2012-08-27 15:14:42

33ኛው ዓለም አቀፍ“Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” የጥናት ጉባኤ መጠናቀቅ


እሁድ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊሊያ ሮማ አቅራቢያ በምተገኘው ሪሚኒ ከተማ “Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” የተየሰየመው ካቶሊካዊ ማኅበርሰብ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው ዓለም አቀፋዊ ዓወደ ጥናት በመቀጠል “የሰው ልጅ ዓይነተኛው ባህርይ ከወሰን አልቦ ጋር ተገናኝነት” በተሰየመው RealAudioMP3 ጠቅላይ ርእስ ሥር የማኅበርሰቡ መሥራች ስመ ጥር ነፍሰ ኄር ክቡር አባ ልዊጂ ጁሳኒ “ሃይማኖታዊ ስሜትና ትርጉም” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት አቢይ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ጥናታዊ ሰነድ ላይ ተንተርሶና፣ በተለያዩ የክብ ጠረጴዛ ውይይት፣ በሥነ ጥበብ መግለጫዎችና ትርኢቶች ተሸኝቶ ያካሄደው የዘንድሮ 33ኛው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት ትላትና ነሐሴ 26 ቀ 2012 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. የ 2013 ዓ.ም. 34ኛው ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጥናቱ መርሃ ግብር ከነሐሴ 18 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን ለማካሄድ በመወሰን መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በመዝጊያው ቀን በካይሮ የዚህ “Comunione e liberazione-ሱታፌና አርነት” የጥናት ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር ዋኤል ፋኦሩቅ በግብጽ የአስክንድሪያ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ክይሪሎስ ካማል ዊሊያም ሳማን የግብጽ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ማሪያነ ማላክ በተለያየ መልኩ “አክራሪነትና ሃይማኖተኛነት” ርእስ ዙሪያ ንግግር ሲያደርጉ፣ ለካይሮ ደቡባዊ ክልል የበላይ ፍርድ ቤት ሊቀ መንበር ሆሳም ሚካዊ “የፍትሕ አስፈላጊነት” በሚል ርእስ ሥር ንግግር ማሰማታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አመልክተዋል።
የሪሚኒ አውደ ጥናት አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ኤሚሊያ ጓርነይሪ፦ “የተካሄደው የ2012 ዓ.ም. ዓወደ ጥናት የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ፍጡር መሆኑ ካለው ግንዛቤ የመነጨ ርእሰ መለያው ለይቶ ከዚህ መለያውና መሆናዊው ትርጉሙ ጋር ተመዛዛኝ ሕይወት በመኖር ፍጡር መሆኑና የእግዚአብሔር ጥገኛ መሆኑ መሠረታዊ ክብሩ ማለት እንድሆነ” በተለያየ መልኩ የተስተነተነበና የተገለጠበት ዓወደ ጥናት እንደነበር በመዝጊያው ቀን ምክንያት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.