2012-07-16 14:31:11

ብራዚል፦ ዓለም አቀፍ የኤኵይፐስ ኖትረ ዳመ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. በ 1939 ዓ.ም. በስመ ጥር ፈረንሳዊ ካህን አባ ሄንሪ ካፋረል ኤኵይፐስ ኖትረ ዳመ በሚል መጠሪያ የምሥጢረ ተክሊክ (የጋብቻ) መንፈሳዊነት እንቅስቃሴ እርሱም ቀንደኛው ዓለማው የክርስትያናዊ RealAudioMP3 ጋብቻ ጥብቅና ምሉእ ገጠመኙን ለማነቃቃት የሚል መሆኑ የሚነገርለት ዓለም አቀፋዊ ማኅበር የዘንድሮ 11ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤው እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 21 ቀን እስከ ሐምሌ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ፓራይባ ከተማ እንደሚያካሂድ ሲገለጥ። ይህ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ጉባኤ በብራዚል ጠባቂ ቅድስት ድንግል ማርያም ዘአፓረሲዳ ቅዱስ ሐወልት በተገኘበት ክልል የሚካሄድና፣ በእርሷ ጥበቃ ሥር የሚከናውን መሆኑም ኤኵይፐስ ኖትረ ዳመ ማኅበር ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
በዚህ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ 200 የፖርቱጋል ዜጎችና ከፖርቱጋል ቋንቋ ተናጋሪ አገሮች የተወጣጡ 80 ልኡካን እንደሚሳተፉ ኤክለሲያ የተሰየመው የዜና አገልግሎት የሊስቦና ረዳት ሊቀ ጳጳሳትና የፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የዓለማውያን ምእመናን እና ቤተ ሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት አባል ብፁዕ አቡነ ዦኣኪም መንደስ የሰጡትን መግለጫ ጠቅሶ በማሳወቅ፣ ባለ ትዳሮችና ቤተሰብ የመጀመሪያይቱ የአማኞች ማኅበረሰብ ነች፣ ቤተ ክርስትያን ጥንትም አሁንም መልኩን እየለዋወጥ ለሚመጣው ምሥጢረ ተክሊልን የሚያሰናክል ወይንም በምሥጢረ ተክሊል ለሚጸናው ጋብቻ ተጋርጦ የሆነውን ለመቅረፍ ክርስትያን ባለ ትዳሮችን በመደገፍ የምትሰጠው አገልግሎት ክርስትያን ባለ ትዳሮች በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ለባለ ትዳሮች ልኡካነ ወንጌል መሆናቸው የሚያበክር ነው እንዳሉ ኤክለሲያ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.