2012-08-13 14:12:58

የቅድስት ኪያራ ዓመት መዝጊያ
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ “ቅድስት ኪያራ የተአዝዞና የነቢያዊ ሕይወት ብሩህ ጽማሬ ነች”


ባለፈው ቅዳሜ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የቅድስት ኪያራ ዘ አሲዚ ዓመታዊ በዓል ባከበረችበት ዕለት የቅድስት ኪያራ ዓመት ተጠናቀዋል።
የዚህች የዛሬ 800 ዓመት በፊት ገና በ 18 ዓመት ዕድሜዋ ሙሉ በሙሉ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ አብነት በመከተል ለእግዚአብሔር ለመሰዋት እነሆኝ በማለት RealAudioMP3 ገዛ እራስዋን ለእግዚአብሔር የሰጠች የቤተ ክርስትያን ልጅ ቅድስት ኪያራ በማስመልከት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰጡት አስተምህሮ ጥልቅና ሰፊ መሆኑ የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. መስክረም 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ባቀረቡት የዕለተ ረብዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ የቅድስት ኪያራ ዘአሲዚ ምስክርነት፣ እንደ እርሷ አበይት ቅዱሳን በእምነት አበይት የሚባሉት ሴቶች አስተዋጽዖ፣ ሴቶች ለቤተ ክርስትያን ኅዳሴ ያላቸው ብቃት የሚያረጋግጥ ሲሆን ቤተ ክርስትያን ውለታው አለባት” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
ቅድስት ኪያራ ቤተ ክርስትያንን ለማደስ ያስቻላት በትህትና ላይ የጸና ነቢያዊነቷ መሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ባሰሙት ሥልጣናዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሲያብራሩ፦ ቅድስት ኪያራ ምንም’ኳ የደናግል ማኅበር አለቃ የነበረች ብትሆንም፣ በቅድሚያ በጠና የታመሙትን የማኅበሩ አባላት ደናግል በማገልገል፣ ዝቅተኛና የተናቀ ተብሎ የሚገለጠውን የአገልግሎ ተግባር በመኖር በሚሰዋ ፍቅር አማካኝነት ሁሉንም በመወጣት የኖረች ነች። ስለዚህ የክርስቶስ አብነት በመኖር የሚያፈቅር ሕይወት የሚጠይቀው መስዋዕትነት በደስታ ኖራለች፣ ካሉ በኋላ ቅድስት ኪያራ በነበረችበት ዘመን አሁንም ቢሆን ዓለምን ለመለወጥ ለማደስ የሚሹት በእዩልኝ የሚንቀሳቀሱ ቢሆኑም፣ ቅድስት ኪያራ ግን በጽሞናና በትህትና ከወንጌላዊ ፍቅር በመነጨ ኃይል አማካኝነት እወነተኛ ኅዳሴ የመሰከረች ነች። አበይት ቅዱሳኖች ለሰው ዘር ቡራኬ ናቸውብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.