2012-09-19 14:32:30

ቅድስት መንበር
የቁጠባና የገንዘብ ሃብት መሥተዳድር ለግልጽነት የአሠራር ሂደት አዲስ አማካሪ


በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕገ ወጥ የገንዘብ ሃብት ድለባ፣ ሕገ ወጣዊ ዱካውን ለመሰወር የሚደረገው በሕጋዊ መዋዕለ ንዋይ የማዋሉ ሂደት ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ የተወጠነው ደንብ ትግባሬ ቅድስት መንበር የምትከተለው የቁጠባና የገንዘብ መሥተዳድር የግልጽነት አሠራር መመሪያ RealAudioMP3 በዓለም የቁጠባና የገንዘብ ሃብት ዘርፍ የሚደነቅ መሆኑ ሲነገር፣ በቅድስት መንበር ይኸንን አሠራር በበለጠ ለማሳየል በሚል ዓላማ መሠረት የስዊዘርላንድ ተወላጅ የሕግ ሊቅ ረነ ብሩኤልሃርት ለግልጽነት የአሠራር ሂደት አማካሪ እንዲሆኑ መመረጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
አዲሱ አማካሪ ብሩኤልሃርት ከቫቲካን ረዲዮ ጣቢያ በጀርመናኛ ቋንቋ የሥርጭት ክፍለ ጊዜ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የተሰጣቸው ኃላፊነትና ፍጻሜው ሲያመለክቱ፣ የቁጠባና የገንዘብ ሃብት መሥተዳዳር ለሚከተለው ለግልጽነት ያአሠራር ጉዳይ አማካሪ በመሆን ቅድስት መንበር የሕገ ወጥ የገንዘብ ሃብት ሕገ ወጥ ዱካውን ለመሰወር የወንጀልና የአሻባሪያን ኃይሎች የሚከተሉት አሠራር ለመወጋት ታቅዶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተወጠነው ሕግ በማክበር ዘርፍ የምትሰጠው አስተዋጽኦ ለማሳየልና በዓለም አቀፍ ደረጃ ገቢራዊነቱን ለማጠናከር ነው ብለዋል።
ቅድስት መንበር በዚህ ሕገ ወጥ የገንዘብ ሃብት ቁጥጥር ሂደት የምትከተለው አሠራር ቀርበው እንደተረዱትም የሚደነቅ መሆኑ ገልጠው፣ ይኽም እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ሰኔ ወር አጋማሽ የኤውሮጳ ኅብረት ድርገት ባካሄደው ግምገማ የመሰከረው መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ ጠቅሰው፣ ቅድስት መንበር የምትከተለው አሠራር ለማሳየል በሚደርገው ሂደት አማካሪ በመሆን የሚያገለግሉ መሆናቸም አስታውቀዋል።
ምንም’ኳ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተወጠነው የወንጀልና የአሸባሪያን ቡድኖች የገንዘብ ሃብት ሕገ ወጣዊው ዱካውን ለመሰወር በሕጋዊ የኤኮኖሚ አውታሮች ለማዋል የሚደረገው ሽርጉድ ለመወጋት የተለያዩ አገሮች የሚከተሉት መዋቅራዊ አሠራር የተለያየ መንገድ የሚከተል ቢሆንም ቅድስት መንበር የምትከተለው የቁጥጥር አሠራር እጅግ ጠንከር ያለ ነው። ይኽም ቅድስት መንበር ያላት ግብረ ገባዊ መሰረታዊ ኃላፊነት የሚያመለክት ነው ብለዋል።
አገረ ቫቲካን የቁጠባና የገንዘብ ሃብት ማእከል አይደለም፣ ስለዚህ ይኽ ጉዳይ ጎልቶ መነገር የሚገባው የቫቲካን ባህርይ መሆኑም አሳስበው፣ ብዙውን ጊዜ የዓለም አቀፍ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የቫቲካን አይነተኛውን መለያ ሳይገነዘቡና ትክክለኛ ግንዛቤ ሳይኖራቸው የሚያሰራጩት ማስታወቂያ ጫና ያለው ቢሆንም፣ ይኽ አባባል ምንም’ኳ በቫቲካን እንደ ነጻ አገር የገንዘብ ሃብት ግብይት የሚከናወን ቢሆንም፣ ቫቲካን የገንዘብ ሃብት ማእከል ብሎ መግለጥ ምክንያት አድርጎ መጥቀስ አቢይ ስህተት ነው፣ ሰለዚህ ቅድስት መንበር የወንጀል ወይንም የአሸባሪያን ሕገ ወጥ የገንዘብ ሃብታቸውን ዱካውን ለመሰወር የሚከተሉት ሕጋዊ መዋዕለ ንዋይ በመቆጣጠር ለመዋጋት የምትከተለው አሰራር የሚደነቀው መሆኑ ማስተጋባት አስፈላጊ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የወንጀልና የአሸባሪያን የገንዘብ ሃብት ሕገ ወጥነት ዱካውን ለመሰወር የወንጀልና የአሸባሪያን ቡድኖች የሚከተሉት መንገድ ለመቆጣጠር የሚሰጠው መለኪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እግብር ላይ ለማዋል ዓለም አቀፋዊ ትብብር አለ። አገረ ቫቲካን ይኸንን ትብብር ለማሳየል በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥረት ከሚያደርጉት አገሮች ውስጥ ቀዳሚነት ይዞ ይገኛል፣ እንዳውም የተወጠነው ደንብ ዘላቂነት ያለው የረዥም እቅድ እንዲሆን አስተዋጽኦ ትሰጣለች ካሉ በኋላ፣ ሥራውን ጀምረው ይኸንን የቅድስት መንበር ውሳኔና ጥረት ለማሳወቅና በዚህ ዘርፍ ለምትከተለው መንገድ በማማከር ለማገልገል ዝግጁ ነኝ በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.