2012-07-13 13:07:09

ዓለም አቀፍ የምግብና የርእሻ ድርጅት-የኤውሮጳ የትብብርና የኤኮኖሚ ልማት ማኅበር


ዓለም አቀፍ የእርሻ ምርት እያሽቆለቆለ ሲሆን ባንጻሩ የምርት ዋጋ ከፍ እያለ መሆኑ ዓለም አቀፍ የምግብና የርእርሻ ድርጅት እንዲሁም የኤውሮጳ የትብብርና የኤኮኖሚ ልማት ማኅበር በማሳወቅ፣ RealAudioMP3 የግብርና ኤኮኖሚ በመደገፍ የምርት እድገት ለማነቃቃትና ብሎም ለማረጋገጥ ጥረት በማድረግ በሚቀጥሉት 40 ዓመታት ውስጥ የምግብ አቅርቦት ጥያቄ ተገቢ መልስ ለመስጠት ብሎም በዓለማችን የሚታየው የርሃብ ችግር ለማስወገድ ለሚደረገው ጥረት መሠረት መሆኑ ያመለክታሉ።
በእርሻው ምርት ላይ ተጽዕኖ የሚሆኑትን የእርሻ ምርት አቅርቦት ዋጋ መቆጣጠር የተፈጥሮ አካባቢ ብከላ እንዳይብስ ብሎም የአረንጓዴው ኤኮኖሚ ማበረታታት እጅግ ወሳኝ መሆኑ የድርጅቶቹ ሰነድ ይጠቁማል።
በሚላኖ የሥነ ምርምር ፖለቲካ መምህር የኤኮኖሚ ሊቅ ሪካርዶ ሞሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ችግሩ የምርት ማሽቆልቆል ሳይሆን፣ የሽያጭ ዋጋ ተመን ከፍ ማድረግ የተለመደ ሆኖ ያለው የኤኮኖሚ ስልት ነው። ስለዚህ የምርት የሽያጭ ዋጋ መናር ምክንያት ሊኖረው ይችላል ይሆናል፣ ነገር ግን የኤኮኖሚ ምርት ማሳየል ብቻ ሳይሆን በእኩል የማከፋፈሉ አሠራር እርሱም የኤኮኖሚ ፍትሕ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄና የገበያው ኤኮኖሚ ማገናኘት ያስፈልጋል፣ የምርት ውጤትና ተጠቃሚው የሚያገናኝ የተስተካከለ የገበያው ዓለም የማስተግበርያ ተቋሞች ያስፈልጋሉ እንጂ እንደሚታየው የምርት ዋጋ ለጥቂት ነጋዴዎች/የንግድ ድርጅቶች እጅ በመተው ባጭሩ በደቡብ ዓለም የሚፈጸመው የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛ እንደ አብነት ጠቅሰው፣ ስለዚህ ገበያ ማስፋፋት ማለትም የአምራቾችና የተጠቃሚው መሠረታዊ ጥያቄ የሚያነብና የሚያገናኝ ገበያ ማስፋፋት ያስፈልጋል። ሆኖም የሽያጭ ዋጋ ላለ ማውረድ ሲባል የሽያጭ ዋጋ እጅግ ከፍ በማለቱ ምክንያት ገዥ የሚያጣው ገበያ ቀር የሆነው ምርት፣ የሽያጭ ዋጋ ተመኑን ዝቅ በማድረግ ተጠቃሚው መሳብ እንጂ የሚታየው ምርቱ ከገበያው ዓለም ማስወገድ የሚለው አሠራር የወቅቱ የገበያ ዓለም ስልት ሆኖ ይታያል። ኅብረ-ብሔራውያን የኤኮኖሚ አውታሮች የሚከተሉት ትርፍ የማግበስበስ ዝምባሌ እንዲሁም የፖለቲካው ዓለም የሚያግባቡት ተጽእኖ ለሚያሳድሩ ለጥቂት አካላት ወይንም ለማኅበራት ዝንባሌ መታዘዝ ልማድ ሆነ ያለው ስልት መወገድ ይኖርበታል። ሰው እንዲሁም ተፈጥሮንም ጭምር ማእከል ያደረገ ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካና ማኅበራዊ ሂደት ወሳኝ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.