2012-08-24 14:17:01

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ሻን በእስያ በቃልና በሕይወት የክርስቶስ መስካሪ”


በ 89 ዓመት ዕድሚያቸው ከትላትና በስትያ ታይዋን በሚገኘው በካቶሊክ ሐኪም ቤት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ያረፉት የኮኣህሲዩንግ ልሒቅ ጳጳስ ቻይናዊ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ብፁዕ ካርዲናል ፖውል ሻን ኩዎ-ሕሲ በማስመልከት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለካኦህሲዩንግ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፒተር ሊዩ ቸንግ-ቹንግ RealAudioMP3 ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት፦ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ሻን ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በማገልገል የኖሩት ምስክርነት በማስታወስ፣ በሳቸው አማካኝነት እግዚአብሔር ለሰጠው ጸጋና ቡራኬ አመስገነው፣ ለወዳጆቻቸው ለወንድሞቻቸው የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት በሙሉ እግዚአብሔር መጽናናቱን እንዲሰጣቸውና የነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ሻን ካህኗ ነፍሳቸው ለእግዚአብሔር ማለቂያ ለሌለው ምሕረት መማጸናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ፊደስ የዜና አገልግሎት ከሰጠው የዜና ምንጭ ለመረዳትም እንደተቻለው፣ በእኚሕ ታላቅ የቤተ ክርስትያንና በቤተ ክርስትያን የሕዝብ አገልጋይ ብፁዕ ካርዲናል ሻን ዕረፍት ምክንያት የሬፓብሊካዊት ቻይና ርእሰ ብሔር ማ ዪንግ ዢዩ የሚገኙባቸው የተለያዩ የመንግሥት ባለ ሥልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች የሐዘን መግለጫ መልእክት ማስተላለፋቸው ሲታወቅ፣ የቡድሃ ሃይማኖት አቢይ መምህር ሼንግ ያን ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት፦ “የብፁዕ ካርዲናል ሻን በሳልና ጥልቅ አስተሳሰባቸው በሁሉም ልብ ውስጥ ለጥልቅ አስተንትኖ መንስኤ ነው” በማለት እንደገለጡዋቸው ሲያስታውቅ፣ በማያያዝ የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት እ.ኤ.አ. እፊታችን መሰከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም. የሳቸውን የአደራ ቃል በሚያከብር በተራ ሥርዓተ ቅዳሴ አማካኝነት የሚፈጸም ሆኖ፣ በፍትሃት የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የሚሰበሰበው ምጽዋትም ለተነጠሉት ድኻው የሕብረተሰብ ክፍል መርጃ እንዲሆን ቃላቸውን በማክበር ለሳን ጉዖ ሺ ማሕበር እንደሚሰጥ ፊደስ የዜና አግልግሎት አስታወቀ።
እኚህ መላ ሕይወታቸው በቻይና ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እንዲሁም በቻይና ለምትገኘው ቤተ ክርስትያን ዕርቅ አገልግሎት ያዋሉ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ሻን በምእመናን በሕዝብ ተወዳጅ መሆናቸው የሚመሰከርላቸው፣ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. በቻይና ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ላስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት ማመስገናቸውና በቻይና በምትገኘው ቤተ ክርስትያን ውስጥ ስደትና መከራ በተከናነበበት ዘመን በቆራጥነት ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ታማኝ ሆኖ የቀረው በድካምነቱም ከዚህች ቤተ ክርስትይን ለተነጠለቸው ቤተ ክርስትያን ለመከተል የመረጠ መካከል ተፈጥሮ ያለው መከፋፈል ተወግዶ ቤተ ክርስትያናዊ ዕርቅ እንዲሰፍን ያገለገሉ፣ የክርስትናው እምነት በእስያ የውሁዳን ቢሆንም የሰናፍጭ ዘር በማለት በመግለጥ ለሦስተኛው ሺሕ ዘመን እስያ የክርስትና እምነት ጸደይ በማለት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የገለጡት ሐሳብ አፍቃሪ እንደነበሩም ፊደስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።
በአስፍሆተ ወንጌል በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት፣ ለዘርአ ክህነት ተማሪዎችና ለውሉደ ክህነት ለተገባ ሕንጸት አሳቢ፣ በብቃት የተሰናዳ ዓለማዊ ምእመን እንዲጸና በሁሉም መስክ ያልታከተ ጥረት ያሳዩ፣ የታመሙት የተገለሉት የኤኮኖሚና የግብረ ገብ ድኽነት ላጠቃቸው እንዲሁም በእድሜ ለገፉት ወላጅ አልባ ለቀሩት በተለያየ መልኩ ለብዝበዛ አደጋ ለተጋለጡት ሴቶች፣ ለእስረኞች ቅርብ በመሆን፣ ማሕበራዊ አገልግሎት የሰጡ በቅርቡ በታይዋን እጅግ ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለው የኑሮ ልዩነት እርሱም በድኻውና በሃብታም የአገሪቱ ዜጋ መካከል የተፈጠረው ልዩነት እንዲቀረፍ ለድኻው የሕብረተሰብ ክፍል ትኵረት እንዲያደርግ ከወንጀለኛ የመቅጫ ሕግ የሞት ፍርድ የሚፈቅደው አንቀጽ እንዲሰረዝ ጥሪ አቅርበው እንደነበርም ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።
እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. በሳምባ ነቀርሳ መጠቃታቸውና ከአምስት ወር ላልበለጠ ጊዜ ብቻ በሕይወት ሊቆዩ እንደሚችሉ ሐኪሞች እንደገለጡላቸው መጀመሪያ ለምን ይኸንን በሽታ ለኔ የሚል ጥያቄ አቅርበው ሲያበቁ ከተረጋጉ በኋላ ግን እግዚአብሔር በግብረ ሰናይ ብቻ ማገልገልን ሳይሆን የሚሰቃዩትን ስቃይ ተካፋይ በመሆን ለሚሰቃዩት ቅርብ ለመሆን ያበቃኝ ነውና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በማለት ተቀብየዋለሁኝ እንዳሉ ዜኒት የዜና አገልግሎት ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.