2012-07-13 13:02:01

የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ


ትላትና የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅድስት መንበር ጉዳይ በተመለከተ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከሐዋርያዊ መንበር ቁጥብ መልእክቶች በስውር በማሾለክ በቅድስት መንበር ላይ የተፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ RealAudioMP3 የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 መኖሪያ ቤት ረዳት የነበሩት ፓውሎ ጋብሪኤለ የወንጀል አጣሪ የበላይ ፍርድ ቤት ተጠያቂው/ተከሳሹ የፈጸመው ወንጀል ለማጣራት በወህኒ ቤት 50 ቀን ማቆየት የሚለው የጊዜ ገደብ ቢጠናቀቅም ቅሉ ተጠያቂው ምርመራው ተጠናቆ ለፍርድ በማቅረብ እስር ወይም ነጻ ተብሎ ሊፈረድበትና ቀዳሚው የምርመራ ውጤት እፍጻሜ ለማድረስ እንዲቻል አሁንም ለተወሰኑ ቀናት ማለት ለሚቀጥሉት እሥር ቀኖች በእስር እንዲቆዩ ሲል የቫቲካን የወንጀል አጣሪው የበላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሰጠበት አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ጉዳዩ የሚያጣራው በብፁዕ ካርዲናል ዅሊያን ሄራንዝ የሚመራው የብፁዓን ካርዲናሎች ድርገት እስከ አሁን ድረስ ስለ ተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ ያካሄደው የማጣራት ሂደት መሠረት ያጠናቀረው ሰነድ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለበጋው እረፍት በሚገኙበት በካስተል ጋንደልፎ እንደሚያቀርብና ቅዱስነታቸው ሰነዱን በማስደገፍ የማጠቃለያ ውሳኔ እንደሚሰጡበት አባ ሎምባርዲ ከገለጡ በኋላ፣ አክለውም በወንጀሉ ለተጠያቂ ጠበቃ የሆኑት ካርሎ ፉስኮ እንደገለጡላቸውም ጋብርኤለ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ መቻላቸውምን ጠቅሰው፣ እስከ አሁን ድረስ በወንጀሉ ተጠያቂ ግለ ሰብ ጋብሪኤለ ብቻ ቢሆንም ቅሉ አንዳንድ ግለ ሰቦች በወንጀል አጣሪው ቀዳሜ የበላይ ፍርድ መጠይቅ እንደተደረገላቸው አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከትላትና በስትያ ለክብራቸው በቀረበው የውህደ ሙዚቃ ትርኢት በእንግድነት ከተገኙት ከኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ጋር መገናኘታቸው ገልጠው፣ በዚህ የበጋው የእረፍት ወቅት ቅዱስነታቸው የናዝሬቱ ኢየሱስ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት የተከታታዩ መጽሓፋቸው ክፍል የሆነውን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕፃንነት ጊዜ በሚያወሱት ወንጌላውያን ላይ የሚያተኵረው ሦስተኛው መድበል እንደሚያጠናቅቁ አስታውቀዋል። በመጨረሻም በቅርቡ በቻይና ለሻንጋይ ሰበካ ረዳት ጳጳሳ እንዲሆኑ አለ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ ለአባ ታደኦ ማ ዳኵይን የተፈጸመው ቅብአተ ጵጵስና የሚያሳዝን ነው። በርግጥ መጀመሪያ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ ሆኖ የቻይና መንግሥት ተቀብሎት ሲያበቃም ቆይቶ የተፈጠረው ሁኔታ ቅብአት ጵጵስናው ሕጋዊነቱን ነስቶታል፣ አባ ማ ዳኵይን ሻንጋይ በሚገኘው ዘርአ ክህነት ትምህር ቤት ውስጥ እንዳሉ ቢታወቅም ቅሉ እስከ አሁን ድረስ ከሳቸው ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት ለማድረግ አለ መቻሉንም አብራርተው፣ በርግጥ ሁኔታው የሚያሳዝን ነው ሲሉ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.