2012-08-17 13:43:57

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ምኅረት ችላ ማለት ወይም መዘንጋት ማለት ሳይሆን ጥልቅ መለወጥ ማለት ነው”


ምኅረት ዓለማችን በየዕለቱ የሚያስፈልገው ዜና ነው። በክፋት መንፈስ ላይ ድል ካልተነሳ የምንኖርበት ዓለም ይቅር ሊለወጥና ሊሻሻል እንደ ማይችል በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ኢየሱስ የሚሰጠው ምኅረት ያለው ጥልቅ ትርጉሙን ገልጠው፣ ምኅረት ክፋትን የሚገስጽ ብቻ ሳይሆን የሚለውጥም ነው እንዳሉ RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያስታውስ። ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 24 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢጣሊያ አኦስታ ከተማ ጸሎት ዘ ሰርክ መርተው ባስሙት አስተምህሮ፦ “ይቅር ማለት ወይንም ምኅረት ማድረግ ችላ ማለት ወይንም መዘንጋት ማለት ሳይሆን ጥልቅ መለወጥ ማለት ነው። ይኽ ደግሞ የኢፍትኃዊነት ውቅያኖስ በሆነው ዓለም የመልካምነትና የፍቅር ውቅያኖስ ሆኖ እንዲለወጥ የሚያደርገው በእግዚአብሔር የሚያደርግ ተግባር ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
አለ ምኅረት ወይም ይቅር ባይነት ፍትህ አይኖርም፣ ሆኖም ግን ይቅር ማለት ምኅረት ፍትሃዊነትን የሚተካ ወይንም የክፋት መንፈስ ህላዌ መካድ ብሎም ኃጢኣት እንዳለ የሚገልጥ እውነት መካድ ማለት አይደለም፣ በክርስትና እምነት ምኅረት ወይንም ይቅር ማለት አዲስ የፍትህ ትርጉም የሚሰጥ፣ ተገቢ ቅጣት በመስጠት የሚወሰን ሳይሆን እርቅና ፈውስ ያዘለ፣ በሰዎች እንዲሁም በቤተሰብ አባላት መካከል ያለው አለ መግባባት የሚያገል መሆኑ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ባቀረቡት የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፦ “እግዚአብሔር በእኛ ተስፋ አይቆርጥም እኛን አይተውም በእኛ ላይ ትእግስቱ አይደክምም ዘወትር በታላቅ ምኅረቱ እኛን ቀድሞ ሊገናኘን ይመጣል” በማለት እንዳስረዱ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ኢየሱስ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት ይቅር በል ይላል፣ ምክንያቱም እኛም ይቅርታ እንደሚያስፈልገን ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ባቀረቡት ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፦ “ኢየሱስ…ለበደሉንን እንድንጸልይ ይኸንን ከባድ ምልክት እንፈጽም ዘንድ እንዳውም ተበዳዮች ብንሆንም የእግዚአብሔር ብርሃን ልባቸውን ያበራ ዘንድ ዘወትር ይቅርታን በመስጠት ይኸንን ልክ እንደ የእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር ተግባር በጸሎታችን እንደግመውም ዘንድ ‘የበደሉንን ይቅረ እንደምንል በደላችንን ይቅር በልልን’ በማለት በምንጸልየው አባታችን ሆይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረን ጸሎት ተገልጦልናል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.