2012-07-06 13:25:46

የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ


በቅርቡ የብፁዓን ካርዲናሎች ምክር ቤት ያካሄደው ስብሰባና የተለያዩ በቅድስት መንበርና በአገረ ቫቲካን በተመለከቱ ወቅታዊ ጉዳይች ሥር የቅድስት መንበር የዜናን ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል በጋባእያ ተገኝተው RealAudioMP3 ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. መከር የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ መሥተዳድር ሂደቱና እንቅስቃሴው እንዲሁም የዚሁ የኤኮኖሚ መሥተዳድር ጉዳይ የሚከተለው አዲስ የመመሪያ ደንብ በማቅረብ በቅርቡ የተሰጡት አዳዲስ የኃላፊነት ሹመት በትክክል መግለጫ እንደሚሰጥበትም ገልጠው፣ በተካሄደው የብፁዓን የካርዲናሎች ምክር ቤት ስብሰባ ምልአተ ጉባኤ የተረጋገጠበትና ኵላዊነትን የመሰከረ ነበር ብለዋል።
ምንም’ኳ በዓለማችን የኤኮኖሚና የቁጠባ ቀውስ ገና ያለ ቢሆንም፣ የቁጠባ መዛባት አሁንም የቅዱስ ጴጥሮስ መባ ከፍ እያለ መምጣቱንም፣ የቫቲካን ቤተ መዘክሮች ገቢ እድገት ማሳየቱንም ገልጠው በእውነቱ ለኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሚሰጠው ድጋፍ የሚመሰገን ነው።
የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ በተመለከተም በተለይ ደግሞ ስለ ቫቲካን ረዲዮ የተከናወኑት ለውጦች የብፁዓን ካርዲናሎች ምክር ቤት ጉባኤ ተገቢነቱ በመገንዘብ ድጋፍ መስጠቱንም ገልጠው፣ ካለው የኤኮኖሚ መዛባት ጋር የተስተካከለ አሠራር እየተከተለ መሆኑ አብራርተው ሆኖም የሠራተኛ ቅነሳ እቅድ አንደማይኖር ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ቅድስት መንበርናን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲያገለግሉ የተሰጣቸው የተልእኮ ኃላፊነት እንዲቀጥሉበት የሰጡት እማኔ ለብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ያላቸው አቢይ ግምት የሚገልጥ ነው ካሉ በኋላ በመጨረሻም የማነይቫል (በሕገ ወጥ የሚካበተው የገንዘብ ሃብት እንቅስቃሴና ሕገ ወጥነቱን ለመሸፈን በጤናማ ኤኮኖሚ የማዋል ሂደቱና የአሸባሪያን የገንዘብ ሃብት እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር) ኮሚቴ ቅድስት መንበር በተመለከተ የሰጠው ግምገማ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንና ጉዳይ ብዙ የሚያሳስብ እንዳልሆነ ገልጠው ቅድስት መንበር በተገባ በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደምትገኝ ነው በማለት የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.