2012-08-25 11:27:56

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ፡


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርትያን ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትናትና ከቀርት በኁዋላ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን ተፈጽመዋል።
ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ላለፉት ሀያ ዓመታት ቤተ ክርስትያኒቱ መምራታቸው እና ባደረባቸው ሕመም ባለፈው ሳምንት በ76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ነው። ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ሀገሪቱ ውስጥ የሃይማኖት መቻቻል እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ በርካታ ሰብአዊ ተቋሞች በማቋቋም ለችግር የተጋለጡ ኢትዮጵያውያንን የረዱ አባት መኖራቸው አጃንስ ፍራንስ ፕረስ የዜና አገልግሎት ከአዲስ አበባ ዘግበዋል።
ከአዲስ አበባ የተሰራጨ ዜና እንዳመለከተው ከብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ግብዐተ መሬት በፊት በተካሄደው ጸሎተ ፍትሐት ላይ ከግሪክ ከግብጽ ሶርያ እና ከሌሎች ሀገራት አብያተ ክርስትያናት የመጡ የሃይማኖት አባቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
የውጭ እንግዶች የመንግሥት ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የቤተ ክርስትያኒቱ ምእመናን በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተሳትፈዋል።
ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባኤ ፕረሲዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ትናትና ስለተፈጸመው የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በሁለቱ አብያተ ክርስትያናት ማለት በካቶሊካዊት እና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን መካከል ያለውን ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሰጡት አስተያየት እናቀርብላችሁለን። RealAudioMP3








All the contents on this site are copyrighted ©.