2012-08-06 16:43:32

ዕለተ ሰንበት መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ር ሊ ጳ በነዲክት ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት የበጋ ዕረፍት በማድረግ ላይ በሚገኙበት ካስተል ጋንዶልፎ የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት መካን ትናንትና ሰንበት ከምእመናን ጋር አብረው መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል ።

በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አንድ ሐሳብ አይደለም ከአንድ ህያው ሰው ጋር መገናነት እና ለህልውናችን ስሜት እና ሚስጢር የሚሰጥ ዓቢይ ጉዳይ እንደሆነ ከምእምንን ጋር አብረው መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል ።

በማያያዝም ማተርያል በተመለከተ መጨነቅ የለብንም ከፈጣሪ ኩሉ ዓለም ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር ይገባናል እሱ ሁሉ የሚቻለው እና ቸር ስለሆነ ሊረዳን ልያግዝነ ልያጥናናን ትችላል ብለዋል ቅዱስ አባታች ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ።ቁሳቁሳዊ በሆኑ ነገራት ብቻ ማትኰር አይገባንም ያሉት በነዲክት 16ኛ እምነታችን አጽንተን መያዝ አለብን ለነፍሳችን ከፍተኛ ግምት መስጠት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የዕለቱ ቃለ ወንጌል ጠቅሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ታምራት በሰራበት ግዜ ህዝቡ እሱን ፍከጋ ሲሯሯጡ ነበር እሱ ደግሞ ማተርያላዊ ነገር ለመኖር አስፈላጊ ቢሆንም ከዚያ ባሻገር የእግዚአብሔር ህልውና እንዳይዘነጉ ያስታውሳቸው ነበር ብለዋል።ዕለታዊ ችግር የምግብ የመልበስ የስራ በማሰብ ብቻ ተጠምደው እንዳይቀሩ ከዚህ የበለጠዘለዓለማዊ መንፈሳዊ ምግብ አለ እና አዳማሳችሁ ክፈቱ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡን ያስታውስ መኖሩ አመልክተዋል።

ሙሴ ለህዝበ እስራኤል የመንግስተ ሰማያት ምግብ ሲሰጣቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ራሱ ሰጠ ያሉት ቅድስነታቸው ኢየሱስ የሕወታችን ምግብ ነው ሰጠን ይህ በሰው ስራ የሚገኝ እለ መሆኑ ዘወትር ማስታወስ ያሻል ብለዋል ከምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ።ይህ የእግዚአብሔር ስራ መሆኑ መጠየቅ መለመን መቀበል አለብን ሰው የተፈጠረው ለማተርያል ለቁሳቁስ ጉዳይ አለመሆኑም በነዲክት 16ኛ አስምረውበታል።በደስታም እና በችግር ግዜ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሆነ ከከርስቶስ ጋር ያለን ግንኙነት ጠበቅ አርገን መያዝ አለብን ይህ ካደረግን በእውነት በደስታ እና ፍቅር እንሟላለን ብለዋል ቅድስነታቸው ።አለምን ከስበን ነፍሳችን ካጠፋን ምን ተጠቀምን በሐላፊ ነገር ሳይሆን በዘለዓለማዊ ነገር ላይ ማትኰር እንደሚገባን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ተማጽነዋል።

መድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የህልውናችን ማእከል ነው ፡ የተወደዳችሁ ምእምናን በዚች ዓለም ላይ እንግዶች መሆናችን ከዘነጋን ኢየሱስ ክርስቶስን ረሳን ማለት ነው እና ይህ መሆን የለበትም ብለዋል አክለው በነዲት 16ኛ ።

እምነታችን ዘወትር በኢየሱስ ክርስቶስ እናስቀምጥ ከሱ ጋር እንገናኝ እንጠይቀው እናመስግነው እውነተኛ ትክክለኛ መንገድ የሚመራ የደስታ የርህራሔ የድኅነት መንገድ እሱ ባቻ ነው እና በነዲክት 16ኛ ትናንትና በካስተል ጋንዶልፎ እኩለ ቀን ላይ ከምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ ያሉት ቃል ነው ውድ አድማጮጫችን ።

በበጋ በዕረፍት ግዜም መጸለይ መርሳት የለብንም ከእምነታችን ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖረን ያስፈልጋል በዕረፍት ላለላችሁ መልካም የደስታ ዕረፍት ያደርግላችሁ በማለት ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጠው ምእመናን ተሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.