ክርስቶስን በመመልከት ያሉበት ሁኔታ ችግርና ስቃይ ቢሆንም በመስቀሉ ሐይልን እንደሚያገኙ፣ በፍቅር ጥላቻን ማሸነፍ፣ በይቅርታ ቂምን ማሸነፍ፣ ልዩነትና፣ መከፋፈል፣ በሕብረትና አንድነት በማሸንፍ የፍቅርን ድግስ እንደግሳለን። ከምን ግዜም የበለጠ የዓለም ቤተክርስቲያን ለመካከለኛው ምስራቅ አብያተ ክርስቲያን በፍቅርና በጸሎት አጠገባ መሆንዋን ለሁሉም አረጋገጥኩላቸው። የመካከለኛው ምስራቅ አብያተ ክርስቲያን ትንሽም ቢሆኑ መፍራት እንደሌለባቸውና በእርግጠኝነት እግዚብሔር ከነሱ ጋር እንደሆነና እኔም ቅዱስ አባታቸው እንደማልረሳችው ኣረጋገጥሁላቸው፣
በሁለተኛው የሐዋሪያዊ ዑደት ቀን ጠዋት ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችና እንዲሁም የተለያዩ ሃገሮች ዲፕሎማት ልዑካንና፣ የተለያዩ የሐይማኖት መሪዎችን ተገናኝቻለሁ። ለነሱም ለወደፊት ሰላም አንድነትና ሕብረት ለመፍጠር የሚያግዛቸውን መንገድ ጠቁሚያሉ። ይኽም የተለያዩ ባሕሎች፣ ሕብረተሰቦችና ፣ ሐይማኖቶች፣ በሐቅና በግልፅ በመነጋገር ወደ አዲስ ወንድማማችነት፣ መለያየትን በማጣመር የእያንዳንዱን ግለሰብ ሰብዓዊ ሕልውና ለመጠበቅ መስራት ነው። እንዲሁም ከተለያዩ የእስልምና ሐይማኖት መሪዎችም ጋር ተገናኝቼ፣ ውይይታችን በመልካም ፍቅርና አክብሮት ተካሂዳል። ፈጣሪያችንን ለተካሄደው ስብሰባ አመሰግነዋለሁኝ። የምንኖርበት ሕብረተሰብ ልዩ ምልክትና በሕብረት መነጋገርን ሲያስፈልገው ሊባኖስ እንዲሁ እንድትቀጥልና ለአረብ አገሮችና ለመላው ዓለም ምሳሌ መሆን ትችላለች፣
ከሰዓት በኋላ የማሮናዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ መኖሪያ ቤታቸው ልዩ በሆነ አቀባበል ብዙ የሊባኖስ ወጣቶችና በዛ አካባቢ የሚገኙ ወጣቶች ያቀረቡልኝ የደስታ አቀባበል ለብዙዎች የማይረሳና በልብ የሚቀር ደስታ መሆኑን እገልፃለሁ። ለነሱም ከሌላው ዓለም የሚኖሩበት አገር ክርስቶስ የጎበኛት፣ የሞተባትና፣ ለኛ ደሕንነት ሲል በትንሣኤ የተነሳበት ምድርና ክርስትናም የተስፋፋበት አገር፣ መሆንዋን በመግለፅ፣ ምንም እንዃን የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩ፡ ሰላምና ዋስትና ባይኖርም፣ በታማኝነት መሬታቸውን በፍቅር እንዳይተውዋት ሳበረታታ፣ በሐይማኖታቸውም ጠንካራና፣ ተስፋቸው በክርስቶስ የደስታችን ምንጭና የግላችንም ጸሎት ከሱ ጋር የጠለቀ እንዲሆንና፣ እንዲሁም አመለካከታችን የሰፋ፡ ለቤተሰብ፣ ለጓደኝነትና ፣ ለሕብረት አላማ እንዲኖረን ነው። ብዙ ክርስቲያንና እስላም ወጣቶች በሕብረትና በሰላም አንድነት ማየቱ በሕብረት የወደፊትዋን ሊባኖስና መካከለኛው ምስራቅን እንዲመሰርቱና ያለውን ሽብርና ጦርነት እንዲቃወሙ አበረታታሁኝ። እርቅና መስማማት ሞት ከሚያስከትሉ ኣደጋዎች ከፍ በማለት ግፊታቸውን መጨመር ኣለባቸው፣
እሁድ ጠዋት በበይሩት ሲቲ ሴንተር ዋተርፍሮንት ኣደባባይ በተካሄደው የመሥዋዕተ ቅዳሴ ስነ ስርዓት ከተለያዩ መካከለኛው ምስራቅ አገሮች የመጡ ብዙ ጳጳሳትና ምዕመናን ተሳትፈዋል። ሁሉንም በእምነታቸው እንዲኖሩና ሳይፈሩ እንዲመሰክሩ ሳበረታታ በእርግጠኝነት የክርስቲያንና የቤተክርስቲያን ጥሪ ወንጌልን ያለ ልዩነት እንደ ኢየሱስ እንዲመሰክሩ ነው። ሌላው የሰጠሁት ትኩረት ግጭት ባለበት ቦታ ሰላምና ሕግን በማገልገል የሕብረትና የሰላም ገንቢ መሳሪያዎች መሆን እንችላለን። ስርዓተ ቅዳሴው ሲፈጸም ለሁሉም ከሁለት ዓመታት በፊት በሮም በተካሄደው የመካከለኛ ምሥራቅ ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት የሆነ “ቤተ ክርስትያን በመካከለኛ ምሥራቅ” የሚለውን ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምዕዳን አስረኪባያለሁኝ። ሰንዱን ለሁሉም የመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት ፓትሪያኮች ካሕናት እና ማኅበረ ክርስቲያን ተከታዮች ሳስረክብ በዚህች ቅድስት መሬት የሚኖሩ ምዕመናን እምነታቸውን ለማበረታታትና ለመደገፍና በሕብረት ወንጌልን እንዲመሰክሩ የሚረዳ ነው፣
እግዚአብሔርን ለዚ ልዩ ስጦታ አመሰግነዋለሁኝ። የወደፊታ ቤተክርስቲያን በዚህች ምድርና ለወጣቶች ለጎልማሶችና ለቤተሰቦች በክርስቶስ እምነታቸውን እንዲያጠነክሩና አሁንም ከወንጌል ጋር በመሆን ከቤተክርስቲያን ጋር አብረው እንዲጓዙ ነው። ለዚህ ላደረኩት ጉብኝት ሳይታክቱ ለሠሩት በሙሉ በድጋሜ አመስግናለሁኝ። የሊባኖስ ጳጳሳት ፓትሪያርኮችና አብራቸውም በሕብረት ለሰሩት የሲኖዶስ ጳጳሳት ዋና ጽ/ቤት አመሰግናለሁኝ። ውለደ ክህነት፣ ዓለማውያን አማኞች እና የሊባኖስ ሕብረተሰብ ከፍተኛና ውድ ድርሻ አላቸው። በሊባኖስ የካቶሊኮች መገኘት ሕብረተሰቡን በማገልገል የሚሰጡት የተስፋ አስተዋጾ በየዕለቱ በኖዋሪው ሕዝብ ላይ ሞገስን እንደሚያስጨምር በዓይኔ አይቻለሁኝ። ልዩ ኣሳብና ምስጋና ለሊባኖስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለተለያዩ ማኅበራትና እንዲሁም በፈቃደኝነት በጸሎት ለደገፉን ሳመሰግን ለሊባኖስ ፕሬሲደንት ክቡር አቶ ሚሸል ሴሊማንና ለሊባኖስ ሕዝብ ላደረገልኝ ልዩ አቀባበል በጣም አመሰግናለሁኝ። ሙስሊሞች በታላቅ አክብሮትና መልካም ግምት ተቀብለውኛል፣ በጉብኝቱ ወቅት ባሳዩት ቀጣይ እና ገንቢ ሽኝት በክርስትያኖችና በሙስሊሞች መካከል የውይይትና የመተባበር መንፈስ እንዲኖር ጥሪ ለማቅረብ አበቃኝ፣ ሁላችን አብረን መለያየት ዓመጽንና ውግ ያን የሚኰንን ቁራጥና ወሳኝ የጋራ ምስክርነት መስጠት እንዳለብን ግዜው የደረሰ ይመስለኛል፣ ከጐረቤት አገሮችም ሳይቀር የመጡ ካቶሊካውንን ጨምሮ ካቶሊካውያን ምእመናኑ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያላቸውን ፍቅር በታላቅ ስሜት ገልጠዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.