2012-06-08 14:57:04

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ግለኝነትና ራስ ወዳድነትን ማሸነፍ”


እ.ኤ.አ. ከግንቦት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በፖላንድና በኡክራይን ለሚካሄደው የኤውሮጳ አገሮች የብሔራው የእግር ኳስ ምርጥ ቡድን ግጥሚያ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ RealAudioMP3 ለፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ለብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ሚካሊክ “ቡዱናዊ ስፖርት የግለኝነትና የልቅ ራስ ወዳድነት አመክኒዮ ለማሸነፍ የሚያግዝ መሆን አለበት” በሚል ጥልቅ ሃሳብ ላይ ያተኮረ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
የኤውሮጳ አገሮች የብሔራዊ የእግር ኳስ ምርጥ ቡድን ውድድር መላ የኤውሮጳ ኅብረተሰብን የሚመለከትና ቤተ ክርስትያንም ችላ የምትለው ወይንም ግድ ያማይሰጣት ባህል አይደለም፣ እርሱም በዚህ የባህል ዘርፍ የሚሳተፉትን ሁሉ የመንፈሳዊነት ጉዳይ እርሷን የሚመለከት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው፣ በትምህርተ ክርስቶስ በሊጡርጊያና በጸሎት መርሃ ግብሮች ሥር ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ በማስታወስ፣ ስፖርት ሰብአዊ ክስተት ያለው እምቅ ኃይል ለሰው ልጅ ለተሟላ እድገት ልዩ መገልገያ መሣሪያና የሰው ልጅ ልክነት ያለው ኅብረተሰብ ለመገንባት የሚያገለግል አካፋይ ነው ካሉ በኋላ ከዚሁ ጋር በማያያዝ የወድማማችነት የቸርነት ቅንነትና ለሰብአዊ አካል ክብር የተሰኙት በማንም አትሌት ችላ ሊባሉ የማይገባቸው አንድ የሰለጠነ ብኄረ-ኅብረተሰብ ለመገንባት አስተዋጽዖ የሚሰጡት እሴቶች የሚያስተጋባበት ሆኖ ከፉክቻና ከተቃዋሚነት ይልቅ ቅን ውድድር የሚያሰኘው ጥረት የሚታይበት መሆን አለበት። ስለዚህ ስፖርት ፍጻሜ ሳይሆን የብሔር ሥልጣኔ ለማረጋገጥ የሚያግዝ ሰዎችን ለሌሎችና ለገዛ እራስ ችግር ከሚያስከትል ጉዳይ ለማራቅ የሚደግፍ መሣሪያ ነው በማለት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 28 ቀን 2000 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያሉትን ሃሳብ ጠቅሰው፣ በጋራና በቡድን ከሚፈጸሙት የስፖርት ዓይነቶች ውስጥ አንዱ የእግር ኳስ ስፖርት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው የመከባበር መንፈስ የሚንጸባረቅበት ንጹሕ ግጥሚያ የሚከናወንበት ግለኝነትና የራስ ወዳድነት አመክንዮ የማይታይበት ሰብአዊ ግኑኝነት እርሱም ሁሉን እንደየ ደረጃው ለወንድማማችነት ለፍቅርና ለእውነተኛው የጋራ ጥቅም ሥፍራ የሚያሰጥ አመክንዮ የሚታይበት መሆን አለበት ብለዋል።
ቅዱስነታቸው ሰላም እና እውነተኛ ደስታ የሚንጸባረቅበት የላቍት በቃልና በሕይወት ሊሚሰከሩ የሚገባቸው ሰብአውያን እሴቶች በሁሉም ዘንድ እንዲኖር የሚያግዝ የስፖርት መርሃ ግብር እንዲሆን ባሰፈሩት ቃለ ምዕዳን ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.