2012-09-07 11:24:01

ቤተ ክርስትያን የወንበዴዎች ሰለባ ለሆኑ እንደ ርኅሩኁ ሳምራዊ ሆና ታገልግላለች


ይህንን ያሉ ቪሲታ አድ ሊሚና ለማድረግ በመንበረ ጴጥሮስ ከር.ሊ.ጳ ጋር የተገናኙ የኮሎምብያ ጳጳሳት ናቸው፣ በኮሎምብያ ያለች ቤተ ክርስትያን በልበ ምሉነት የምትደክመው በዓመጽ ላለቀችው ሃገር የሰላም ተስፋ ለመስጠት ነው፣ የበጎታ መንግስትና ተቃዋሚዎቹ በቤተ ክርስትያን አማካኝነት የሰላም ድርድር እያደረጉ ናቸው፣ በዚህ ሁኔታ ያለችውን ቤተ ማኅበራዊና ግብረ ተል እኮአዊ ሁኔታን ለር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛና ለሮማው ኩርያ ለማስታወስ አንድ የጳጳሳት ቡድን ለቪሲታ አድ ሊሚና ሮም ውስጥ ይገኛሉ፣
ትናንትና ከር.ሊ.ጳ ጋር ከተገናኙ በኋላ የብወንአቨንቱራል ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄክቶር ኤፓልሳ ኲንተሮ ስለግኑኝነቱና ስለሃገረ ስብከታቸው ለቫቲካን ራድዮ ይህንን መግለጫ ሰጥተዋል፣ “እኔ የማስተዳድረው ሰበካ ከ80% የሚሆኑ ከአፍሪቃ የመጡ 3% የአገሩ ተወላጆችና 17% ከሁለቱም የተደባለቁበት ሃገረ ስብከት ነው፣ በሰላማዊ ውቅ ያኖስ ጠረፍ የሚገኝ ራቅ ያለ ሃገረ ስብከት ነው፣ ቦታው የግጭት ቦታ ነው ነገር ግን የሕይወት ወንጌልን ሌት ተቀን እንሰብካለን፣ ብፁዕ ዮውሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዳሉት ይህ ወንጌል የጉዞ አችን መሪ ነው፣ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስም የእውነት ወንጌል ብለውታል፣ ተል እኮ አችን እጅግ ከባድና ፈታኝ ነው ሆኖም ግን የተስፋ ምስክሮች በመሆን እዛ እንገኛለን፣ ከሁሉም በላይ እኔ በምኖረው ዞን ብዙ የሞቱ ብዙም የጠፉ እንዲሁም ብዙ የተፈናቀሉ ሰዎች ይገኛሉ፣ ቤተ ክርስትያን በዚህ አከባቢ እንደ ርኅሩኅ ሰማርያዊ በመሆን ችግርረኞችን ትቀበላለች ከሳቸው ጐንም ትንቀሳቀሳለች፣ በሃገረ ስብከቴ ለምሳሌ ያህል በየዓመቱ ኅዳር 2 ቀን የአጋርነት ቀን ነው፣ እኔ እንደ ጳጳስ ብዙ ሰዎች ወደ ተጐድዋት ቍምስና በመሄድ ከም እመናኑ ጋር በመቃብር ቤት ቅዳሴ አሳርጋለሁ፣ ሥራው ከባድ ቢሆንም የመጽናናት ቃል አደርሳለሁ፣ ለዚህ ሁሉ ኃይል የሚሰጠን ደግሞ ጌታ ራሱ ነው፣ እዚህ መጥተን ሁኔታውን ከቅዱስነታቸው ጋር ተወያይተናል፣ ቅዱስነታቸውም የኮሎምብያ ጳጳሳት የሰላምና የዕርቅ ጉዞ እንዲሳካ በብርቱ ሥራ እንድምንገኝ በመረዳት ከሁሉም በላይ ኃይለኛ ጸሎት እንደሚያስፈልግ እርሳቸውም እንደሚጸልዩ ገልጠውልናል፣ የኮሎምብያ መንግሥት “እውነት ፍትሕ እና መካካስ” የሚል አዋጅ አውጥተዋል፣ እኛ ጳጳሳት ደግሞ ወንጌልን ተከትለን ከዚህ አዋጅ ባሻገር መጀመርያ መሆን ያለበት “ምሕረትና ዕርቅ” ነው እንላለን፣ ሁሌ በመስከረም ወር የሰላም ሳምንት በጸሎትና አስተንትኖ እናከብራለን ስለዚህ ለዚሁ ዓመት የሰላም ሳምንት በብወን አቨንቱራ ሃገረ ስብከቴ መሪ ሃሳብ “የማይታየውን እንደሚታይ እናድርግ” የሚል ሆኖ ወገኖቻቸው ለተጉዱና ለጠፉ ቤተ ሰቦች ለሰላም እንሰራለን አይዞ አችሁ “ሕይወት ፍትሕ መተባበርና ሰላም” የሚል ኮሚሽን አለን፣ ይህም ኮሚሽን ለሰላም ሌት ተቀን እየሠራ ነው፣ ይህ ሁሉ ጥረት እየተደረገም ሳለ ለምሳሌ ዘንድሮ ብቻ 17 ሴቶች ተገደሉ 40 ሰዎች ጠፉ ባጠቃላይ በዓመጸኛ ሞት የተጎዱ 140 ናቸው፣ ይህ ሁሉ ያሳዝነናል፣ ጸረ ሕይወት ነው ጸረ ሰላምም ነው፣ በዚሁ የአዲስ ስብከተ ወንጌል ሲኖዶስ ሊካሄድ በምንዘጋጅበትና የእምነት ዓመት የሚጀመርበት ጊዜ እንደ መላው ዓለም ሁሉ በሥቃይ የምትገኝ አገራችንም የክርስቶስ ፍቅር ኃይል ትሆናለች፣ ሲሉ አስተያየታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.