2012-09-15 08:00:29

የር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ሐዋርያዊ ዑደት በሊባኖስ


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ ላይ በመካከለኛው ምስራቅ፤ ሊባኖስ ላይ የሶስት ቀናት ሐዋርያዊ ዑደት ለመጀመር ከመንበረ ሐዋርያዊ ከጰጥሮስ ተነስተዋል፣ ቅዱስነታቸው ከሮም ወደ በይሩት ሲበሩ ለጣልያን ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ እና ላቋረጥዋቸው ሀገራት መሪዎች ማለት የቆጵሮስ እና የግሪክ ሀገራት መሪዎች ለካሮሎስ ፓፖውልያስ እና ለቆጵሮስ መሪ ዲመትሪስ ክሪስቶፍያ የሰላምታ ተለግራሞች አስተላለፈዋል፣
የሊባኖስ ርእሰ ከተማ በይሩት ከዘለዓለማዊት ከተማ ሮም 2.196 ኪሎሜትር ርቀት ያለው ሲሆነ በረራው ሶት ሰዓት ከ15 ደቂቃ መፍጀቱ ታውቆዋል፣ ቅዱስ አባታችን በበይሩት ሰዓት አቆጣጠር 13 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ራፊቅ ሐሪሪ ሀገራት አቀፍ አውርፕላን መራፍያ ደርሰዋል፣
የቅድስነታቸው አውሮፕላን በሰላም ራፊቅ ሐሪሪ እንደ ደረሰ በሊባኖስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል እና የሐዋርያዊ ጉብኝቱ የፕርቶኮል ዋና ሐላፊ የቆመውን አውሮፕላን ውስጥ ገብተው ለቅድስነታቸው ሰላምታ አቅርበዋል፣
ቅዱስነታቸው ከአሊታያ አውሮፕላን እንደወረዱ የሀገሪቱ የመንግስት በፕረሲዳንት ሚሸል ስለይማን በየማሮናዊት ቤተ ክርስትያን ፓትርያሪክ ቡቸራ ቡጥሮስ ራይ የሚመሩ የሃይማኖት እና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል፣
በመንግስት በኩል ከፕረሲዳንት ሚሸል ሱለይማን ሌል የሊባኖስ መንግስት ሸንጎ ፕረሲዳንት ናቢህ በሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕረሲዳንት ናጂብ ሚቃቲ በርካታ ዲፕሎማቶች የተገኙ ሲሆን ሁለት ሕጻናት ለቅድስነታቸው ጉንጉን አበባ ሰጥተዋል። ለቅዱስ አባታችን በነዲክት ክብርም 21 ግዜ የመድፍ ድምጽ ተሰምተዋል፣
የሊባኖስ እና የቫቲካን ብሔራዊ መዝሙሮች ከተሰሙ በኃላ የሊብኖስ መንግስት ፕረሲዳንት ሚሸል ሱለይማን በመንግስታቸው እና ህዝብ ስም የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል፣ “በሀገራችን ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን ማቀድዎ እና ገቢራዊ ማድረግዎ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል በዚሁ አጋጣሚ የሊባኖስ ማህበረ ስቦች በጉብኝትዎ ደስተኞች መሆናቸው ሊገልጽልዎ እወዳለሁ፣ እዚህ ሊባኖስ ውስጥ መልካም ቆይታ እንዲሆንልዎ ከልብ እመኛለሁ ቅዱስ አባታችን የሰላም ሰው በመሆንዎ እና ወደ ሊባኖስ በመምጣትዎ ጥልቅ ደስታ ይሰማናል፣” ብለዋል፣
ፕረሲዳንቱ የእንኳን ደሃን መጡ ንግግር ካደረጉ በኃላ ቅድስነታቸው ባሰሙት ንግግር “ክቡር ፕረሲዳንት ሚሸል ሱለይማን በመጀመርያ መንግትዎ እና የሊባኖስ ጳጳሳት እና ፓትርያሪካት በሊባኖስ ሐዋርያዊ ዑደት እንዳደርግ ለሰጣችሁኝ ዕድል ከልብ አመስገናለሁኝ እግዚአብሔር የተመስገነ ይሁን” ብለዋል፣
ቅድስነታቸው ንግግራቸው በማያያዝ “በሊባኖስ ሐዋርያዊ ዑደት ለማደረግ ያበቃኝ እግዚአብሔር አመስግናለሁኝ ካሉ በኃላ ሀገሪቱ ሲጐበኝ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፣ በቅድስት መንበር እና በሊባኖስ መንግስት መካከል ያለውን የቆየ ጽኑ ግንኙነት ለማስታወስ እወዳለሁኝ” ያሉት ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ይህንን መልሶ ለማጠናከር እንደሚረዳ ከፍተኛ እምነት እንዳላቸውም ገልጠዋል፣ “ሐዋርያዊ ጉብኝቱ እስዎ ሕዳር ወር በ2008 በቅርቡም በወርሀ የካቲት 2011 ቫቲካን ላይ ላደረጉት ጉብኝት ከ11 ወራት በኃላም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቫቲካን ጉብኝት መልስ መሆኑም መጥቀስ እወዳለሁኝ” ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው በበይሩት ራፊቅ ሐሪሪ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ያደረጉት ንግግር በማያያዝ፡ “ሌላው የዚሁ በሊባኖስ የሚያካሄደው ሐዋርያዊ ጉብኝት ምክንያት የመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት Ecclesia in medio oriente የመካከለኛው ምስራቅ ቤተ ክርስትያን የተሰኘ ቫቲካን ውስጥ የካሄዱት ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ለመፈርም እና ለጳጳሳቱ ለማስረከብ ነው” ብለዋል፣ በመቀጠልም፤ “በዚሁ አጋጣሚ ለሁሉም የሊባኖስ ፓትርያሪካት በተለይ የሊባኖስ ማሮናዊት ቤተ ክርስትያን የቀድሞ ለፓትርያሪክ ናስራላህ ቡጥሮስ ስፊር እና የወቅቱ ፓትርያሪክ በቸራ ቡጥሮስ ራይ አመሰግናለሁኝ፣ እንዲሁም ጠቅላላ የመካከለኛው ምስራቅ ክርስትያኖች ሰላምታየ ይድረሳቸው” ብለዋል፣
“ዛሬ ፈርሜ ለመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት እና ፓትርያሪካት የማስረከበው የድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ለሚቀጥሉ ዓመታት የጉዞ ሰሌዳ ይሆናል፣ እዚህ በይሩት ውስጥ ከክርስትያኖች ጋር አብሬ ስጸልይ እና መሥዋዕተ ቅዳሴ ሳሳርግ ደስታ ይሰማኛል፣ እዚህ ለሚገኙ የሊባኖስ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ሰላምታዪ ይድረሳቸው፣ ባለፉት ሩቅ ዓመታት ሊባኖስ ውስጥ የነበረው አሳዛኝ ሁኔታ አልረሳሁትም ሆኖም አሁን ሊባኖስ ውስጥ የተለያየ እምነት የሚከተሉ ማሕበረ ሰቦች በጋርዮሽ በሰላም በመፈቃቀር እና በመተባበር ሲኖሩ ማየት ደስ የሚያሰኝ እና ይህ ለመካከለኛው ምስራቅም ሆነ ለዓለም መልካም አርአያ ነው፣ በጋራ አብሮ ለመኖር ስሜት በማስወገድ እና በሰከነ አእምሮ ማሰብ እንደሆነ ያመለከቱት ቅድስነታቸው ይህ ብዚህ እንዳለ ሆኖ በየቅዱስ ጰጥሮስ ወኪል እና ሊብኖስ መካከል ያለውን ግንኙንት ታሪካዊ እና ጥልቅ ነው፣
ክቡር ፕረሲዳንት እና የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ ወደ ሊባኖስ የመጣሁት የእግዚአብሔር ሰው እና የሊባኖስ እና መካከለኛው ምስራቅ የሰላም መልእክተኛ በመሆን ነው” በማለት የጉብኝቱ ዓላማ ገልጠዋል፣
ቅድስነታቸው ከፕረሲዳንት ሚሸል ስለይማን ጋር በግል ለአጭር ግዜ ከተነጋገሩ በኋላ ከሐሪሪ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሀሪሳ ቤተ ጵጵስና ተጉዘዋል፣ ከምሳ ከዕረፍት በኋላ እዚያው ሀሪሳ ውስጥ ወደ ሚገኘው ግሪክ መልቂታ ቅዶስ ጳውሎስ ካተድራል ተጉዘዋል። ከግሪክ መልቂታ ፓትርያሪክ ጎርጎርዮስ ላሀም ጋር ተገናኝተዋል፣ ካተድራሉ ውስጥም የመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት እና ፓትርያሪካት በተገኙበት በሀሪሳ የቅዱስ ፓውሎስ ካተድራል የድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ፈርመዋል፣
ማምሻውን የዛሬ ሐዋርያዊ ውሎአቸው አጠቃልለው አንድ ኪሎ ሜትር ርቆ ወደ ሀሪሳ ቤተ ጵጵስና ይሄዳሉ፣
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛን ሸኝተው ወደ ሊባኖስ የተላኩ የስራ ባልደረቦቻችን እንደ ዘገቡት፡ የሊባኖስ ጋዜጠኞች፤ the daily star፤ L’Orient፡ le jour፡ Al nahar፡ Ael Moustakbal፡ al Safir፡ እና Aztag የተባለ የአርመን ጋዜጣ በሙሉ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ሐዋርያዊ ዑደት ሊባኖስ በመጀመርያ ገጽ በማስፈር ሐዋርያዊ ጉብኝቱ አስመልክተው ለንባብ አብቅተዋል።ቅድስነታቸው እስከ ፊታችን ሰንበት ሊባኖስ ውስጥ እንደሚቆዩ ይታዋቃል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.