2012-06-12 09:52:28

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ዛሬ በኢጣልያና ሌሎች ብዙ አገሮች ኮርፑስ ዶሚኒ ማለት በዓለ ቅዱስ ቁርባን፤ የጌታ ቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ ታላቅ በዓል ይከበራል፣ በዛሬው ቀን በብዙ አደባባዮችና ጐዳናዎች በጥቀ ቅዱስ ቍርባን የሚደረግ ዑደት ዘወትር ሕያው የሆነ ልማድ ይደረጋል፣ በሮማ ከተማ በሃገረ ስብከት ደረጃ ባለፈው ሓሙስ በትክክለኛ ዕለቱ የበዓሉ ሥርዓተ ዑደት ተደርገዋል፣ በዚሁ ዕለት ኢየሱስ በቅዱስ ቍርባን አማካኝነት በመሃከላችን የመኖሩ ደስታን ምስጋና በየዓመቱ በክርስትያኖች ይታደሳል፣
የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ በዓል ለቅዱስ ቍርባን የሚቀርብ ታላቅ ሕዝባዊ አምልኮ ነው፣ በዚሁ ምሥጢር ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዳሴም ባሻገር አለምንም የጊዜ ገደብ ሁሌ በመካከላችን መኖሩን ያረጋግጥልናል፣ ቅዱስ ዩስጢኖስ ቤተ ክርስትያን ስትመሠረት ጥንታዊ ምስክርነት ስለ ቅዱስ ቍርባን ሥርዓተ አምልኮ ትቶልናል፣ ቅዱሱ ስለዚህ ሲናገር “በቅዳሴው ለተሳተፉ ቅዱስ ቍርባን ከታደለ በኋላ በቦታው ላልተገኙ ደግሞ በዲያቆናት ይላክ ነበር” ይላል፣ ስለዚህ በቤተ ክርስትያናት የከበረው ቦታ ቅዱስ ቍርባን የሚቀመጥበት መንበረ ታቦት ነው፣ ስለዚህ ምስክርነት በምናገርበር ባሁኑ ጊዜ ባለፉት ቀናት የጀመረው ገናም በሰሜናዊ የጣልያን አገር በኤሚልያ ሮማኛ እጅግ ለተጐዱ ቤተ ክርስትያናት ስላስታውስ ለማለፍ አልፈልግም፣ በዚህ አደጋ የክርስቶስ ቅዱስ አካል የሆነው ቅዱስ ቁርባን በመንበረ ታቦት በፍርሽራሽ ተደፍኖ ይገኛል፣ እዛ የሚገኙ ማኅበረ ክርስትያን ከካህናቶቻቸው በባዶ ሜዳ ወይም በተንዳ እንዲያስቀድሱ ተገደዋል፣ ስለሁላቸው በሙሉ ልቤ እጸልያለሁ፣ ስለሚሰጡት ምስክርነትና ለመላው ሕዝብ ስለሚያበረክቱት አመስግናቸዋለሁ፣ ሁኔታው በጌታ ስም እንድንሰብሰብና የነጋድያን ዳቦ ከሆነው ከቅዱስ ቍርባን ኃይል ማግኘት አስፈላጊነትን የሚያሳድስ ነው፣ ይህንን የሕይወት እንጀራ ቈርሶ ከመከፋፈል ሕይወት ንብረት እና የኑሮ ክብደትን ለመከፋፈልና እንግዳ ለመቀበል የሚያስፈልግ ጸጋ ይወለዳል፤ ይታደሳልም፣
የቅዱስ ሥጋሁ ወክቡር ደሙ በዓል በቅዱስ ቁርባን ፊት በሚደረገው ስግደትና አስተንትኖ የሚገኙትን ትሩፋት ያሳስበናል፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ጳውሎስ 6ኛ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የቅዱስ ቍርባን አምልኮ እንደምትታመን ለማስታወስ እንዲህ ብለዋል፤ “በቅዳሴ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከመሥዋዕተ ቅዳሴ ውጭም የተባረከውን ኅብስት በታልቅ ጥንቃቄ በማስቀመጥ ክርስትያን ም እመናን ሊያመሰግኑትና በታላቅ ደስታ ዑደት በማካሄድ ሊባረኩ ከፈለጉ ከመንበረ ታቦት እያወጣች ታበርክተዋለች” (ሐዋርያዊ መልእክት ሚስተርዩም ፊደይ - ምሥጢረ እምነት ቁ.57)፣ የቅዱስ ቍርባን ስግደት ጸሎት በግል በመንበረ ታቦት በአስተንትኖ እያሉ ለመድረስ ይችላል፣ እንዲሁም በኅብረት መዝሙረ ዳዊት በመድገም ይሁን ሌላ መዝሙር በመዝመር ሁሌ ግን ጽሞና ብዙ ጊዜ ሊሰጠው ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም በቅዱስ ቍርባን ያለው ኢየሱስ በልባችን ውስጥ ሲናገረን ለመዳመጥ እንድንችል ነው፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም የዚህ ዓይነት ጸሎት አስተማሪ ናት፣ ምክንያቱም ኢየሱስን በእምነት ዓይን ለማየትና በልብ ተቀብሎ በሰብ አዊና መለኮታዊ ኅላዌው ያስተነተነው ከእርሷ በላይን ከእርሷ የሚበልጥ ማንም የለምና፣ በእርሷ አማላጅነት በእያንዳንዱ የቤተ ክርስትያን ማኅበር የምሥጢረ ቅዱስ ቍርባን እውነተኛና ጥልቅ የሆነ እምነት ይስፋፋ፣
ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ፤
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፣ እፊታችን ሓሙስ ሰኔ 14 ቀን በዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ የደም ለጋሾች ቀን እንደሚዘከር ለማስታወስ እወዳለሁ፣ የብዙ ህሙማን ሕይወት ለማዳን ይህንን የአጋርነት ጥሪ በመቀበል ደም ለሚለግሱ ሁሉ ምስጋናየን ለመግለጥ እወዳለሁ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.