2012-09-04 15:01:42

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ ፡



የኢትዮጵያ መንግስት ጠቃላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ሥርዓተ ግብአተ መሬት ትናትና ሰንበት ወርሃ መስከረም ሁለት ቀን አዲስ አበባ ላይ ተፈጸመ ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመንበረ ፃባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን ነው የተፈጸመው ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚኒስትሮች ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት የክልል ርእሰ መስተዳድሮች የሃይማኖት አባቶች የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት ወዳጆቻቸው መገኘታቸው ከአዲስ አበባ የደረሱ ዘገባዎች አስታውቀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ከንጋቱ በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ጀምሮ በታላቁ ቤተ መንግስት የፍትሀተ ጸሎት ከተደረገለት በኃላ ለመጨረሻ ስንብት በባልት ቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን ፡ በብዙ ሺ ሃዘንተኞች ታጅቦ እና በወታደራዊ ክብር ዘብና በሃዘን ማርሽ ታጅቦ መስቀል አደባባይ መድረሱ ዘገባዎቹ አስገንዝበዋል።
በመስቀል አዳባባይ በተካሄደው መንግስታዊ የሃዘን ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች የመንግስታት ተወካዮች ዓለም አቀፍ ልዑካን መገኘታቸው ተነግረዋል።
“አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመኑ ለራሱ እና ለቤተ ሰቡ ግዜ ሳሰጥ
ለኢትዮጵያ ህዝብ እድገት የተጋ እና ድህነትን ለማጥፋት ሌት ተቀን የሰራ
መሪ ነበረ “ በማለት እመቤት አዜብ መስፍን በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ መናገራቸው ከቦታው የደረሰ ዜና ዘግበዋል።
በማያያዝም “መለስ ለህዝብ ኖሮ ለህዝብ የሞተ “”በመሆኑም የጀመራቸው የልማት ተግባራት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን ከግብ ለማድረስ ጥረት እንደሚያደርጉ መግለጣቸው ተመልክተዋል።የተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች እና የመንግስታት ልዑካንም ንግግር ያዳረጉ
ሲሆን ሟቹ ጸረ ድህነት ያለሰለሰ ጦርነት ያካሄዱ የመልካም አመራር ሂደት የቀየሱ እና ይህንን ያራመዱ በማለት ማወደሳቸው ተገልጸዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት ዘ ካቶሊካውያን እና የሀገሪቱ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉብባኤ ፐረሲዳንት ብጹዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ትናትና የቀብር ሥነ ሥርዓት የተፈጸመላቸው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተዉት ውርሻ ማለት ራእይ ምን እንደሚመስል እና በቅርብ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ትናንቱ ህዝባዊ መንጋታዊ እና ዓለም አቀፋዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት አልታየም እና ይህ እንዴት ይመለከቱታል ፣ ፣
ብጹዕ አቡነ ብርሃነ የስሱስ ለሰጡኝ መግለጫ ፡ በስሜ እና በራድዮ ቫቲካን የአማርኛ እና ትግርኛ አድሞጮች አመሰግንዎታለሁኝእግዚአብሔር ይስጥልኝ።








All the contents on this site are copyrighted ©.