2012-08-27 11:51:04

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ባለፉት የዕለተ እሁድ አስተንትኖዎች “ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ” መሆኑን የገለጠበት በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ሰዎች በአምስት እንጀራና ሁለት ዓሣዎች ከመገበ በኋላ በቅፍርናሆም ቤተ መቅደስ ስላደረገው ንግግር ተመልክተናል፣ ዛሬ የሚቀርብልን ቃለ ወንጌል ደግሞ ሐዋርያት ለዚህ ንግግር የሰጡት ግብረ መልስ የሚመለከት ነው፣ ኢየሱስ ንግግሩን ያቀረበው ሆን ብሎ ግብረ መልሳቸውን ለማወቅ መሆኑን ለመግለጥ እዛ ከሐዋርያት ጋር አብሮ የነበረው ወንጌላዊው ዮውሐንስ “በዚህም ምክንያት ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ኢየሱስን መከተል ተዉ” (ዮሐ 6፤66) ይላል፣ ለምን ያልን እንደሆነ ምክንያቱ ኢየሱስ “ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፣ ሥጋዬ የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ ለዘላለም ይኖራል” (ዮሐ 6፡51፡54) ያለውን ስላላመኑ ነው፣ እውነትም እነኚህ ቃላት ያኔ ልትቀበላቸውና ልትረዳቸው እጅግ ከባድ ነበሩ፣ እንዳልኩት ይህ ግልጸት ለእሳቸው አይገባቸውም ነበር ምክንያቱም እሳቸው በዚህ ዓለም አስተሳሰብ ያስቡ ነበርና፣ ሆኖም ግን በእነዛ ቃላቶች የኢየሱስ ምሥጢረ ፋሲካ እንደ ትንቢት ተነገረ፣ ማለትም እርሱ ለዓለም ድኅነት ራሱን አሳልፎ እንደሚሰጥ የአዲስ ኪዳኑ ቍርባን ሥጋውና ደሙ ሆኖ የእርሱ በቅዱስ ቍርባን መኖርን ይገልጥ ነበር፣
ኢየሱስን ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ትተውት እንደሄዱ ባየ ጊዜ ወደ አሥራ ሁለቱ ቀና ብሎ “እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁን፧” አላቸው (ዮሐ 6፡67)፣ በሌሎች አጋጣሚዎች እንደሆነው ሁሉ እዚህም ቅዱስ ጴጥሮስ በአሥራ ሁለቱ ስም “ጌታ ሆይ! ወደ ማን እንሄዳለን፧ አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፣ እኛም ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ አንተ እንደሆንክ አምነናል አውቀናልም” (ዮሐ 6፡68-69) ብሎ ይመልሳል፣ እኛም እንደ እርሱ ወደ ማን እንሄዳለን፧ ብለን ማሰላሰል እንችላለን፣ ይህንን ጥቅስ የሚመለከት እጅግ ጥሩ የሆነ የቅዱስ አጎስጢኖስ ሐተታ አለ፣ ቅዱሱ ስለ ዮውሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 በሚያቀርበው ስብከት “አያችሁ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ በእግዚአብሔር ጸጋ እና በመንፈስ ቅዱስ አስተንፍሶ ወዲያውኑ ተረዳው፣ ለምን ተረዳው ያልን እንደሆነ ስለአመነ ነው፣ ለዚህም አንተ የዘላለም ሕይወት ቃላት አሉህ፣ አንተ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ሥጋህን እና ደምህን በመስጠት ሕይወት ትሰጠናለህ፣ እኛም አምነናል አውቀናልም፣ ይላል፣ አውቀናል ከዛም አምነናል አይልም ነገር ግን አምነናል ከዛም አውቀናል ይላል፣ ለማወቅ አምነናል፣ ምናልባት ከማመን በፊት ለማወቅ የሞከርን ብንሆን ኖሮ ለማወቅም ይሁን ለማመን ባልቻልንም ነበር፣ በምን አምነናል ምንስ አውቀናል፧ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ መሆንህን ማለትም አንተ ዘላለማዊው ሕይወት ራሱ ነህ፣ በሥጋህና በደምህ ማንነትህን ትሰጠናለህ” ይላል ቅዱስ አጎስጢኖስ ለምእመናኑ ባቀረበው ስብከት፣
በመጨረሻ ኢየሱስ ከአሥራ ሁለቱ የማያምን አንድ ሰው እንደነበረ ማለትም ይሁዳ እንደሆነ ያውቅ ነበር፣ ያኔ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርቱ እንዳደረጉት ሁሉ ይሁዳም መሄድ ይችል ነበር፣ እንዲያው ልበ ቅኑና ልበ ንጹሕ ቢሆን ኖሮ ትቶ መሄድ ነበረበት፣ ሆኖም ግን ከኢየሱስ ጋር ቀረ፣ ከኢየሱስ ጋር መቅረቱም በእምነት ወይም በፍቅር ምክንያት ሳይሆን መምህሩን በምሥጢር ለመበቀል ነበር፣ ለምን ያልን እንደሆነ ይሁዳ እንደተከዳ ሆኖ ይሰማው ነበር ምክንያቱም እርሱ ቀናእተኛ ስለነበር መሲሑ በምድራዊ ሥልጣን አሸናፊ ሆኖ በሮማውያን ግዛት አንጻር መሪ እንዲሆን ይፈልገው ነበር፣ ኢየሱስ ይህንን የይሁዳ ተስፋ ውድቅ አደረገው፣ አሁን ችግሩ ይሁዳ ትቶ አለመሄዱ ነው፣ የባሰ ጥፋቱ ደግሞ አስመሳይነቱ ነው፣ ይህም የሰይጣን ባህርይ ምልክት ነው፣ ለዚህም ነው ኢየሱስ ለአሥራ ሁለቱ “ከእናንተ አንድ ዲያብሎስ ነው” (ዮሐ 6፡70) ያላቸው፣
እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ በኢየሱስ እንድናምንና ከእርሱና ከሌሎች ሁሉ ዘወትር በልበ ቅኑነት እንድንኖር ትረዳን ዘንድ እመቤታችን ድንግል ማርያምን እንለምን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.