2012-08-10 15:23:48

የእምነት ዓመት ተከታታይ የመስተዳድር ቢሮ መግለጫ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት11 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲከበር ያወጁት የእምነት ዓመት መሠረት የእምነት ዓመት ጉዳይ የሚከታተለው የአመራር ቢሮ ትላትና የእምነት ዓመት መርሃ ግብር ይፋ ማድረጉ RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የእምነት ዓመት የገዛ እራሱ ዳብሊው ዳብሊው ዳብሊው አኑስፊደይ ነጥብ ቪኤይ በሚል ርእስ ሥር በተመሠረተው የድረ ገጽ አድራሻ አማካኝነት የእምነት ዓመት በተመለከት የሚሰጠው ወቅታዊ ዜና የሚቅርቡት መግለጫዎችና ክንዋኔዎች ለመከታተል እንደሚቻል በዚህ አጋጣሚ በማስታወቅ፣ የእምነት ዓመት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የክርስትና እምነት ለማስፋፋት በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 7 ቀን እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ሊካሄድ የወሰኑት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ተግባር እንዲሁም የእምነት ዓመትም ለማርያም አማላጅነት ለማቅረብ ብሎም ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መክፈቻ ዋዜማ ምክንያት ወደ አሲዚና ወደ ሎረቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የፈጸሙት ጴጥሮሳዊ ንግደት የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት በሎሬቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ጴጥሮሳዊ ንግደት በመፈጸም የእምነት ዓመት በይፋ ያስጀምራሉ። እ.ኤ.አ. ጥቅምት 6 ቀን 2012 ዓ.ም. የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በሚል ስያሜ በአማንያንና ኢአማንያን መካከል ያስጀመረው የውይይት አውደ ጥናት መርሃ ግብር መሠረትም አማንያንና ኢአማንያን እምነት ላይ ያተኮረ የውይይት ዓውደ ጥናት በአሲዚ ይካሄዳል።
እ.ኤ.አ. ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው ዲስ አስፍሆተ ወንጌል የክርስትና እምነት ለማስፋፋት በሚል ርእስ ሥር የሚካሄደው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በይፋ ይጀመራል። ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ የመላ አህጉራት የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ብፁዓን ጳጳሳትና የሲኖዶስ አበው የሚሳተፉበት በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 10 ሰዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ የእምነት ዓመት ይጀመራል። ለዝክረ 50ኛው ዓመት የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ምክንያት ካስተል ጋንዶልፎ ከሚገኘው ጳጳሳዊ ሕንፃ ተነስቶ አጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚደርሰው የካቶሊክ ተግባር ማኅበር የሚያዘጋጀው የችቦ የሚመራ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ይከናወናል። እ.ኤ.አ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው በቤተ ክርስትያን ዘኢየሱስ “የዳንተ አሊጔሪ እምነት” በሚል ርእስ ሥር የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው ባህላዊና ሥነ ጥበባዊ መርሃ ግብር ይከናወናል፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው ቅድስት ሶፊያ ካቴድራል፣ በኡክራይን የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አዘጋጅነት ጸሎተ ሰርክ ይደገማል።
እ.ኤ.አ. ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና ለሲኖዶስ አበው ክብር በኡክራይን የመንፈሳዊ መዝሙር መዘምራን ቫቲካን በሚገኘው ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ የውህደ ጥዑም ሙዚቃ ትርኢት ይቀርባል። እ.ኤ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም. የስብከተ ወንጌል ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ያዘጋጀው ልኡካነ ወንጌል ሃሳብ ያደረገ ጸሎተ ሰርክ ይፈጸማል።
እ.ኤ.አ. ጥቅምት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ለሰባት የእምነት መስካሪያን ሰማእታት በቅድስት ቤተ ክርስትያን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ብፅዕና ይታወጅላቸዋል። እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 26 ቀን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በሮማ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ እምነት ተከታይ አስተማሪዎች ማኅበር የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ እምነት ተከታይ አስተማሪዎች ዓለም አቀፍ ጉባኤ ይካሄዳል።
እ.ኤ.አ. ከህዳር 15 ቀን እስከ ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም. የጤና ጥበቃና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሐኪም ቤቶች፣ የአስፍሆተ ወንጌል ሥፍራ፣ ለሰብአዊና መንፈሳዊ አገልግሎት ተልእኮ” በሚል ርእስ ሥር ያዘጃቸው ጉባኤ ይከናወናል። እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሚመሩት በሮማ የሚገኙት ጳጳሳዊ ተቋሞች የጳጳሳዊ መናብርተ ጥበብ ተማሪዎች የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የሮማ አቢይ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የመናብርተ ጥበብ ተማሪዎች የሚሳተፉበት የዘመነ ምጽኣት ቀዳሜ ጸሎተ ሰርክ ይፈጸማል። እ.ኤ.አ. ታህሳስ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ተጀምሮ ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጠቃለል የታይዘ ማኅበርሰብ ከሮማ ሰበካ ኅየንተ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የመላ ኤውሮጳ ወጣቶች ጉባኤ ይጀመራል። የተከበራችሁ አድማጮቻችን የእምነት ዓመት ቀጣዩ የ 2013 ዓ.ም. መርሃ ግብሩን ዝርዝር በሚቀጥለው አርብ እናቀርብላችኋለን።







All the contents on this site are copyrighted ©.