2012-07-04 14:15:04

የኤውሮጳ መጻኢ በእምነት በኵል


የታደሰ የእምነት ምስክርነት በፖለቲካው ዓለም ለኤውሮጳ ብሩህ መጻኢ መንገድ መሆኑ አርባ የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የሚያቅፈው የኤውሮጳ አገሮች RealAudioMP3 ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የዋና ጸሓፍት ጉባኤ እ.ኤ.አ. በኤዲምቡርግ ከሰኔ 29 ቀን እስከ ሓምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማእከል በማድረግ የክርስትያኖች ሚና በማኅበራዊ ዘርፍ በሚል ርእስ ሥር ባካሄደው 40ኛው ይፋዊ ምሉእ ጉባኤ ፍጻሜ ባወጣው የማጠቃለያ ሰንድ እንዳሰመረበት ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።
አዲስ አስፍሆተ ወንጌል፣ ሁሉም የካቶሊክ ምእመን፣ የተቀበለው እምነት በውስጣዊ ኅዳሴ አማካኝነት እንዲኖር የሚል ጥሪ የሚያሰማ መሆኑ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ዋና ጸሓፍት ጉባኤ የፍጻሜ ሰንድ ያሰፈረው ሐሳብ እምነትና ዕለታዊ ሕይወት በመነጣጠል የሚኖር ከቃልና ከሕይወት ምስክርነት ጥሪ የራቀ የማይገናኝ የተዘጋ እምነት የመኖር አዝማሚያ በተስፋፋበት በጥንታዊው ክርስትያን ክፍለ ዓለም፣ እግዚአብሔር በግላዊ ሕይወት አጥሮ መኖር በኤውሮጳ ለዘርፈ ብዙ ቀውስ መሠረት መሆኑ ከታሪክ የምንረዳው እውነት ሲሆን፣ የሃይማኖት ነጻነት መጣስ መንግሥታት በቤተ ክርስትያን ጉዳይ ለጣልቃ ገብነት ተግባር የሚገፋፋ መሆኑም ያለው ወቅታዊው ሁኔታ መሠረት በማድረግ በማብራራት፣ ያለው የግለኝነት የፍንጥዝያ፣ ኣልቦ ስነ ምግባርና አልቦ ግብረ ገብነት ኑሮ የተሰኙት ለጨለምተኛ ሕይወት መንገዶች ቤተ ክርስትያን በመለየት አእምሮን በማነቃቃት ልብ ለእምነት ክፍት እንዲሆን በማስተማር፣ የእምነት አመክንዮ በማስፋፋት የታደሰ ቀልብ በመከተል ግብረ ገባዊና ሥነ ምግባራዊ ደንቦች የምታቀርብ ብቻ ሳትሆን፣ የስነ ምግባርና የግብረ ገብ አመክንዮነት በማስተማርና በማስገንዘብ ግብረ ገብና ሥነ ምግባር ልዳቢ ሳይሆን በሰው ልጅ ህሊና የእግዚአብሔር ድምጽ መሆኑ ታስተምራለች።
ተስፋ የሚመነጨውም ከፖለቲካ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው፣ ስለዚህ ገዛ እራስ በእርሱ ብርሃን ቦግ እንዲል ሲፈቀድ ወደ ዓለም ብርሃን ማድረስ ይቻላል በማለት በሰሜን አመሪካ የእምነት ነፃነት ለአደጋ የሚይጋልጥ በመንግሥት እየጸደቁ ያሉት ሕጎች እንዲሁም በኤውሮጳ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በአጋኖ የሚነዙት በይሆናል የሚሉት እውን ዜና እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ የሚከተሉት የሐሳት መንገድ ቤተ ክርስትያን የሚገልጣት እንዳልሆነ የዋና ጸሓፍት ጠቅላይ ጉባኤ ፍጻሜ ሰነድ እንደሚያመለክተውም ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.