2012-07-23 17:31:14

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት ለዕረፍት ከሚገኙበት የካስተልጋንደልፎ ሐዋርያዊ አደራሽ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱ ቃለ ወንጌል በመጥቀስና በዓለም ዙርያ በሚከናወኑ ጉዳዮች በማትኰር “ጸላኤ ሠናያት ጠብ ይዘራል እግዚአብሔር ግን ሰላም ይፈጥራል፣” ሲሉ ካስተማሩ በኋላ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በደንቨር ከተማ በተካሄደው ዕልቂት እና በዛንዚባር በጠለቀችው መርከብ አደጋ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ኃዘን በመግለጥ በመንፈስ ቅርበታቸውን ገልጠዋል፣ እንዲሁም በዚሁ ሳምንት በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ የሚከፈቱ የኦሊምፒክ ውድድሮች ለዓለማችን የሰላምና የዕርቅ ፍሬ እንዲያመጡ ያላቸውን መልካም ምኞት ገልጠዋል፣
ቅዱስነታቸው ትናንትና እኩለ ቀን ከካስተልጋንደልፎ አከባቢ እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በቦታው ከተገኙ ምእመናን እና ነጋድያን የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሰረጋቸው በፊት ይህንን አስተምህሮ አቅርበዋል፣
ውድ ውንድሞችና እኅቶች፤ የዚሁ እሁድ ቃለ እግዚአብሔር “እግዚአብሔር የሰው ልጅ እረኛ” መሆኑን የሚያሳስበን መሠረታውና ዘወትር አስደናቂ የሆነ ትምህርት ያቀርብልናል፣ ይህም የሚያመለክተው እግዚአብሔር ዘወትር ሕይወት እንደሚመኝልን እንዲሁም ልንመገብበትና ልናርፍበት ወደ ምንችል ና ወደ መልካም የእረኝነት ቦታ ሊመራን እንደሚፈልግ እንጂ ልንጠፋና ልንሞት እንደማይፈልግ ወደ የጉዞ አችን ዓላማ የሆነው የተትረፈረፈ ሕይወት እንድናገኝ ይረዳናል፣ እያንዳንዱ አባትን እያንዳንድዋ እናት ለልጆቻቸው የሚፈልጉት መልካም ነገር፤ ደስ የሚያሰኝ እና እውን የሚሆን ነገር ቢኖር ይህ ነው፣ በዛሬው ወንጌል ኢየሱስ የጠፉ የቤተ እስራኤል በጎች እረኛ መሆኑን ይገልጣል፣ በሕዝቡ ላይ ያለው አመለካከት የእርኝነት አመለካከት ነው፣ ለምሳሌ ያህል በዛሬው እሁድ ወንጌል “ኢየሱስም ከታንኳይቱ ወጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩ አዘነላቸው፥ ብዙም ነገር ያስተምራቸው ጀመር” (ማር 6፡34) ይላል፣ እንዲህ ባለ አግባብ ኢየሱስ በስብከቱ እንዲሁም ሕመምተኞችን እና ኃጢአተኞችን በመንከባከብ የጠፉትንን በእግዚአብሔር አብ ምሕረት ሥር ወደ ትክክለኛና ዋስትና ያለው ቦታ ሊያሰምር ባደረጋቸው ተግባሮቹ እረኛ የሆነውን እግዚአብሔርን ሥጋ ያለብሳል፣
ኢየሱስ ካዳናቸው የጠፉ በጎች መካከል ማርያም የምትባል ከገሊላ ሓይቅ አከባቢ የመጣች ለዚህም መግደላዊት የተባለች ሴትም ነበረች፣ በዛሬው ዕለት ቤተ ክርስትያናችን የዚህች ቅድስት ዝክረ በዓል ታስታውሳለች፣ ወንጌላዊው ሉቃስ እንደሚያመለክተው (ሉቃ 8፡2) ኢየሱስ ከዚች ሴታ ሰባት አጋጋንት አወጣ፤ በጸላኤ ሠናያት ተውጣ ከነበረችበት አዳናት፣ ይህ ኢየሱስ ያከናወነው የመዳን ተግባር እምን ላይ የተመሠረተ ነው፧ ብለን የጠየቅን እንደሆነ ከእውነተኛ ፍጹም ሰላም የሚመነጭ ግለሰው በሚያደርገው ንስሓና ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ከሚያደርገው ዕርቅ ፍሬ ነው፣ እንደእውነቱ ከሆነ ጸላኤ ሠናያት ሁሌ በሰው ልጅ ልብ የመለያየት ዘር እየዘራ በሥጋና ነፍስ በሰው ልጅና በእግዚአብሔር መሃከል እንዲሁም በግለሰዎች እና በማኅበረሰብ እየለያየና ጠብ እየጫረ በሰው ልጅና በተፈጥሮ መካከልም ሳይቀር መለያየት እየፈጠረ የእግዚአብሔር ሥራን ለማውደም ይጥራል፣ ጸላኤ ሠናያት ውግያና ጠብ ይዘራል፤ እግዚአብሔር ግን ሰላም ይፈጥራል፣ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው ክርስቶስ “እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥” (ኤፈ 2፡14)፣ ይህንን መሠረታዊ የሆነ የዕርቅ ተግባር ለመፈጸም መልካሙ እረኛ የሆነው ኢየሱስ በግ ዑ ለእግዚአብሔር መሆን ነበረበት “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ 1፡29) እንዲህ በማድረግ ብቻ አስደናቂውን የመዝሙረ ዳዊት ተስፋ ማለትም “ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።”(መዝ 23፡6) የሚለውን እውን እንዲሆን አድረገዋል፣
ውዶቼ፧ እነኚህ ቃላት ልባችንን ይቀሰቅሳሉ፤ ምክንያቱም ጥልቅ የሆነውን ፍላጎታችንን ይገልጣሉ፣ ለሕይወት እንድያው ለዘለዓለማዊ ሕይወት እንደተፈጠርን ያውጃሉና፣ እነኚህ ቃላት እንደ መግደላዊትዋ ማርያም እግዚብሔርንና ሰላሙን በሕይወቱ ያጣጣመ ሰው የሚናገራቸው ቃላት ናቸውና፣ ከሁሉም ይልቅ እነኚህ ቃላት በድንግል ማርያም ተነግረዋል፣ እርሷ በመልካሙ እረኛ የሆነው የእግዚአብሔር በግ ተደግፋ በሰማያዊ እረኝነት ለዘለዓለም ትኖራለች፣ ሰላማችን የሆነችው የክርስቶስ እናት ማርያም ስለእኛ ጸልዪልን፣”
በደንቨር ክተማ ዛሬ ጥዋት በተፈጸመው ስሜተ ቢስ በሆነው የግድያ ዓመጽ እና በዛንዚባር ባጋጠመው የመርከብ አደጋ በጠፋው ሕይወት የተሰማኝን ሐዘን እገልጻለሁ፣ የመዋቾቱ ቤተ ሰብና ጓደኞች ሓዘን ተሳታፊ መሆኔን ሳመለክት በዚሁ ለቈሰሉ ሰዎች በተለይ ደግሞ ሕጻናት እና ለሁላቸውም ቅርበቴን በመግለጥ በጸሎቴ እንደማስባቸው ላረጋግጥ እወዳለሁ፣ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ ክርስቶስ ኃይልና መጽናናት እንዲያስገኝላቸው ሐዋርያዊ ቡራኬን እሰጣለሁ፣
ከጥቂት ቀናት በኋላ በለንደን 30ኛው ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ውድድሮች ሊካሄዱ ነው፣ የኦሎምፒክ ውድድሮች በዓለም እስፖርት ታላቅ ክንዋኔ ነው፣ ለዚህም ከብዙ አገሮች ብዙ አትሌቶች ይሳተፋሉ፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ይህንን በልዩ ትኵረት ትመለከተዋለች፣ እነኚህ የሎንዶን ውድድሮች ለመላው ዓለም የወንድማማችነት አጋጣሚ እንዲሆኑ እንጸልያለን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.